በአለም ላይ ህብረት፣ አንድነት፣ ትብብርና የሚሳሰሉት መሰባሰብን የሚያወሱ ቃላቶች ይዘወተራሉ። የተባበሩት መንግስታት፣
የአፍሪካ አንድነት፣ የተባበሩት የአሜሪካ ግዛቶች ወይም USA፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የተባበሩ አረብ እምሬቶች ውይም UAE ለአብነት
መጥቀስ ይቻላል።
እነዚህ አጠራሮች ቃላቶቹ ስለሚያምሩ ብቻ የመጡ አይደሉም ለአመታት ተጸንሶ ምጡ በራሱ ተጨማሪ አመታትን ፈጅቶ የተወለዱ
ናቸው። ዛሬ ሃያል የምትባለው አገረ አሜሪካ የመሰባሰብ ውጤት ናት። በተጽኖ ፈጣሪነቱ የሚጠቀሰው የአውሮፓ አገራት ህብረት የመሰባሰብ
ውጤት ነው። የአለምን አገራት በአንድ የሚያሰባስበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም እንዲሁ።
ምክንያቱም ግልጽ ነው ‘’አንድነት ወይም መሰባሰብ ሃይል ስለሆነ ድር በያብር አንበሳ ያስር እንደሚባለው አንድ ሆነ
ብቻህን መስራት የሚትችለው ነገር በላይ ተባብሮ የሚተሰራው ነገር ይልቃል። እንደዚህ አይነት ትብብሮች አብሮ የመግዘፍ ጉዳይ ግን
ወደ አፍሪካ አገራት ሲመጣ ያን ያህል ጎልቶ አይታይም። በስንትና ስንት ጥረት ከተቋቋመው የአፍሪካ ህብረት ጀምሮ ተጽኖ ፈጣሪነቱ
አጠያያቂ ነው። አብዛኛው የአንድ ቀጠና አገራት ወይም ጎረቤት አገራት መካከልም ተባብሮ ያለውን አዋጥቶ ትልቅ ከመሆን ይልቅ ሽኩቻ
ይበዛል።
ይሄ ነገር ግን ቆየ ወይም አልተሳካም ተብሎ የሚታው ነገር ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች ይደረጋሉ ለዚህም በአፍሪካ ህብረት
አጀንዳ 6023 ላይ የተቀመጠውን አገራትን የማስተሳሰር ግብ የተቀመጠው። ከዚያም ቀደም ተብሎ የተሞከሩና የተወሰኑ ውጤቶችንም ያስመዘገቡ
የደቡብ አፍሪካ አገራት የልማት ትብብር SADEC የምዕራብ አፍሪካ ECOWAS እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካውን IGAD መጥቀስ ይቻላል።
አሁንም ግን ገና ብዙ ስራ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት በመደመር ፍልስፍናቸው ከአገራዊ አንድነት አልፎ ቀጠናዊ አንድነትን
የሚያቀነቅን የጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ አህመድ ራዕይ ይህንኑ እውን ለማድረግ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መካከል ይጠቀሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እንደሚታወቀው ወደ ስልጣን ከመምጣቸው ቀዳሚ ስራቸው ካደረጉት ተግባራት መካከል ኢትዮጵያ
ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ያላትን ለሁለት አስርት አመታት የተቋረጠውን ግንኙነት፤ ሁለት ወንድማማች ህዝብ መካከል መኖር የነበረበትን
ሰላማዊ ግንኙነት ወደ ቦታ መመለስ ነበር። ሁለቱ አገራት ማካከል ተዘገቶ የነበሩትን ድንበሮች ከፋፍቶ ህዝቡ በየብስም ይሁን በአየር
ትራንስፖርት ተጉዞ እንዲገናኝ አድርገዋል።
በዚህ ተግባራቸው ከሁለቱ አገራት ህዝብ አልፎ በአለም ዙሪያ ካለው ህዝብ አድናቆት ተችረዋቸዋል፤ እውቅንም አግኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አላማቸው ሁለቱ አገራት መካከል ሰላም አንዲወረድ
ማድረግ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የቀጠናው አገራት ተደምሮ በጋራ እንዲያድጉ ማድረግም እንደሆነ ሲናገሩ ተደመጡ። ተናግሮ ብቻም አላቆሙም
በኤርትራና ጂቡቲ መካከል የነበረው የድንበር አከለካባቢ ግጭት አብቅቶ ሰላም እንዲወርድ ማደራደር ጀመሩ።
በሶማሊያና ኤርትራ መካከል የነበረውም ግንኝነት እንዲሁ ተሻሽሎ ወደ መተባበር እንዲሸጋገር ጥረት ማድረግ ጀምሩ፣ በዚህም
እሳቸውን ጨምሮ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች በተገኙበት የሶስትዮሽ ትብብር ማዕቀፍ አስመራ ላይ ተፈረመ።
በዚያም አላቆሙም በትናንትናው እለትም የኬኒያውን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያትን ይዞ አስመራ ላይ ከተሙ፤ የሶስትዮሽ ግንኙነትና
ትብብር ዙሪያም ምክክር አደረጉ።
ዛሬም የሀገረ ኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ይዞ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ተጉዘው የሶስትዮሽ ምክክር እንደሚያደረጉ ነው የሚጠበቀው። ታዲያ የነዚህ
ሁሉ ጥረቶች ዋናው ግቡ በምስርቅ አፍሪካ ቀጠና አገራት መካከል ትስስር በመፍጠር፤ ያላቸውን ተጋርቶ እንዲያድጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
ነው።
ይህንንም አካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ መደመር ብሎ ይጠሩታል፤ ማለትም ያለቸውን ደማመሮ ወይም አንድ ላይ
አድርጎ አንድ ትልቅ አቅም መፍጠር ማለት ነው። ይህ ደግሞ እውን የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም መሰል ትብብሮች በአለም ዙሪያ
ቅድም የጠራውላቸውን ሃያልና ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም ያለችው፣ ህዝቦቻቸው ከራሳቸው ተርፎ ሌሎችን የሚረዱ አገራት መፍጠር ችለዋልና።
ወሳኙ ነገር ግን መንግስታትና ህዝቦቻቸውም መደመር የታላቅነት፣ የሃያልነትና የብልጽግና መሰረት መሆኑን ተገንዝቦ አብሮ
ተባበሮ ለማደግ ልባቸውንና በራቸውን ክፍት ማደረግ ነው።
ያ ሲሆን ቀጠናው ከጦርነት፣ ሽኩቻና ከሽብር ነጻ ወጥቶ ታሪኩ ተለውጦ ዜጎች እንደልባቸው ተዘዋውሮ የሚሰሩበት፤ በአንድ
አገር ያለው ወደብ ለሁሉም የሚሆንበት፤ በአንድ አገር ያለው ምርት ሁሉም አገር የሚሸጥበትና ሁሉም ያለውን ሽጦ ያልየለውን የሚገዛበት
ትልቅ ገቢያ ይፈጠራል። ያኔ የጠቅላይ ሚኒስትር ተባብሮ ትልቅ የመሆን ራዕይ እውን ይሆናል።
እኛም እንላለን ዛሬውኑ ለበጎ ነገር መተባበር እንጀምር።
No comments:
Post a Comment