EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Tuesday, 4 August 2015

አክራሪነት የደቀነው አደጋ

(በእውነቱ ብላታ - ሚኒስትር ዲኤታ)

አገራችን የበርካታ ሃይማኖቶች መናሃሪያ አገር ነች፡፡ እጅግ በርካታ የአለማችን ሃይማኖቶች ከፈለቁበት መካከለኛው ምስራቅ የመነጩ ኃይማኖቶችን በቀደምትነት ተቀብላ ያስተናገደች አገር ነች፡፡ የአይሁድ ኃይማኖት፣ ክርስትናና እስልምና ገና ከጠዋቱ መስፋፋት ሲጀምሩ ተቀብለው ካስተናገዱ የአለማችን አገሮች ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ አገር ናት፡፡ ከነዚህ ጥንታዊ ሀይማኖቶች በተጨማሪ በኋለኞቹ ዘመናት በየትኛውም የዓለም ክፍል እየተፈጠሩ የተስፋፉ እምነቶችን ተቀብላም አስተናግዳለች፡፡ ከእነዚህ በተጓዳኝ አገራዊ መሰረት ያላቸው ሃይማኖታዊና ባህላዊ እምነቶችንም ያስተናገደች አገር ነች፡፡
የእነዚህ ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ እምነቶች ተከታይ የሆኑ ህዝቦቻችን እጅግ አብዛኛውን ጊዜ በመቻቻልና በመተሳሰብ አገራቸውን ገንብተዋል፡፡ ከውጭ ጥቃትም ተከላክለዋል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአገራችን የቆዩት መንግስታት ለዘመናት በተከተሉት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ምክንያት አንዱን ሃይማኖት ከሌላው እያስበለጡ በህዝቦች መካከል በሃይማኖት እኩልነት ላይ ያልተመሰረተ ግንኙነት እንዲሰፍን አድርገው ኖረዋል፡፡

ይህን የመሰለ ግልፅ ጭቆናና በደል ከዘውዳዊው ስርአት ጀምሮ እስከ ደርግ መንግስት ውድቀት ከቀጠለ በኋላ አዲሱ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የሃይማኖት እኩልነትን በህግና በተግባር ለማስከበር ችሏል፡፡
አገራችን በዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስት የምትመራ ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ ከሁሉ በፊት ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል እውቅና ተሰጥቷቸው ተከብረዋል፡፡ በህገ መንግስታችን መሰረት የሃይማኖት የበላይ ወይም የበታች የለም፡፡
ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል ናቸው፡፡ ሃይማኖትና መንግስት ተነጣጥለዋል፡፡ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ሃይማኖትም በመንግስት አስተዳደር ጉዳይ እጁን አያስገባም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሃይማኖትና ትምህርት እንዲነጣጠሉ ተደርጓል፡፡ ዜጐች የመረጡትን ሃይማኖት ያለአንዳች ውጫዊ ተፅዕኖና ግዳጅ የመከተልና የማክበር መብትን ተጐናፅፈዋል፡፡ በተግባርም ሁሉም ሃይማኖቶች በነፃነት የሚገለፁ፤ የሚሰበኩና የሚከበሩበት ሁኔታ ተረጋግጧል፡፡
መንግስት ሁሉም ሃይማኖቶች በቂና ተገቢ የእምነት ማድረሻ ስፍራዎች እንዲያገኙ፣ ለሁሉም ሃይማኖቶች በቂ የቀብር ቦታዎች እንዲመቻቹ፣ ሃይማኖታዊ በዓላት እኩል መንግስታዊ እውቅና ተሰጥቷቸው እንዲከበሩ ተደርጓል፡፡
በሃይማኖት ላይ የተመሰረተ የማበላለጥ ስራ እንዳይኖር፣ የመንግስት አገልግሎት ለሁሉም ዜጐች ከሃይማኖት ልዩነት ባሻገር በእኩልነት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ በእነዚህ ሁሉ መስኮች የሚፈፀሙ ስህተቶች ካሉም በህግ የሚያስጠይቁ እንደሆኑ ተደርጓል፡፡
ከዚህ አኳያ ሲታይ በአገራችን የሃይማኖት እኩልነት በህግና በተግባር የተከበረ ሆኗል፡፡ ይህም በመሆኑ ከአሉባልታና መሰረተ ቢስ ስሜት ቀስቃሽ ውንጀላዎች በስተቀር ሃይማኖታዊ አድሎ እንዲፈፀም የሚያደርግ ህግ አለ ብሎ በማስረጃ የተደገፈ ወቀሳና ትችት ለማቅረብ አንዳችም ተጨባጭ መሰረት የሌለበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
እነዚህ እንደተጠበቁ ሆኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ አክራሪነት በአገራችን በመገንባት ላይ ያለውን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርአት የሚፈታተን ሆኗል፡፡ የእስልምና ሆነ የክርስትና እምነቶችን ሽፋን በማድረግ የሚካሄዱት ፅንፈኛ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተደጋገሙና አልፎ አልፎም የግጭት መልክ እየያዙ ሲሄዱ ቆይተዋል፡፡
በዚህ ረገድ በክርስትናና እስልምና እምነቶች ሽፋን የሚራመዱ ፅንፈኛ ተቃውሞዎችን ስንመረምር የምናገኛቸው እውነታዎች በሃይማኖት ሽፋን ለመነገድ የሚሞክሩት ወገኖች ምን ያህል መሰረተ ቢስ በሆነ አጀንዳ ሁከትና ትርምስ ለመፍጠር እንደሚሞክሩ የሚያሳዩ ናቸው፡፡

4 comments:

  1. This comment has been removed by the author.

    ReplyDelete
  2. እኛ ኢትዮጵያውያን ብሔር, ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች በዘር.. በሃይማኖት.. ልዩነት ሳይኖር የእኩል ተጠቃሚነት መብት በኢፌዲሪ ህገመንግሥት ተረጋግጧል.... በመፈቃቀድ እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነታችን ውበታችን ሆኖ.....ብዙሃነታችን ባግባቡ ባስተናገደ ስርዓት እየተዳደርን ነው.... በኢትዮጵያ ያንዱ ሃይማኖት የበላይ የሌላው የበታች ተደርጎ የሚታይበት አሠራር የለም.... I አሸባሪ ሃይማኖት የለውም....... አክራሪነት እኔ ብቻ ትክክል ነኝ ማለት ፀረ- ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው... የመቻቻል ክብር የሚጎድላችው.... የኔ ብቻ ይበልጣል ባይ.... የሁለቱም ጫፍ የሃይማኖት አክራሪዎች እና ትምክተኞችን መጨረሻችው ለሃገራችን ዲሞክራሲያዊ አንድነት የማይበጁ ISIS እና መሠል ጠላት ስለሚሆኑ በጋራ እንታገላለን !!!!! ሙስሊምና ክርስቲያኑን ኢትዮጵያዊ በሃይማኖት... በጎሣ...ለመነጣጠል መርዝ የምትረጩ እንደ እነ-""Dimtsacin Yisema "" ወገኖች እረፉ..... እኛ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያንና ሙስሊሞች የአሸባሪዎች አመለካከት አያለያየንም!!! !!!!!!

    ReplyDelete
  3. እኛ ኢትዮጵያውያን ብሔር, ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች በዘር.. በሃይማኖት.. ልዩነት ሳይኖር የእኩል ተጠቃሚነት መብት በኢፌዲሪ ህገመንግሥት ተረጋግጧል.... በመፈቃቀድ እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነታችን ውበታችን ሆኖ.....ብዙሃነታችን ባግባቡ ባስተናገደ ስርዓት እየተዳደርን ነው.... በኢትዮጵያ ያንዱ ሃይማኖት የበላይ የሌላው የበታች ተደርጎ የሚታይበት አሠራር የለም.... አሸባሪ ሃይማኖት የለውም....... አክራሪነት እኔ ብቻ ትክክል ነኝ ማለት ፀረ- ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው... የመቻቻል ክብር የሚጎድላችው.... የኔ ብቻ ይበልጣል ባይ.... የሁለቱም ጫፍ የሃይማኖት አክራሪዎች እና ትምክተኞችን መጨረሻችው ለሃገራችን ዲሞክራሲያዊ አንድነት የማይበጁ ISIS እና መሠል ጠላት ስለሚሆኑ በጋራ እንታገላለን !!!!! ሙስሊምና ክርስቲያኑን ኢትዮጵያዊ በሃይማኖት... በጎሣ...ለመነጣጠል መርዝ የምትረጩ እንደ እነ-""DIMTSACHIN YISEMA"" ወገኖች እረፉ.. እኛ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያንና ሙስሊሞች የአሸባሪዎች አመለካከት አያለያየንም !!!!!!

    ReplyDelete
  4. Fundamentalism isn't about religion, it's about power. Salman Rushdie

    ReplyDelete