ከተማ በተለያዩ ምሁራን የተለያየ ትርጉም ቢሰጠውም አብዛኞችን የሚያግባባው ከተማ ብዙ ህዝብ በመሰረተ ልማት በተገነባ አካባቢ በአንድ ላይ የሚኖርበት ስፍራ ነው። በእንደዚህ አይነት ቦታ ላይ የህዝቡ አኗኗር ዘይቤ፣ ኢኮኖሚው፣ የአስተዳደር ስርዓቱ ለየት ይላል። ከገጠሩ አንጻር አነስ ያለ አካባቢ ቢሆንም የነገሮች ሁሉ መነሻና መድረሻ እንደመሆኑም የተለየ ትኩረት ይስባል።
ሳምንቱ የከተሞችም ነው ብለን ነው ስለከተሞች አንድ ነገር ማለት የፈለግነው፡፡ እስኪ መሪው ፓርቲ ኢህአዴግ ስለከተሞቻችን ምን ይላል፣ ምንስ አስቧል የሚለውን በወፍበረር እንዳስስ።
ከኢህአዴግ መሰረታዊ ፕሮግራም ቢታይ የገጠር ልማቱን የሚደግፉና ከገጠር ልማቱ ጋር የተያያዙ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች የሚሰሩባቸው ከተሞች በየእርከኑ እንዲቋቋሙ ማድረግ፣ ከተሞች የሚኖራቸው የመሰረተ ልማት አገልግሎት በአካባቢው ልማት ከሚጫወቱት ሚና ጋር የተያያዘ እንዲሆን ማድረግ፣ በከተሞች የሚኖረው የመሬትና የመሰረተ ልማት አቅርቦት ቅድሚያ በአካባቢው ለሚፈጠሩ የንግድና የምርት ተቋማት በሚሰጥ አኳኋን እንዲተዳደር ማድረግ፣ የከተማ ሊዝ ፖሊሲ አፈፃፀም ላይ ያሉ ችግሮችን በአፋጣኝ ማስወገድና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን፣ የከተማ የዕድገትና የማስተር ፕላን ዝግጅትና አፈፃፀሙን በሚመለከት ያለን ሙያዊ ብቃት እንዲዳብር ማድረግ ላይ የሚያተኩር ነው።
የቅርብ አመታት ሁኔታዎችን ለመዳሰስ ደግሞ በድርጅቱ ህገ ደንብ መሰረት የትልቁ ስልጣን ባለቤት የሆነው የድርጅቱ ጉባዔ ስለከተሞች ምን ግምገማ አለው፣ ለቀጣይ አመታትስ ምን አቅጣጫ አስቀምጧል? የሚለውን እንይ።
የድርጅቱ ጉባዔ በየሁለት አመት ተኩል ወይም በየሶስት አመቱ የሚካሄድ እንደመሆኑ፣ ዘንድሮ በወረሃ መስከረም ሃዋሳ ላይ የተካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ጉባዔ ከሶስት አመት በኋላ ነበር የተካሄደው።
ይህ ጉባዔ ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ በከተሞቸ ዙሪያ ሲሰሩ የነበሩ ስራዎችን በጥልቀት ገምግሞ ደካማና ጠንከራ ጎኑ ላይ መክሮ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። በዚሁ መሰረት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስታንዳርዶች በ142
ከተሞች ተግባራዊ እየተደረጉ ቢሆንም የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ ባለመቻሉ ለኪራይ ሰብሳቢነት እና የመልካም አስተዳደር ጉድለት ተጋላጭነታቸው ሰፊ እንደነበረ ገምግሟል።
በከተሞች
የስራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት በተደረገ ጥረት በመደበኛ እና በመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር በተለይ ደግሞ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ የሚታየውን የአመለካከት እና የክህሎት ክፍተት ለመቅረፍ ጥረት ሲደረግ የቆየ ቢሆንም ካለው ሰፊ የለውጥ ፈላጊነትና የወጣቱ ጥያቄ አንፃር በቀጣይ ልዩ ትኩረት መስጠትን ይሻል።
የከተሞች
የምግብ
ዋስትናና
የስራ ዕድል ፈጠራ በከተሞች ከድህነት ወለል በታች እየኖሩ ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ከምግብ ዋስትና እጦትና ተጋላጭነት ማላቀቅና በረዥም ጊዜ የኑሮ ሁኔታቸውን በማሻሻል ከድህነት እንዲወጡ እና የራሳቸው ስራ ፈጥረው ገቢ እንዲያገኙ ለማድረግ ፕሮግራም ተቀርጾና አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ በ2009
በጀት ዓመት ጀምሮ በፓይለት ደረጃ በ11 ከተሞች ወደ ትግበራ በመግባት ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ታይቷል፡፡
ማህበራዊ
ሴፍቲኔት
የቀጥታ
ድጋፍ አገልግሎት ተደራሽነትን ከማጠናከር አንፃር ባለፉት ዓመታት በከተሞች በሚከናወኑ በአረንጓዴ ልማት፣ በተቀናጀ የከተሞች ተፋሰስ፣ በደረቅ ቆሻሻ እና በግብርና ልማት ለ322,699 ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ370,343 ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥረዋል። እንዲሁም በተገኘው ሀብት ልክ 70,542 ዜጎች የቀጥታ ድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። የፕሮግራሙ አፈፃፀም አበረታች ሆኖ በመገኘቱ እና በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ፍላጎት ያለ በመሆኑ የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራምን በስፋት ለማከናወን እንዲቻል በቀጣይ ወደ ተጨማሪ ከተሞች በማስፋት ዜጎቻችንን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ተብሏል።
የከተማ
ፕላን ዝግጅትን በተመለከተ የከተሞች መሠረታዊ ካርታ፤ መሰረታዊ ፕላኖች፤ የከተሞች መዋቅራዊ ፕላን፤ የከተሞች ስትራቴጂክ ፕላን፤ የከተማ ዲዛይን፤ የሰፈር ልማት ፕላን በተለያዩ የአፈፃፀም ደረጃ ለማዘጋጀት ተችሏል።
የከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ የፀደቀውን ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ ከመፈፀም አንፃር የፖለቲካ አመራሩ ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል ባለመሆኑ ህገ-ወጥነትን በመከላከል ለልማቱ በቂ የለማ መሬት ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት እንዲሁም ለቤት ልማቱና ለመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አቅርቦቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጥሮ እንደነበረም ተገምግሟል።
የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ማሻሻል የከተማ መሬት ውስን ሀብት በመሆኑ እና ከፍተኛ የህገ ወጥ ወረራና የኪራይ ሰብሳቢነት ፍላጎት የሚንፀባረቅበት ዘርፍ እንደመሆኑ መጠን በሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ርብርብ እየተደረገባቸው ከሚገኙ ስራዎች አንዱ ነው። የባለፉት ሁለት አመታት ተኩል አፈፃፀም በከተሞች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል 60ሺ ሄክታር የለማ መሬት ለማዘጋጀት ታቅዶ 44 ሺ ሄክታር በላይ መሬት በማዘጋጀት 30 ሺ 466 ሄክታር መሬት ለተጠቃሚ ተላልፏል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንዱስትሪ ቦታ በማዘጋጀት 3 የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲከለሉ ማድረግ ተችሏል፡፡
በከተማ ማስፋፊያ አካባቢ ልማት ፕላን ትግበራ ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ አርሶ አደሮች ከአሁን በፊት በቂ ካሳ ሳያገኙ ከመሬታቸው የሚነሱበትን እና ለጉስቁልና የሚዳረጉበትን ሁኔታ በሚፈታ መልኩ የልማቱ ጉልህ ተጠቃሚ በማድረግ አኗኗራቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ ታቅዶ
የልማት
ተነሺ አርሶ አደሮችን ህይወት ለማሻሻል የሚያስችል ስትራቴጂ ሰነድና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡
በተጨማሪም የከተማ መሬትን ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ለማጽዳት ህጋዊ ካዳስተር በማልማት በትኩረት ሲሰራበት የነበረ ሲሆን ባለፉት ዓመታት በ14 ከተሞች የ42 ሺ 474 ይዞታዎችን ህጋዊነት በማረጋገጥ 32 ሺ 342 ይዞታዎችን በመመዝገብ ለዜጎች የይዞታ ማረጋገጫ መስጠት ተችሏል፡፡ ሆኖም ከዕቅዱ
አንፃር
በከፍተኛ
ደረጃ የዘገየ ስራ መሆኑን ነው ጉባዔ የገመገመው።
የከተማ የመኖሪያ ቤት ልማትን በተመለከተ የከተማ ነዋሪዎችን የቤት ችግር በማቃለል፣ በልማቱ አማካይነት በሚደረገው እንቅስቃሴ በከተሞች የሚታየውን የስራ አጥነት ችግር ለመቀነስ፣ የኀብረተሰቡን የቁጠባ ባህል ለማዳበር፣ የከተሞችን ገጽታ ለማሻሻል እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አቅም ለማሳደግ
በዘርፉ
ርብርብ
ሲደረግ
እንደነበረ
ተጠቅሷል።
በዚህም
መሰረት
የተቀናጀ
ቤቶች ልማት ኘሮግራም በመንግስት 125,000 ቤቶችን በ2ኛ የዕቅድ ትራንስፎርሜሽ ዘመን ለመጀመር በዕቅድ ተይዞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 61 ሺ 924 (49.5%) ቤቶች በመሰራት ላይ ሲሆኑ በሌሎች የኢንዱስትሪ ፓርክ በሚገነባባቸው ከተሞች ለመገንባት የታቀዱ ቤቶች በፋይናስ ዕጥረት ምክንያት እንዳልተጀመሩ።
በሌሎች
አማራጮች
በሕብረት
ስራ ማኀበራት 108 ሺ አራት ቤቶችን፣ በግለሰቦች 35 ሺ 566 ቤቶች፣ በሪልስቴት 12 ሺ 367 ቤቶችን መገንባታቸው ለጉባዔ የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል።
በአሁኑ
ወቅት በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ግንባታቸው የተጀመሩ ከ138 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በግንባታ ላይ የሚገኙ ሲሆን ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ባሳለፍናቸው ሶስት ዓመታት በ20/80 ፕሮግራም 40 ሺ 538 ቤቶችን እና በ40/60 ፕሮግራም 972 ቤቶችን ማስተላለፍ ተችሏል።
የከተሞች
የተቀናጀ
የመሠረተ
ልማት አቅርቦት በተመለከተ የከተሞች የመሠረተ ልማት አቅርቦት፣ አስተዳደርና የከተማ ንጽህና አገልግሎት ለማሻሻል የማህበራዊና የአካባቢያዊ ደህንነትን ማዕቀፍ መሠረት በማድረግ በከተሞች የተለያዩ የመሠረተ ልማቶችን ለመገንባት በታቀደው መሠረት በርካታ መሠረተ ልማቶች ተገንብተዋል።
የከተሞች የአረንጓዴ ልማትና ፅዳትን ከማሻሻል አንፃር የተመረጡ አዲስና ነባር አረንጓዴ ፓርኮች እንዲለሙ፣ የውሃ አካላትና ዳርቻ ቦታዎች በስታንዳርድና ዲዛይን እንዲጠበቁና እንዲለሙ እና የዘላቂ ማረፊያ ቦታዎች በስታንዳርድና ዲዛይን መሰረት እንዲለሙ ተደርጓል። እንዲሁም ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ሽፋን ለማሳደግ፣ ቆሻሻን በዓይነት ለይቶ መልሶ የመጠቀም እና የፋይናንስ ስርዓት በ41 ከተሞች ያለውን አደረጃጀት በመጠቀም ስርዓቱን ለመዘርጋት ጥረት ተደርጓል።
ጉባዔ ለቀጣይ አመታት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የመጣውን ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት በአግባቡ ለመያዝ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው የተሳለጠ ለማድረግ በፕላንና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ሁሉን አቀፍ የከተማ ልማት ፕሮግራሞች ትኩረት ተሰጥቷቸው ተግባራዊ እንዲደረጉ ነው አቅጣጫ ያሰቀመጠው፡፡
በከተሞች መካከል የተመጣጠነ እድገት እንዲኖር የክልል ተወዳዳሪ ከተሞችን የማጠናከር ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል ከተማዎቹን በመሰረተ ልማት ግንባታ የማጠናከርና ማንኛውም ዜጋ ያለስጋት ሰርቶ እራሱን መቀየር የሚችልባቸው ብዝሀነትን ማስተናገድ የሚችሉ ኢትዮጵያዊ ከተሞች መፍጠር ቁልፍ ጉዳይ ተደርጎ ይሰራበታል፡፡
የዜጎች መሰረታዊ ፍላጎት የሆነውን የመጠለያ ጥያቄ ለማሟላት በድርጅቱ የሚመራው መንግስት እስካሁን ከተጓዘባቸው አቅጣጫዎች በተለየ መልክ የመሬት እና የፋይናንስ አቅርቦቶችን ለማመቻቸት የሚሰራ ይሆናል፡፡ ከዚህም ባሻገር መንግስት በቀጥታ ተሳታፊ የሆነባቸውን የግንባታ እንቅስቃሴዎች ደረጃ በደረጃ በመቀነስ ራሱ ቤት ፈላጊው በማህበር ተደራጅቶ አቅሙን በማስተባበር የሚሰራበትን ሁኔታ የሚያመቻች ሲሆን እንደ ሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ሁሉ የውጪ ሃገር የሪል እስቴት ባለሃብቶች በዘርፉ የሚያደርጉት ተሳትፎ እንዲጎለብት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም የኢህአዴግ ጉባዔ ወስኗል፡፡
What are the advantages of a pay-to-earn casino with pay-to-earn
ReplyDeletePay-to-earn casino หาเงินออนไลน์ bonuses. One of the easiest things you can do in 메리트카지노 online casinos is find your favorite game. Pay-to-earn casino bonuses 1xbet allow you to