ሰላም
የሁሉ ነገር ዋስትና ነው፡፡ ሰርቶ የመለወጥ፣ ወልዶ የማሳደግ፣ ወጥቶ የመግባት፣ ዘርቶ የማፍራት በአጠቃላይ በሰው ልጆች የእለት
ተእለት ተግባር ውስጥ ከምንተነፍሰው አየር ያልተናነሰ ዋጋ አለው፡፡ ሰላም ከሌለ ነገ የለም፡፡ ስለነገ ማሰብም ማቀድም የሚቻለው
በሰላም ውስጥ ነው፡፡ ስለ ሰላም አስፈላጊነት በዚህች በተወሰነች ገፅ ዘርዝሮ መጨረሽ ፈፅሞ የማይቻል በመሆኑ ይህን ያነሳሁበትን
ጉዳይ ወደ ማብራራት ልሂድ፡፡
ውድ አንባብያን
ታሪክ እንደሚዘክረው አገራችን በበርካታ ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፋ ዛሬ በምናየው ተነፃፃሪ ሰላም፣ ልማትና እድገት ውስጥ የምትገኘው
አገር የማስተዳደር ኃላፊነት የተረከበው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት እና ህዝባችን የአገራችን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲሰፍን
በከፈሉት ዋጋ፤ ህዝባችን በተባበረ ክንድ ድህነትን በማስወገድ ላይ በመረባረባቸው ነው፡፡ ሁላችንም እንደምንገነዘበው ባለፉት
25 ዓመታት አገራችን የማሽቆልቆል ጉዞዋን ገትታ ፈጣንና አለም አቀፋዊ ዕውቀናን ባገኘ የእድገት ምህዋር ውስጥ ትገኛለች፡፡ ፈጣንና
ተከታታይ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማስመዝገብ አገራችን ተስፋ የሚጣልባት የብርሁ ተስፋ ተምሳሌት መሆንም ችላለች፡፡
በጥቅሉ
በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ድህነትን ለማስወገድ የሚደረገው ርብርብ
ዛሬም ከሰላምና ልማት ወዳዱ ህዝባችን ጋር በተባበር ክንድና በይቻላል መንፈስ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ይህ ነባራዊ ሁኔታ
እንደተጠበቀ ሆኖ ዛሬም ወደፊት ከመጓዝ አግደውና ጠፍንገው የያዙ ተግዳሮች ቀላል የሚባሉ አይደሉም፡፡ ኢህአዴግ ባለፉት 15 የተሃድሶ ዓመታት በልማት፣ በሰላም እና በዴሞክራሲ መስኮች የተመዘገቡ ለውጦችን በጥልቅ ተሃድሶ
ግምግማ በመለየትና እንቅፋት ያላቸውን በመለየት የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ትኩረት ስጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ በአገራችን የተፈጠረው አለመረጋጋትም ለቀጣይ ስኬታችን እንቅፋት የሚሆን በመሆኑ መቋጨት እንደሚገባው
በመደምደም ወደተግባር ከገባም ውሎ አድሯል፡፡
በአገራችን
ለዓመታት ተገንብቶ የቆየው ሰላማችን ላይ ጥላ ያጠላው ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ የታየው አለመረጋጋትና ግጭት ለዓመታት
በገነባናቸው ልማቶችና ሃብቶች ላይ ያነጣጠር ከኢትዮጵያዊነት ወግና ባህልም ጭምር ያፈነገጠ በመሆኑ ጉዳዩን ሰከን ብሎ በማየት
ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማስጠበቅና ከድህነት ጋር የምናደረግ ትግል ላይ እንቅፋት ሆኖ እንዳይቀጥል ብሎም የሁሉ ነገራችን
መሰረት የሆነውን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ መገንባት ስለሚገባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ግድ ሆኖ በመገኘቱ የአስቸኳይ ጊዜ
አዋጅ እንዲታወጅ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግ ወትሮም ቢሆን ለህዝብ ያለውን ውግንና በተጨባጭ ማስመስከር የቻለ ከህዝብ አብራክ ወጥቶ
ለህዝብ ጥቅም መከበር ዋጋ የከፈለ ድርጅት ለመሆኑ የአገራችን ህዝቦች ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ ዛሬም እያደረገ ያለው ይህኑን
ነው፡፡
ምንም
እንኳን ባለፉት ዓመታት በመጣንባቸው መንገዶች የህዝብ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም እኩይ ተግባር ውስጥ የነበሩ አመራሮች
ቢኖሩም ኢህአዴግ እንደ ድርጅት ከዚህ መሰረታዊ ክፍተት የፀዳ በመሆኑ ጉዳዩን በጥልቀት በመታደስ ንቅናቄ ውስጥ በማየት ከህዝብ
ጥቅም አኳያ እየተመዘን መፍትሄ እንዲቀመጥላቸው ቀጣይ ስራዎችም በጥቅብ ዲስፕሊን እንዲሰሩ የማያወላዳ እርምጃ በመውሰድ ላይ
ይገኛል፡፡ ኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት እንደ አገር ተጋርጦ የነበረውን አደጋም እየፈታበት ያለው መንገድ
ለሰላም ካለው ቁርጠኝነት፤ ለህዝብ ካለው ውግንና በመነሳት መሆኑን መረዳት የሚያስፈልግ ይሆናል፡፡
ውድ አንባብያን
መስከረም 28 ቀን 2009 ዓም በአገራችን ለስድስት ወራት የሚቆይ አዋጅ ታውጆ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የህገመንግስቱ አንቀፅ
93 እንደሚገልፀው በአገራችን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ አንድም ወረራ ሲያግጥም፣ ወይም ህገ መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥል
ሁኔታ ሲፈጠር በሌላ በኩል ደግሞ የተፈጥሮ አደጋና የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲያጋጥም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጃል፡፡
በአገራችን የተደነገገው አዋጅም መነሻ ከእነዚህ መካከል በግልፅ የተቀመጠው ህገ መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ በመፈጠሩና
ይህንንም በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት መፈፀም ሳይቻል በመቅረቱ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
በተለያዩ
ድረ ገፆችና ማህበራዊ ሚዲያዎች እንደሚነበበውና አንዳንድ አፍራሽ ሃይሎች እንደሚያናፍሱት አዋጁ ህግና ስርዓት ባልተከተለ መልኩ
አልያም መብትን በሚጋፋ መልኩ የተተገበረ ሳይሆን ህገ- መንግስታዊ መሰረት ያለውና ዓለም አቀም ተሞክሮም ጭምር ያለው መሆኑን መገንዝብ
ግድ የሚል ይሆናል፡፡ በህገ መንግስቱ መሰረትም አዋጁን የመደንገግ ስልጣን ያለው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ
በዚህ መንፈስ ምክር ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አዋጁን የማፅደቅ ስራ ሰርቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም አዋጁ የ6 ወር ጊዜው ከተጠናቀቀም
በኋላ ህዝባችን ሰላሙ በአስተማማኝ ሁኔታ እስኪገነባ ድረስ አዋጁ መቀጠል እንደሚገባው በመግለፁ ብሎም በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች
የሚታዩ ግጭቶች በመኖራቸው ምክር ቤቱ አዋጁን ለተጫማሪ 4 ወራት እንዲራዘም ደንግጓል፡፡
አዋጁ
አስቀድሞ መታወጁም ይሁን እንዲራዘም መደረጉ በቅን ልቦን ፋይዳው ለማን ብሎ ለመረመረ ቀላል መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ አዋጁ ለሰላማችን
ከሆነ ሰላማችን ለእኛ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ መሰረት በመሆኑ ህፃን ከአዋቂ በሰላም ውስጥ ካልሆነ አንድም እርምጃ መጓዝ ስለማይቻለው
አዋጁ ለሁሉም ሰላማዊ ዜጋ የላቀ ፋይዳ እንዳለው መገንዘብ ይገባል፡፡
ውድ አንባብያን
ላለፉት ዓመታት በአገራችን የተመዘገቡት የሚያጓጉና በተስፋ የመሰጡ ለውጦች በተጀመረው ልክ ተጠናክረው መቀጠል እነደሚገባው እሙን
ነው፡፡ ለዚህ ፈተና የሆኑ ተግዳሮቶች ሁሉ በህይወታችን ላይ የተጋረጡና በመለወጣችን ላይ የመጡ በመሆናቸው መነቀል የሚገባቸው ይሆናል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ህግ መንግስቱን ለመጠበቅ፣ የዜጎች ሁለንተናዊ መብቶች ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከልና ሰላማዊ ወደሆነ
ሁኔታ ለመለወጥ በመሆኑ ይህን አጀንዳ ለማብጠልጠል የሚራወጡ አካላት ራሳቸውን ትዝብት ውስጥ ከመክተት የዘለለ ትርፍ እንደማያገኙ
እሙን ነው፡፡
በርካታ
የዓለማችን አገራት ሰለጠኑ የምንላቸውን ጨምሮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ አልፈዋል አሁንም አገራቸውን ለመጠበቅ በአስቸኳይ ጊዜ
አዋጅ ውስጥ ያሉ አገራት እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ዓላማው አንድም ከፈተጥሮ አደጋ አልያም ከሰው ሰራሽ አደጋ አገርን ለመጠበቅ አስገዳጅ
ሁኔታ ውስጥ ሲገባ የሚደነገግ ነውና በዚህ መንፈስ በመረዳት ሁሉም ዜጋ እንደጀመረው ሁሉም ሰላሙን በመጠበቅ የሚያጠፋውንም በሰከን
አዕምሮ እንዲያስብ በመገሰፅ በቀጣይ ሩቅ ለመድረስ የያዝነውን እቅድ ለማሳከት መሰረት ለሆነን ሰላማችን ዘብ እንቁም፡፡ ሰላም በዋጋ
አይተመንም፡፡ ሰላም ከምንተነፍሰው አየር ያልተናነሰ ዋጋ አላትና ለሰላማችን እንትጋ፡፡ ሰላም፡፡
No comments:
Post a Comment