EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Wednesday, 8 March 2017

የደመወዝ ስኬል ማስተካከያውን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ

የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ስኬል ማስተካከያን በተመለከተ በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር በጋራ የተሰጠ ማብራሪያ
የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የሚባለው ደመወዝን ከገበያ ጋር ለማቀራረብ የመንግስትን የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ ማሻሻያ ነው። የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ሲደረግ ቀድሞ ማስተካከያ የተደረገባቸውን ወይም የተሻለ ክፍያ የሚያገኙ ሠራተኞችን አይመለከትም። የኑሮ ውድነት ማካካሻ የሚባለው ደግሞ ወቅታዊ የገበያ ሁኔታ በሰራተኛው ኑሮ ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቅረፍ የመንግስትን የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ የኑሮ ውድነት ማካካሻ ነው። የደመወዝ ስኬል ማስተካከያም ሆነ የኑሮ ውድነት ማካካሻ ያለፉት 10 ዓመታት ተሞክሮ የሚያሳየው በአማካይ በየሦስት ዓመቱ መደረጉን ነው።

በሌላ በኩል የደመወዝ ጭማሪ ከመደበኛ የውጤት ተኮር ምዘና ውጤት ላይ ተመሥርቶ ለአንድ ሰራተኛ ከተመደበበት የሥራ ደረጃ የጣሪያ ደመወዝ ሳያልፍ የሚደረግ መደበኛ የእርከን ደመወዝ ጭማሪ ነው። በዚህም ሠራተኛው ከነበረበት የመነሻ ወይም የእርከን ደመወዝ ወደ ቀጣዩ የእርከን ደመወዝ ላይ እንዲያርፍ የሚደረግበት አሰራር ነው።
በሐምሌ 2008 ለመምህራን የፀደቀው ማሻሻያ የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ነው። በተመሳሳይ በጥር ወር 2009 .. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመንግስት ሰራተኞች የፀደቀውም የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ነው። ሁለቱም የደመወዝ ጭማሪ አይደሉም።
እንደተገለፀው ከስድስት ወራት በፊት ማለትም በያዝነው በጀት ዓመት መጀመሪያ የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የተደረገላቸው ተቋማት አሉ። እነዚህም ዳኞች፣ ዐቃብያነ ህግ፣ መምህራንና የአካዳሚ ሠራተኞች እና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ናቸው፡፡ ከአገሪቱ ኢኮኖሚና የመክፈል አቅም ጋር እንዲሁም ከአሰራር አኳያ የስኬል ማስተካከያ በየመንፈቅ አመቱ ሊካሄድ የሚችል ባለመሆኑ እነዚህ ተቋማት በአሁኑ ስኬል ማስተካከያ አልተካተቱም፡፡
በተመሳሳይ ቀድሞውንም የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የተደረገላቸውና በልዩ ስኬል የዓላማ ፈፃሚዎች ደመወዝ ስኬል እየተስተናገዱ የነበሩና በአንፃራዊ መልኩ በተለያዩ ጊዜያት ከሌላው የመንግሥት ሠራተኛ ከፍ ያለ የደመወዝ ስኬል ተፈቅዶላቸው የነበሩ 33 ተቋማትም በአሁኑ ማስተካከያ አልተካተቱም። (ዝርዝራቸው ከግርጌ ቀርቧል፡፡)
ስለሆነም ይህ የአሁኑ የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የሚመለከተው ከተጠቀሱት ውጪ ያሉትን በፌዴራልና በክልል ያሉ በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የፖሊስና መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የሕዝብ ተመራጮችንና ተሿሚዎችን ነው። ይህም በተሟላ ጥናት ላይ የተመሠረተና የመንግሥትንም የመክፈል አቅም ያገናዘበ በመሆኑ ፍትሃዊ ነው።
የአሁን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ዝቅተኛ ደመወዝ 582 ብር የነበረውን መነሻ ደመወዝ ወደ 860 ስኬሉን ከፍ የሚያደርግ እና መድረሻ ጣሪያውን 1,439 ብር የሚያደርግ ነው።  ከፍተኛ ደመወዝ ፕሣ - 9 ሲሆን 5,781 ብር የነበረው መነሻው ወደ 7,647 በማሳደግ እና ጣሪያውን 10,946 በማድረግ ስኬሉ ተሻሽሏል።
አሁን የተደረገውን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ በተመለከተ ያለው ሁኔታ ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የፐብሊክ ሰርቫንቱን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያን እንደ ደመወዝ ጭማሪ በመውሰድ በቅርቡ ማስተካከያ የተደረገላቸውን መምህራንንም ይመለከታል በሚል የሚራመደው ሀሳብ የተሳሳተ መሆኑን መረዳትና ትክክለኛውን ሁኔታ መገንዘብ ያስፈልጋል።
የመምህራን ደመወዝ ስኬል ማስተካከያ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ሐምሌ 2008 . ላይ ሲደረግ መምህራን የሰው ኃይልን የመቅረፅ ትልቅ ተልዕኮ ያላቸው በመሆኑ የተለየ ትኩረት በመስጠት ነው። አሁን ለሌሎች ተቋማት የተደረገው የደመወዝ ስኬል ማስተካከያም ቢሆን ከመምህራን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት ያለው ነው። ይህንንም የተወሰኑ አብነቶችን በማንሳት ማየት ይቻላል፡፡
1)  መሰናዶ /ቤት 2 ድግሪ ያለው ጀማሪ መምህር 4,269 ብር ሲሆን 2 ዲግሪ ያለው ጀማሪ ሠራተኛ በሌሎች ተቋማት 3,137 ብር ነው።  ይህ ሰባት ዕርከን ልዩነት ያለው ነው።  እንዲሁም ከፍተኛ መሪ ርዕሰ መምህር 12,112 ብር የሚከፈለው ሲሆን በሌሎች መንግሥት ተቋማት ያለው መካከለኛ አመራር [ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወዘተ] 7,647 ብር ይከፈለዋል።  ይህ ከአሥር እርከን በላይ ልዩነት ነው።
2)  በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ዲግሪ በመምህርነት የተቀጠረ 4,662 ብር በሌሎች የመንግሥት ተቋማት 2,748 ብር ይከፈለዋል።  ይህ 12 (አሥራ ሁለት) እርከን ልዩነት ያለው ነው።  በዚሁ መስክ ከፍተኛ መሪ መምህር III 11,720 ሲከፈለው በመንግሥት ተቋማት ያለ መካከለኛ አመራር [ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወዘተ] 7,647 ብር ይከፈለዋል።  ይህ ደግሞ ከአሥር እርከን በላይ ነው።
3)  በመጀመሪያ ዲግሪ ቴክኒካል ድሮዊንግ መምህር 4,085 ብር ሲከፈለው በሌሎች ተቋማት ያለው ግን 2,748 ብር ይከፈለዋል።  ይህ ደግሞ የዘጠኝ እርከን ልዩነት ያለው ነው።  በተመሳሳይ ዘርፍ ከፍተኛ መምህር 10,567 ብር ሲሆን በሌሎች ተቋማት 7,647 ብር ነው።  ይህ የዘጠኝ እርከን ልዩነት ነው።
4)  9-10 ክፍል ጀማሪ መምህር 3,137 ብር ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪ በሌሎች ተቋማት ጀማሪ 2,748 ብር ነው። ይህም የሦስት እርከን ልዩነት ያለው ነው።  የከፍተኛ መሪ መምህር 8,539 ሲሆን በሌሎች ተቋማት መካከለኛ አመራር [ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወዘተ] ደመወዝ ግን 7,647 ነው።
5)  1-8 ክፍል ጀማሪ የዲፕሎማ መምህር 2,404 ብር ሲሆን በሌሎች ተቋማት 2,100 ብር ነው።  ይህም የሦስት እርከን ልዩነት ያለው ነው።
6)  የሰርተፍኬት መምህራን ጀማሪ መምህር 1,828 ብር ሲሆን በሌሎች ተቋማት 1,370 ብር ነው።  ይህ የስድስት እርከን ልዩነት ያለው ነው።
ስለሆነም በአጠቃላይ ሲታይ መንግሥት ለመምህራን የተለየ ትኩረት እንደሰጠና ይህም ተገቢ መሆኑን ማየት ይቻላል። በቀጣይነትም በተለይ የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርትና መሰል ድጋፎች በሁሉም አካባቢዎች አቅም በፈቀደ መጠን ደረጃ በደረጃ እየተሟሉ መሄድ ይኖርባቸዋል። ከዚህ አኳያ የተጀመሩ ሥራዎችም አበረታች ናቸው። በዚህ አጋጣሚ መላ መምህራን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት የምታደርጉትን ትጋት በማጠናከር በሀገራችን የሕዳሴ ጉዞ ላይ አሻራችሁን ለማሳረፍ እንድትረባረቡ ጥሪ እናቀርባለን።
በተለያዩ ጊዜያት ከሌላው የመንግሥት ሠራተኛ ከፍ ያለ የደመወዝ ስኬል ተፈቅዶላቸው የነበሩ
1.  የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት ተመራማሪዎች
2.  ብሔራዊ ኘላን ኮሚሽን
3.  የፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል
4.  የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን
5.  የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር
6.  ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
7.  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8.  የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት
9.  የብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዮት የተመራማሪዎች
10.   ብሔራዊ  የአፈር ምርምር ላቦራቶሪ
11.   ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ምርምር ማዕከል ተመራማሪዎች
12.   የመንገድ ትራንስፖርት  ባለስልጣን
13.   የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር
14.   የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን
15.   የደን ምርምር ኢንስቲትዮት
16.   የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዮት
17.   የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር
18.   የቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን
19.   የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት
20.   የከተሞች የሥራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ
21.   የታላቁ የኢትጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት
22.   ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት
23.   ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
24.   ከፍተኛ ፍርድ ቤት
25.   የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
26.   የተቀናጀ መሠረተ ልማት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ
27.   የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዮት
28.   የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
29.   የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኘሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዮት
30.   የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ
31.   የኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት
32.   የፋይናንስ ደህንንት መረጃ ማዕከል
33.   ብሔራዊ መረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስቴር

8 comments:

 1. መምህርነት ትውልድ የሚታነጽበት ታላቅ ሙያ ነው፡፡ አንድ ሀገር የወደፊት እጣ ፈንታዋን ለመወሰን መጀመሪያ መስራት ያለባት መምህራኖች ላይ ነው፡፡ የብዙ የአደጉ ሀገሮች ተሞክሮም የሚያሰየው ይህንኑ ሀቅ ነው፡፡ በትምህርት ሴክተሩ የደከመ ሀገር ሌሎች ሴክተሮቹም የበለጠ ደካማ እንደሚሆኑ በዘርፉ የተሰሩ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ምክናየቱም ዶክተሩም ሆነ ኢንጅነሩ የመምህሩ ውጤቶች ናቸው፡፡ “Teaching creates all other professions” እንድሚባልው፡፡ በብዙ ሀገሮችም መምህራን ከፍተኛ ክብርና ዝና አላቸው፡፡ So,I would like to thanks all of the concerned body for the consideration, but there is a little bit problem even now. Teachers are only waiting for this monthly salary, but others may not. So, please, here my advice for both teachers and governments.
  1. Most of us we criticize things as per our individual speculation, which is not ethical as scholar. So, please try to come up with ultimate solution if you have.
  2. Sheltering issue is the great problem nowadays, so, governments should be work hard on this.
  3. መምህር ማንበብ፣ መመራመር የራሱን እውቀት ማሰደግ አለበት፡፡ ለለት ኑሮው ሳያስብ በድንብ ተዘጋጅቶ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆነውን ትውለድ መቅረጽ ነበር ያለበት፡፡ ነገር ግን ዛሬ የምናየው ሌላ ነው፡፡ Most of the teachers are running here and there, specially these higher educations to overcome the high rocketing everything on the market. I am in doubt wether they ready and give what is expect from for students. So, this may be harm our education quality. So, we all are obliged to focus on the future consequence not on daily life of the individual. since "Teacher is like a candle — it consumes itself to light the way for others!"

  May if I wrote something wrong please correct me, it is not time to criticize everything, rather making our effort to correct.

  4. ድል እና ድምቀት ለኢትዮጽያ ህዝብ

  ReplyDelete
  Replies
  1. First of all, I wuold like to thank you for this article. But, there are some essential defects or errors in the english part of your article. Quality and precision are very impotrtant in school teaching.Because,
   teachers are preparing new generations for the 21st century world class work forces.

   Delete
  2. First of all, I wuold like to thank you for this article. But, there are some essential defects or errors in the english part of your article. Quality and precision are very impotrtant in school teaching.Because,
   teachers are preparing new generations for the 21st century world class work forces.

   Delete
  3. First of all, I wuold like to thank you for this article. But, there are some essential defects or errors in the english part of your article. Quality and precision are very impotrtant in school teaching.Because,
   teachers are preparing new generations for the 21st century world class work forces.

   Delete
 2. በመመሪያ አተረጓጎም ችግርና የአፈፃፀም ችግር ምክንያት እስካሁን የደመወዝ እስኬል ማሻሻያ ተጠቃሚ ያልሆን መምህራን አለን፣ ምናልባት ከዚህ ማብራሪያ በሁዋላ እንደገና ዘወር ብለው በማሰብ ያገዱብንን የደመወዝ ማሻሻያ እንደሚያነሱልን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ (ዉቅሮ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ የትግራይ ክልል ቴ.ሙ.ት.ስ ቢሮ፣ የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ)

  ReplyDelete
 3. https://www.youtube.com/watch?v=MRPRJUTPLnU

  ReplyDelete
 4. Enter your comment...If anybody cares out there will you explain the fact that a university lecture with 10 years of experience is paid a similar amount of 10400 birr salary with a fresh lecture with zero years of experience. How in the world a person with mind decide to put up such scales ....I always needed an answer from EPRDF people but everybody refers me it is being handled by the superiors...I need Eprdfs answet

  ReplyDelete

 5. አንድ የግብርና የልማት ጣቢያ ሰራተኛ በሌላ ክልል ከ4 ዓመት በላይ
  የስራ አገልግሎት እያለው በግል ችግር ምክንያት በዜሮ የስራ ልምድ
  ተቀጥሮ እያገለገለ ይገኛል።
  በሌላ ክልል የነበረው ለደሞዝ ለማሻል ሊጠቅመው አልቻለም
  አዲሡ መመሪያ(jeg) ሊረዳው ይቺላል? ወይስ?
  አንድ በሉት ????????

  ReplyDelete