EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Monday, 4 March 2019

ወደ ታላቅነት የሚወስደው ጉዞ


(በአቡ ኬ)

በአለም ላይ ህብረት፣ አንድነት፣ ትብብርና የሚሳሰሉት መሰባሰብን የሚያወሱ ቃላቶች ይዘወተራሉ። የተባበሩት መንግስታት፣ የአፍሪካ አንድነት፣ የተባበሩት የአሜሪካ ግዛቶች ወይም USA፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የተባበሩ አረብ እምሬቶች ውይም UAE ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።

እነዚህ አጠራሮች ቃላቶቹ ስለሚያምሩ ብቻ የመጡ አይደሉም ለአመታት ተጸንሶ ምጡ በራሱ ተጨማሪ አመታትን ፈጅቶ የተወለዱ ናቸው። ዛሬ ሃያል የምትባለው አገረ አሜሪካ የመሰባሰብ ውጤት ናት። በተጽኖ ፈጣሪነቱ የሚጠቀሰው የአውሮፓ አገራት ህብረት የመሰባሰብ ውጤት ነው። የአለምን አገራት በአንድ የሚያሰባስበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም እንዲሁ።

ምክንያቱም ግልጽ ነው ‘’አንድነት ወይም መሰባሰብ ሃይል ስለሆነ ድር በያብር አንበሳ ያስር እንደሚባለው አንድ ሆነ ብቻህን መስራት የሚትችለው ነገር በላይ ተባብሮ የሚተሰራው ነገር ይልቃል። እንደዚህ አይነት ትብብሮች አብሮ የመግዘፍ ጉዳይ ግን ወደ አፍሪካ አገራት ሲመጣ ያን ያህል ጎልቶ አይታይም። በስንትና ስንት ጥረት ከተቋቋመው የአፍሪካ ህብረት ጀምሮ ተጽኖ ፈጣሪነቱ አጠያያቂ ነው። አብዛኛው የአንድ ቀጠና አገራት ወይም ጎረቤት አገራት መካከልም ተባብሮ ያለውን አዋጥቶ ትልቅ ከመሆን ይልቅ ሽኩቻ ይበዛል።

ይሄ ነገር ግን ቆየ ወይም አልተሳካም ተብሎ የሚታው ነገር ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች ይደረጋሉ ለዚህም በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 6023 ላይ የተቀመጠውን አገራትን የማስተሳሰር ግብ የተቀመጠው። ከዚያም ቀደም ተብሎ የተሞከሩና የተወሰኑ ውጤቶችንም ያስመዘገቡ የደቡብ አፍሪካ አገራት የልማት ትብብር SADEC የምዕራብ አፍሪካ ECOWAS እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካውን IGAD መጥቀስ ይቻላል።

አሁንም ግን ገና ብዙ ስራ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት በመደመር ፍልስፍናቸው ከአገራዊ አንድነት አልፎ ቀጠናዊ አንድነትን የሚያቀነቅን የጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ አህመድ ራዕይ ይህንኑ እውን ለማድረግ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መካከል ይጠቀሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እንደሚታወቀው ወደ ስልጣን ከመምጣቸው ቀዳሚ ስራቸው ካደረጉት ተግባራት መካከል ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ያላትን ለሁለት አስርት አመታት የተቋረጠውን ግንኙነት፤ ሁለት ወንድማማች ህዝብ መካከል መኖር የነበረበትን ሰላማዊ ግንኙነት ወደ ቦታ መመለስ ነበር። ሁለቱ አገራት ማካከል ተዘገቶ የነበሩትን ድንበሮች ከፋፍቶ ህዝቡ በየብስም ይሁን በአየር ትራንስፖርት ተጉዞ እንዲገናኝ አድርገዋል።

በዚህ ተግባራቸው ከሁለቱ አገራት ህዝብ አልፎ በአለም ዙሪያ ካለው ህዝብ አድናቆት ተችረዋቸዋል፤ እውቅንም አግኝተዋል።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ አላማቸው ሁለቱ አገራት መካከል ሰላም አንዲወረድ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የቀጠናው አገራት ተደምሮ በጋራ እንዲያድጉ ማድረግም እንደሆነ ሲናገሩ ተደመጡ። ተናግሮ ብቻም አላቆሙም በኤርትራና ጂቡቲ መካከል የነበረው የድንበር አከለካባቢ ግጭት አብቅቶ ሰላም እንዲወርድ ማደራደር ጀመሩ።

Thursday, 28 February 2019

የአድዋን የድል በዓልን በአዲስ የለውጥ መንፈስ


(ሚራክል እውነቱ)የአድዋ የድል በዓል  በመላው ሀገራችን በድምቀት ለማክበር እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ከዛሬ 123 ዓመት በፊት ስለተፈጸመው የአድዋ ድል ልዩ ክብር የምንሰጥባቸው በርካታ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ አድዋ ዘመናዊት ኢትዮጵያን ከጥንታዊ ታሪኳ ጋር ያገናኘ ታላቅ ገድል የተፈፀመበት መሆኑ ከታሪካዊ ዳራው መረዳት ይቻላል:: የአድዋ ድል ኢትዮጵያ ሲባል አንገታችንን ቀና አድርገን በኩራት እንድንራመድ የጥንት አባቶቻችን ጀግንነትና ለሀገር ያላቸውን ፍቅር የተመሰከረበት የጦርነት ድል መሆኑን መስካሪ አያሻውም፡፡


መች ይሄ ብቻ ባህላችን ሳይበረዝ ሳይከለስ ተጠብቆ እንዲኖር አስችሎናል- አድዋ:: ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት በአውሮፓውያኑ መጤ ባህል ቅኝ ግዛት የመወረር ምልክቶችን ብናይም፤ የመላ አፍሪካዊያን ኩራትና ድል የሆነው የአድዋ ድል በጦርነት ወቅት እምቢ ለሀገሬ በሚል አይበገሬነት መንፈስ ከአራቱም ማዕዘናት ገንፍሎ በመውጣት የኢትዮጵያዊያንን አንድነት ለአፍሪካዊያን ብሎም ለዓለም ሀገራት ከፍ አድርጎ እንዲታይ ያስቻለ ድል መሆኑ እንድናከብረውም እንድንዘክረውም ምክንያት ሆኖናል፡፡ 

ይህን በዓል እንድናከበር ያስገደደን ምክንያታችን የጣሊያን መንግስት ባህር አቋርጦ ከአፍ እስከ ገደፉ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ታጥቆ ሀያልነቴንና ታላቅነቴን ለዓለም አሳይበታለሁ ባለው ጦርነት ላይ ኢትዮጵያዊያኑ  በወንጭፍና በጎራዴ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት አንገቱን አስደፍቶ ወደ መጡበት ባህር ማዶ መመለሳቸው ሀገራችን በዓለም ዓቀፍ መድረክ እንድትታወቅና እንድትከበር ምክንያት ስለሆነ ነው፡፡ 

በርካታ የአውሮፓ ሀገራት የአፍሪካን ምድር እንደ ቅርጫ መቀራመት ብቻ ሳይሆን ሀያልነታቸውን በማሳየት ቀኝ ገዥነታቸውን በየሀገራቱ ያለውን እምቅ ሀብቶችን የግላቸው በማድረግ አሳይተዋል፡፡ በአፍሪካ ምድር ለጠላት ያልተንበረከኩ ሀገራት ቢኖሩ ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ናቸው፡፡ በተለይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነጻነታችንን አስከብረን እንዴት መኖር እንደምንችል አስመስክራበታለች፡፡ ለሌሎች ሀገራት ሕዝቦችም አርዓያ ሆኗቸዋለች፡፡ ለነፃነታቸው በቁርጠኝነት እንዲታገሉ ምሳሌ በመሆን ለዓለም የነፃነት ትግልና ክብር ምሳሌ የሆነች ሀገር ናት - ኢትዮጵያ፡፡ ሌላው የአድዋ ጦርነት ጥቁር ሕዝብ ማሸነፍ እንደሚችልና የሰው ዘር ሁሉ እኩል እንደሆነ አውሮፓውያን ትምህርት ያገኙበት ድል ነው፡፡ብዙዎቻችን የአድዋ ድል በዓልን ለምን መዘከር እንዳስፈለገን ግልፅ ስለመሆናችን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ከዚህ አኳያ አንድ ፅሁፍ ላይ ያነበብኩትን ላካፍላችሁ፤ ‹‹አድዋን ድል የምንዘክረው በታሪካችን ስለምንኮራ ብቻ አይደለም፡፡ እንደ አንዳንዶችታሪክ ተወቃሽ ትውልድ ላለመሆንም ጭምር እንጂ›› ይላል፡፡ ምን ይሄ ብቻ ሌላም ምክንያት እናስቀምጥ በአለም ህዝቦች ታሪክ ለነጭ ትዕቢት ድንበር አልባ የዘረኝነት መርዝ የማይገዛ ጥቁር ህዝብ መኖሩን ያስመሰከረ የዓድዋ ድል ስለሆነ ልንዘክር ይገባናል ይላል ፅሁፉ።የነጭን አንገት ያስደፋ በሀፍረት ያሸማቀቀ በፍርሀት ያርበደበደ ኢትዬጵያዊነት ኩራት አፍሪካነት ኩራት ጥቁርነት ክብር መሆኑን ያስመሰከረ የአፍሪካውያን ኩራት የዓድዋ ድል መሆኑን ሌላኛው እንደ ምክንያት አድርጎ ያስቀምጠዋል ።
የአድዋ ድል በዓልን ስናከብር በኢትዮጵያችን የመጣውን ለውጥና ህዝቡ እየተመለከተ ያለውን የሰላም፣የአንድነትና የልማት አብሪ ተስፋዎች እንዳይደበዝዙ ከድርጅታችን ኢህአዴግ ጎን የምንሰለፍበት ጊዜ ላይ መሆናችንን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የዘንድሮው 123ኛው የዓድዋ የድል በዓል ስንዘክር በተለየ ወቅት ላይ ሆነን ነው፡፡ ከዚህ በፊት በሀገራችንን አጋጥመውን የነበሩ ችግሮች በይቅርታ በዕርቅ ዘግተን እቺ በአያት ቅድመ አያቶቻችን ደምና ላብ የተገነባች ሀገር ወደፊት ለማራመድ ቆርጠን በተነሳንበት ወቅት ላይ ነው፡፡   ሀገርን የማበጣበጥ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ፊት ለፊት በመታገል ኢትዮጵያችንን ከትርምስ የማዳንና መሰረታዊ ለውጦችን የማስቀጠል ድርብ ሀላፊነታችንን ለመወጣት ዳግም ቃል የምንገባበት የድል በዓል ሊሆን ይገባል መልዕክቴ  ነው፡፡ የአባቶቻችንና የአንድነትና የመተባበር መንፈስ ወርሰን ወደፊት ታላቅ ሀገር እንገንባ፡፡Sunday, 24 February 2019

መደማመጥ ለአገራዊ አንድነት መሰረት

(ፑላሎ ፓፒ)

በአገራችን ባህልና ወግ ማልደው ሲነሱ ቸር አውለኝ ማለት የተለመደ ነው፡፡ እናም እኔም ቸር አውለኝ ብዬ መልካም መልካሙን እያሰብኩ ወደ መስሪያ ቦታዬ የሚወስደኝ ታክሲ ውስጥ ገባሁ፡፡ የታክሲው ረዳት ሂሳብ ሲል ሁሉም ወደኪሱ እየገባ ሂሳቡን እየሰጠ መልስ ያለውም መልሱን እየተቀበለ ቀጠልን፡፡ በመሃል መልስ ሰጠኽኛል አልሰጠኸኝም ጭቅጭቅ ተነሳ፡፡ ሁሉም ያወራሉ፡፡ ረዳቱም ተሳፋሪውም፡፡ ቀጠል አለና ደግሞ ሌላው ተሳፋሪ ‹‹ተረጋጋ ሰጥቶሃል›› አለው፡፡ አሁን ጭቅጭቁ ከአንድ ወደ ሁለት ሰፋና ሌሎች ተሳፋሪዎችም ታክለውበት መጯጯ ሆነ፡፡ አዳማጭ በሌለበት እንዴት መግባባት ይቻላል፡፡ ወይ መደማመጥ ደጉ አልኩኝ፡፡ ሾፌሩ በመሃል ገብቶ በቃ ተወው ስህተት ባትሆን ይሄ ሁሉ ሰው አይናገርህም አለና ረዳቱን ሊያቀዘቅዘው ሞከረ፡፡

ይሄ ትንሽ የሚመስል የታክሲ ገጠመኝ ነገሩን አገራዊ ወደሆነው ሁኔታችን እንደስበው አስገደደኝ፡፡ እኛስ ከስሜት ወጣ ብሎ በአስተውሎት ነገሮችን መመዘን፤ እንደ አገርም ለመግባባትም ላለመግባባትም መደማመጣችን በህይወታችን ውስጥ ያለውን ትሩፋት በመገንዘብ ነው ወይ እየተጓዝን ያለነው፡፡ ይህ ሁላችንም ልንመልሰው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ለሃሳብ ነፃነት  እውቅና የሰጠች፤ ሰዎች የመናገር የመፃፍ መብታቸው የማይገፈፍ መሆኑን በህገመንግስቷ የደነገገች አገር ናት፡፡ ይህ የሃሳብ ነፃነት አንዱ በአንዱ ላይ ተፅእኖ እንዲያሳድር ሳይሆን ሰዎች ሰብዓዊ የሆነ መብታቸውን በመጠቀም አንዱ የአንዱን መብት አክብሮ መንቀሳቀስ እንዲችል ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡ የአገራችን ህዝብ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙትን ፈተናዎች በአስተዋይነቱ ሲሻገራቸው የቆየ ህዝብ ነው፡፡ ከቤተሰብ ጀምሮ ችኩልነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንደሌለው በምሳሌ ሳይቀር እየተነገረው ነው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚያድገው፡፡ የቸኮለ አፍሶ ለለቀመ እንደዲሉበችኩልነት ውስጥ አስተዋይነት የለም፡፡ ራስን ስሜትና ፍላጎት ከመጫን ባለፈና አምባገነን ከመሆን የዘለለ ትርፍ የለውም፡፡ 


አሁን አገራችን ያለችበት ሁኔታም የራሰን ስሜትና ፍላጎት ሌላው ላይ ለመጫን የሚደረግ መውተርተር ነው፡፡  አገራችን የሚያስፈልጋት ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ሆኖ ሳለ አንዱ ወገን በጉልበት እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን በሚል እሳቤ የሚደነፋበት መደማመጥ የሌለበት የፉክክር ጊዜ ሆኗል፡፡ አገራችንና ህዝቦቿን ከገቡበት ቀውስ ማውጣት የሚቻለው መንግስትን ያዳክማሉ ተብለው የሚታሰቡ ተግባራትን በመከወን ሳይሆን በጋራ ዓላማን ግብ አገር የሚያቃና ተግባር በመፈፀም ነው፡፡  

ዛሬ በቡድን ተዋቅሮ ጎራ ለይቶ መነቋቆር ቀላል ሊሆን ይችላል፤ ነገ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ የተፈጠረውን ክፍተት ማጥበብ  እንደ ማስነው ጉድጓድ የሚቀል አይሆንም፡፡ ሁላችንም እንደምናስተውለው አሁን አገራችን ጉራማይሌ በሆነ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ባለፉት ዓመታት በአገራችን የተከሰተውን ችግር ከመሰረቱ መቅረፍ የሚያስችሉ በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ህገመንግስቱ በግልፅ ያስቀመጣቸው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚሸራረፉበት ሁኔታ እንዳይኖር ያለፈውን አፈፃፀም ማስተካከል በሚቻልበት ሁኔታ ማስተካከያዎች ተደርገዋል፡፡   

አገራችን የምትከተለው የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲጎለብት እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያግቧቸው ጉዳዮች ላይ ተቀራርበው መነጋገር የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ አገር ማኩረፊያ እንጂ ከአገር አኩሩፎ በባዕድ አገር መኖር እንዲበቃ በውስጥ ትግል ዴሞክራሲያዊ የሆነች አገር ለመገንባት የሚያስችል ስራ ተሰርቷል፡፡ እነዚህና መሰል ተግባራት በለውጥ ሂደት ውስጥ የተፈፀሙ እና እየጎለበቱ የሚሄዱ ናቸው፡፡

አሁን ላይ መንግስት እየወሰዳቸው ያለውን የሪፎርም ስራዎችን በአስተዋይነት መመልከት ይገባል፡፡ መንግስት ጆሮ ስጡኝ ሲል ህዝብ ጆሮ ሊሰጠው ይገባል፡፡ መንግስትም ህዝብን የሚዳምጥበት ሁኔታዎችን በማመቻቸት አገራችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ በአስተዋይነት መሻገር ይገባል፡፡

ይህ የመደማመጥና ገንቢ ትችት እየተሰጣጡ የመተራረም ባህል ከጠፋ ቆመንለታል ያለነውን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ ከመውደቀ ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ እያንዳንዱ ዜጋ ከቤቱ ጀምሮ የሚከፍለው ማናቸውም የጊዜና የእውቀት መስዋዕትነት ነገውን የተሻለ ለማድረግ ካለው ጉጉት የመነጨ ነው፡፡ ይህን የግልም ሆነ አገራዊ ፍላጎት ማሟላት የሚቻለው የመደማመጥ ባህል በማዳበርና ችግሮችን በአስተዋይነት በመሻገር ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ባለው የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ በሁሉም አቅጣጫ እየተሸረሸረ የመጣው የመደማመጥ ባህላችን እንዲያንሰራራ ማድረግ ይገባል፡፡ መደማመጥ ከሌለ መስማማት አይኖርም፤ የጋራ የሆነ እምነት መገንባት አይቻልም፡፡ መደማመጥ ከሌለ ሃሳቡን ሳይሆን ከሃሳቡ በስተጀርባ ያለውን አሉታዊ ትርጉም ወደማሰለሰል ይኬዳል፡፡ መደማመጥ ለሁሉም ነገር መሰረት ነው፡፡ መደማመጥ የሩቅ አሳቢነት ምልክት ነው፡፡ መደማመጥ የአስተዋይነት ምልክት ነው፡፡ መደማመጥ የስልጣኔ መለኪያ ነው፡፡

Wednesday, 20 February 2019

የአባገዳዎችና ሃደ ሲቄ የእርቅ ጉዞ መጨረሻው ያጓጓል


(አቡ ኮ)

በአገሪቱ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከህዝቡ ገፍቶ የመጣው ለውጥ ጋር ለመራመድ የአመራር ለውጥ አድርጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በርካታ ብሔራዊ መግባባትን የሚያጠናክሩ እርቅና መቀራረብ ላይ ያተኮሩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

ከነዚህም መካከል በአገር ቤት በተለያየ ምክንያት በማረሚያ ቤቶች የነበሩ የነበሩ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ማድረግና ከአገር ውጭ ሆነው ሲታገሉ የነበሩ ሲንቀሳቀቁ የነበሩየፖሊቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት መጥተው በሰላማዊ መንግድ እንዲታገሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበዓለ ሲመታቸው ካደረጉት ንግግር ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ይህንን ጥሪ ተቀብለው ሁሉም ስለኢትዮጵያ ብለው የተደራጀ የፖሊቲካ ድርጅቶች እናት አገራቸው ተመልሰዋል። ከነዚህም መካከል  የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር /ኦነግ/ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ሂደት  በርካታ ኢትዮጵያዊያን በአደባባዮች ወጥተው ደስታቸውን እንዲገልጹ አስችሎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን የኋላ ኋላ በምዕራብና  መደቡብ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ታጥቆ የሚንቀሳቀሱ አካላት በመኖራቸው ግጭቶችና የሰላም መታወኮች ተከስቶ ቆይቷል። ይሄው ድርጊትም የአገሪቱ ዜጎች ዘንድ የእርቅና የመተባበር፤ ተደመሮ ለጋራ እድገት የሚሰራበት ወቅት ነው የተባለበት ጊዜ ላይ መሰል አለመረጋጋቶች መፈጠራቸው ግራ የሚያጋባ ስሜት መፍጠሩ አልቀረም።

ያኔ ነበር ጉዳዩ ያሳሰባቸው የኦሮሞ አባገዳዎችና ሃደ ሲቄዎች፣ እውቅ ፖለቲከኞች፣ አክቲቭስቶችና ገለልተኛ የሆነ ልሂቃንን ይዞ ለሰላም የኦነግና የክልሉን መንግስት ደጅ መጥናትን የተያያዙት። በዚህም ሁለቱ አካላት ወደ ሰላማዊ ትግል የሚደረግ ጉዞ ላይ ያጋጠመው ችግር ዙሪያ ‹‹እኛ እናሸማግላችሁ፤ የህዝቡም የደስታ ጭላንጭል ሙሉዕ ይሁን ኑ ሁሉንም እኔ ፈታለው›› ብሎ መንግስትንም ኦነግንም ጠየቀ።

ጥያቄያቸውም በሁለቱም ሰላም ፈላጊ ወገን ተቀባይነት አግኝቶ በአባገዳዎች የሚመራ ቴክኒካል ኮሚቴ ተቋቋሞ ወደ ስራ ከተገባም  ወር አለፈው። ኮሚቴው የመጀመሪያ ስራው ያደረገውም በአምቦ ትልቅ የእርቅ ጉባዔ ተጠርቶ ኮርማ ታርዶ በኦሮሞ ህዝብ ባህል መሰረት እርቅ መውረዱን ማብሰር ነበር።  በመቀጠልም የኦነግን ታጣቂዎች ትጥቃቸውን  በክብር ለአባገዳዎች አስረክቦ ወደ ተዘጋጁ ካምፖች ገብቶ ተገቢውን ስልጠና በመውሰድም ወደ ቀጣዩ ሰላማዊ የህይወት ምዕራፍ እንደሚሸጋገርም ተወሰነ።

Tuesday, 19 February 2019

የዜጎችን የመጠለያ ጥያቄ ለመመለስ በላቀ ትጋት

(ነፎ አብዲ ኬ)

ከተማ በተለያዩ ምሁራን የተለያየ ትርጉም ቢሰጠውም አብዛኞችን የሚያግባባው ከተማ ብዙ ህዝብ በመሰረተ ልማት በተገነባ አካባቢ በአንድ ላይ የሚኖርበት ስፍራ ነው። በእንደዚህ አይነት ቦታ ላይ የህዝቡ አኗኗር ዘይቤ፣ ኢኮኖሚው፣ የአስተዳደር ስርዓቱ ለየት ይላል። ከገጠሩ አንጻር አነስ ያለ አካባቢ ቢሆንም የነገሮች ሁሉ መነሻና መድረሻ እንደመሆኑም የተለየ ትኩረት ይስባል።

ሳምንቱ የከተሞችም ነው ብለን ነው ስለከተሞች አንድ ነገር ማለት የፈለግነው፡፡ እስኪ መሪው ፓርቲ ኢህአዴግ ስለከተሞቻችን ምን ይላል፣ ምንስ አስቧል የሚለውን በወፍበረር እንዳስስ።

ከኢህአዴግ መሰረታዊ ፕሮግራም ቢታይ የገጠር ልማቱን የሚደግፉና ከገጠር ልማቱ ጋር የተያያዙ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች የሚሰሩባቸው ከተሞች በየእርከኑ እንዲቋቋሙ ማድረግ፣ ከተሞች የሚኖራቸው የመሰረተ ልማት አገልግሎት በአካባቢው ልማት ከሚጫወቱት ሚና ጋር የተያያዘ እንዲሆን ማድረግ፣ በከተሞች የሚኖረው የመሬትና የመሰረተ ልማት አቅርቦት ቅድሚያ በአካባቢው ለሚፈጠሩ የንግድና የምርት ተቋማት በሚሰጥ አኳኋን እንዲተዳደር ማድረግ፣ የከተማ ሊዝ ፖሊሲ አፈፃፀም ላይ ያሉ ችግሮችን በአፋጣኝ ማስወገድና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን፣ የከተማ የዕድገትና የማስተር ፕላን ዝግጅትና አፈፃፀሙን በሚመለከት ያለን ሙያዊ ብቃት እንዲዳብር ማድረግ ላይ የሚያተኩር ነው።

የቅርብ አመታት ሁኔታዎችን ለመዳሰስ ደግሞ በድርጅቱ ህገ ደንብ መሰረት የትልቁ ስልጣን ባለቤት የሆነው የድርጅቱ ጉባዔ ስለከተሞች ምን ግምገማ አለው፣ ለቀጣይ አመታትስ ምን አቅጣጫ አስቀምጧል? የሚለውን እንይ።

የድርጅቱ ጉባዔ በየሁለት አመት ተኩል ወይም በየሶስት አመቱ የሚካሄድ እንደመሆኑ፣ ዘንድሮ በወረሃ መስከረም ሃዋሳ ላይ የተካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ጉባዔ ከሶስት አመት በኋላ ነበር የተካሄደው።

ይህ ጉባዔ ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ በከተሞቸ ዙሪያ ሲሰሩ የነበሩ ስራዎችን በጥልቀት ገምግሞ ደካማና ጠንከራ ጎኑ ላይ መክሮ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። በዚሁ መሰረት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስታንዳርዶች 142 ከተሞች ተግባራዊ እየተደረጉ ቢሆንም የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ ባለመቻሉ ለኪራይ ሰብሳቢነት እና የመልካም አስተዳደር ጉድለት ተጋላጭነታቸው ሰፊ እንደነበረ ገምግሟል።

በከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት በተደረገ ጥረት በመደበኛ እና በመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር በተለይ ደግሞ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ የሚታየውን የአመለካከት እና የክህሎት ክፍተት ለመቅረፍ ጥረት ሲደረግ የቆየ ቢሆንም ካለው ሰፊ የለውጥ ፈላጊነትና የወጣቱ ጥያቄ አንፃር በቀጣይ ልዩ ትኩረት መስጠትን ይሻል