EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Wednesday, 20 February 2019

የአባገዳዎችና ሃደ ሲቄ የእርቅ ጉዞ መጨረሻው ያጓጓል


(አቡ ኮ)

በአገሪቱ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከህዝቡ ገፍቶ የመጣው ለውጥ ጋር ለመራመድ የአመራር ለውጥ አድርጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በርካታ ብሔራዊ መግባባትን የሚያጠናክሩ እርቅና መቀራረብ ላይ ያተኮሩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

ከነዚህም መካከል በአገር ቤት በተለያየ ምክንያት በማረሚያ ቤቶች የነበሩ የነበሩ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ማድረግና ከአገር ውጭ ሆነው ሲታገሉ የነበሩ ሲንቀሳቀቁ የነበሩየፖሊቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት መጥተው በሰላማዊ መንግድ እንዲታገሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበዓለ ሲመታቸው ካደረጉት ንግግር ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ይህንን ጥሪ ተቀብለው ሁሉም ስለኢትዮጵያ ብለው የተደራጀ የፖሊቲካ ድርጅቶች እናት አገራቸው ተመልሰዋል። ከነዚህም መካከል  የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር /ኦነግ/ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ሂደት  በርካታ ኢትዮጵያዊያን በአደባባዮች ወጥተው ደስታቸውን እንዲገልጹ አስችሎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን የኋላ ኋላ በምዕራብና  መደቡብ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ታጥቆ የሚንቀሳቀሱ አካላት በመኖራቸው ግጭቶችና የሰላም መታወኮች ተከስቶ ቆይቷል። ይሄው ድርጊትም የአገሪቱ ዜጎች ዘንድ የእርቅና የመተባበር፤ ተደመሮ ለጋራ እድገት የሚሰራበት ወቅት ነው የተባለበት ጊዜ ላይ መሰል አለመረጋጋቶች መፈጠራቸው ግራ የሚያጋባ ስሜት መፍጠሩ አልቀረም።

ያኔ ነበር ጉዳዩ ያሳሰባቸው የኦሮሞ አባገዳዎችና ሃደ ሲቄዎች፣ እውቅ ፖለቲከኞች፣ አክቲቭስቶችና ገለልተኛ የሆነ ልሂቃንን ይዞ ለሰላም የኦነግና የክልሉን መንግስት ደጅ መጥናትን የተያያዙት። በዚህም ሁለቱ አካላት ወደ ሰላማዊ ትግል የሚደረግ ጉዞ ላይ ያጋጠመው ችግር ዙሪያ ‹‹እኛ እናሸማግላችሁ፤ የህዝቡም የደስታ ጭላንጭል ሙሉዕ ይሁን ኑ ሁሉንም እኔ ፈታለው›› ብሎ መንግስትንም ኦነግንም ጠየቀ።

ጥያቄያቸውም በሁለቱም ሰላም ፈላጊ ወገን ተቀባይነት አግኝቶ በአባገዳዎች የሚመራ ቴክኒካል ኮሚቴ ተቋቋሞ ወደ ስራ ከተገባም  ወር አለፈው። ኮሚቴው የመጀመሪያ ስራው ያደረገውም በአምቦ ትልቅ የእርቅ ጉባዔ ተጠርቶ ኮርማ ታርዶ በኦሮሞ ህዝብ ባህል መሰረት እርቅ መውረዱን ማብሰር ነበር።  በመቀጠልም የኦነግን ታጣቂዎች ትጥቃቸውን  በክብር ለአባገዳዎች አስረክቦ ወደ ተዘጋጁ ካምፖች ገብቶ ተገቢውን ስልጠና በመውሰድም ወደ ቀጣዩ ሰላማዊ የህይወት ምዕራፍ እንደሚሸጋገርም ተወሰነ።



ይህንኑ ውሳኔ እውን ለማድረግም በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ቀናት ላይ የቴክኒክ ኮሚቴው ለሁለት ተከፍሎ ወደ ምስራቅ ጉጂና ወለጋ ያቀናው። ዛሬ ላይ ደግሞ የሚሰማው ዜና መልካም ነው። ያልተመለሰ ጥያቄ አለ  ብሎ ቤቱን ዱርና ጫካ ያደረገው ወታደር የአባቶች ጥሪ ሰምቶ ትጥቁን ፈቶ ለአባቶች እያስረከበ ወደ ተዘጋጀለት ጊዜያዊ ካምፕ ሲገባም እየተመለከትን ነው።

ይህ  በእጅጉ የሚያስደስት የአገሪቱንና በተለይም በቀጥታ ሰላማቻው እየታወከ ለነበረ ዜጎች መጪን ጊዜ  ተስፋ ሰጪና ብሩህ የሚያደርግ ተግባር ነው። ይህ ክስተት እኛ ኢትዮጵያን የውስጥ ችግራችን በራሳችን ባህልና አገባብ የመፍታት የካበተ አቅም እንዳለን በተግባር ያሳየ ሆናል፤ ባህላዊው የገዳ ስርዓታችን በዛሬዋ ኢትዮጵያ ደማቅ አሻራውን እያሳረፈ መሆኑን በተግባር አይተናል፤  ትጥቅ አስፈትቶ ለሰላም የሚያንበረክክ አኩሪ ባህል እንዳለን ለዓለም አሳይተናል። አሁንም አንተም ተው አንችም ተይ ብሎ እርጥብ ሳር ብቻ ይዞ ትጥቅ  ጭምር ለሚያሰፈቱ እናቶቻችን መታዘዝ ዛሬም ከኛ ጋር የሚያስብል ተግባር ነው።

No comments:

Post a Comment