በአሜሳይ ከነዓን
አገራችን
ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መናኽሪያ፣ የኃይማኖት ብዝሃነት ያለባት፣ የየራሳቸው ቋንቋ፣ ባህል፣ ስነልቦናና
መልክዓ ምድራዊ አሰፋፈር ያላቸው ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባለቤት የሆነች አገር ናት። በአገራችን ታሪክ ያለፉት መንግስታት
ብዝሃነትን የማይቀበሉ በመሆናቸውና ብዝሃነትን ማስተናገድ የሚችል ስርዓት መገንባት ባለመቻላቸው አገራችንና ህዝቦቿን ለከፋ ችግር
ዳርገዋቸዋል፡፡ በአገራችን የፌዴራሊዝም ስርዓት እውን ከመሆኑ አስቀድሞ የነበሩት መንግስታት በኃይማኖትም ይሁን በቋንቋና ባህል
የሚገለፁ ብዝሃነቶችን እንደ ስጋት ይቆጥሩ የነበሩ በመሆናቸው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማፈን
አስከፊ ጭቆና አድርሰውባቸዋል
አገራችን ካላት ተጨባጭ ሁኔታ ብዝሃነትን በሃይል የመጫን አማራጭ የጥፋት መንገድ ከመሆኑ ያለፈ ፋይዳ እንደሌለው በተግባር ተረጋግጧል፡፡ የነበረው የአሃዳዊና የተማከለ የመንግስት አወቃቀር የአገራችንን ብዝሃነት የማያስተናግድና ብዝሃነታችንን የሚጨፈልቅ በመሆኑ
ለአገራችን ህዝቦች ከድህነት መውጫ አማራጭ መሆን ሳይችል ቀርቷል፡፡
የአገራችን ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትግልን በመምራት በህዝባችን ላይ ይደርስ የነበረውን ብሄራዊና መደባዊ ጭቆና እንዲወገድ በማድረግ በኩል ኢህአዴግ
መስዋትነት የከፈለበት መሰረታዊ መነሻም ይሄው ነው፤ የብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በእኩልነት እንዲረጋገጡ
ማስቻል፡፡
ኢህአዴግ ከህዝባችን ጋር በመሆን ባካሄደው መራራ ትግል ለድል ከበቃ በኋላ ዋነኛ ማዕከሉ የነበረው
ለብዝሃነታችን እውቅና የሰጠና ይህንኑ የሚያከብር ፌዴራላዊ ስርዓት መመስረት ነበር፡፡ በአገራችን የፌዴራላዊ ስርዓት እውን
መሆን ከጀመረ በኋላ የሀገራችን ህዝቦች ከግዳጅ አንድነት ወጥተው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው የተከበረባትና ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ተችሏል። ከበርካት የመራራ ትግል ዓመታት
በኋላም የአገራችን ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ወደውና ፈቅደው የሚኖሩባትን አገራቸውን መስርተዋል፡፡ በጋራ የቃል ኪዳን ሰነዳቸውም አፅንተዋል፡፡
የፌዴራል ስርዓታችን አንዳንድ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች
እንዲሚያራግቡት ሳይሆን ልዩ ባህሪያት ያሉትና በተለይ ለብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሁለንተናዊ መብቶችን ያጎናፀፈ ነው፡፡ ለብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትና ለህዝቦች ማንነት የሚሰጠው ትኩረት የፌዴራሊዝም ስርዓታችን
ልዩ ባህሪያትና መገለጫዎች
ናቸው።
የፌዴራላዊ ስርዓታችን በተጨባጭ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን እየፈጠረ መሆኑ በተረጋገጠበት በዚህ ወቅት የትምክህት ኃይሎች በህዝቦች መራራ ትግል ላይመለስ የተቀበረውን የግዳጅ አንድነት በመናፈቅ የፌዴራል ስርዓቱን ‹‹በታኝ ነው›› በማለት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሲያጣጥሉትና ለርካሽ ተግባራቸው መሳሪያ ሊያደርጉት ሲሞክሩ ይስተዋላል። በሌላ ጎኑ ደግሞ ጠባብነት የተጠናወታቸው ሃይሎች በአገራችን የብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብቶች ህገመንግስታዊ እውቅና
አግኝተውና ተከብረው ባለበት ሁኔታ ባለፉት ስርዓቶች የነበሩ ችግሮችን ዛሬም ድረስ እንደቀጠሉ በማስመሰል የፌዴራል ስርዓቱ ላይ ሲዘምቱ ይታያሉ፡፡
የፌዴራላዊ ስርዓታችን አጠቃላይ ዓላማ የህዝቦችን ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ የማስፈን እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን የሚያፋጥን፤ አንድ የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ መገንባት ነው። ባለፉት ዓመታት በተጨባጭ እንደታየው ፌዴራላዊ ስርዓታችን የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ አድርጓል። በህገ መንግስታችን አንቀፅ 89 በግልፅ እንደተቀመጠው ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ሃብት እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበት፣ ሀብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የሚከፋፈልበት እንዲሁም ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚኖሩባቸውና በማደግ ላይ ያሉ ክልሎችን መንግስት ልዩ ድጋፍ የሚያደርግበት አሰራር እንዲዘረጋ በተደነገገው መሰረት ባለፉት ዓመታት በተከናወነው ተግባር ክልሎች የመልማት እድል አግኝተው አቅማቸው እየጎለበተና በህዝቦቻቸው ኑሮ ላይ የተሻለ ለውጥ መመዝገብ ችሏል።
የሀገራችን ፌዴራሊዝም በፉክክር ላይ ሳይሆን በትብብር ላይ የተመሰረተ አብሮ የመልማትና የማደግ አቅጣጫን የሚከተል በመሆኑ የህዝቦችን እኩል የመጠቀም መብት እያረጋገጠ ይገኛል። የፌዴራል ስርዓታችን በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ የአገራችን ህዝቦች ዋነኛ ጠላታቸው በሆነው ድህነት ላይ እንዲዘምቱ አስችሏቸዋል፡፡ የአገራችን ህዝቦች የሁልጊዜም አጀንዳቸው ከድህነት
መላቀቀ በመሆኑ በዚህ ጉዞ ላይ መንገዳቸውን ሊያደናቅፈቸው የሚጥር
ሁሉ ዋጋ መክፈሉ አይቀሬ ነው፡፡ የአገራችን ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ‹‹ልዩነታችን ውበታችን፤ አንድነታችን ጥንካሬያችን››
በማለት በልዩነታቸው ውስጥ አንድ የሚያደርጋቸውን ከድህነት የመውጣት ህልማቸውን ለማሰካት ዛሬም የሚያደርጉት ርብርብ ተጠናከሮ ይቀጥላል
፡፡
No comments:
Post a Comment