(በሓዱሽ ካሡ)
ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ከሶስት አመት በፊት ነሐሴ 15/2004 ዓ.ም በህይወት ከተለየን ጀምሮ ከደቂቅ እስከ ሊህቅ እንዲሁም ከህፃን እስከ አዋቂ በአጠቃላይ መላ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ጨምሮ የዓለም ህዝቦች፣
የሀገራት መሪዎች፣ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ የዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ድርጅት መሪዎች፣ ከያንያን፣ የስፖርት ዓለም ሰዎች፣ የሲቪክ ማህበራት መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ለሰላም ዘብ የቆሙ ኃይሎች፣ የዴሞክራሲ
ጠበቆች፣ የአረንጓዴ ልማት አቀንቃኞች፣ ተመራማሪዎችና ዲፕሎማቶች፣ ወዘተ
“የምጡቅ አዕምሮ ባለቤት” /World Class Mind/ ከሚለው ጥልቅ እና መሳጭ አገላለፅ
ጨምሮ
የተለያዩ አባባሎችን በመጠቀም አክብሮታቸውንና አድናቆታቸውን ገልፀውለታል።
የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊን ስብእናና ተግባር በተመረጡ ቃላት ንግግር ወይም በጥቂት ገፅ ፅሁፍ ወይም በተወሰኑ መጣጥፎች ብቻ
ለመግለፅ መሞከር በጣም አዳጋች ነው፡፡
ለዚህም ነው
የእሱን ከውቅያኖስ የጠለቀና ከአድማስ ባሻገር የመጠቀ ዘመን ተሻጋሪ ተራማጅ አስተሳሰብና ህያው ተግባራቱን አስመልክተው ብዙዎች
በተረዱትና አቅማቸው በፈቀደው
ልክ
የተለያየ አገላለፅ ቢጠቀሙም
ስለሱ ከተነገረው በላይ ያልተነገረለት ይበዛል የምንለው።
መለስ
ዜናዊ
ፈላስፋ፣ የአዳዲስ ሃሣብ አመንጪ፣ ዕውቅ ፖለቲከኛ፣ የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ቀማሪ፣ አዋጊና ተዋጊ፣ ዲፕሎማት፣ ተመራማሪ፣ የህዳሴ መሃንዲስ፣ የመሠረታዊ ለውጥ መሪ
ብቻም
ሳይሆን የሩቁን አቅርቦ ማየት የቻለ ታላቅ መሪ ነበር።
መለስ ፋሽስታዊውን ወታደራዊ የደርግ ሥርዓት ለመደምሰስ በተደረገው እልህ አስጨራሹ የ17 ዓመታት መራራ
የትጥቅ ትግል ወቅት አንድም ለመድረኩ የሚመጥኑ፣ አልያም
ከዓመታት በኋላ ዕውን የሚሆኑትን ጉዳዮች
የሚያመለክቱ ሳይንሳዊ ትንታኔዎችን ያቀርብ ነበር። ለምሳሌ ፋሽስታዊው ወታደራዊ ደርግ ሞት አፋፍ ላይ በነበረበት በ1981 ዓ.ም የደርግ
መንግሥት ከተገረሰሰ በኋላ ስለሚኖረው የሽግግር ወቅት
ሂደትና የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ
አስመልክቶ የሚከተለውን ብሎ ነበር።
“አንዳንዶቻችን በአጋጣሚ ክቡር የመስዋዕትነት ዕድል ሳይገጥመን ድሉን እናጣጥመዋለን፡፡ ሆኖም ከትጥቅ ትግሉ ይልቅ ቀጣዩ የትግል መድረክ ውስብስብና ከባድ ነው፡፡ ለምን ቢባል አሁን እያደረግነው ባለው ፍልሚያ የትምክህተኝነት አመለካከት ጠበቃውና የድህነት ዘበኛውን ደርግ አቸንፈን ከመንበረ ሥልጣኑ የምናሽቀነጥረው በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ በፖለቲካ አውድማ ቢሆንም በዋነኛነት ግን በጠመንጃ አፈሙዝ ነው፡፡ ስለዚህ የትምክህት አስተሳሰቡ በአገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 100 ዓመት ሰርፆ የቆየ በመሆኑ እንዲሁም በውስጥም በውጭም ያሉት የርዕዮቱ መሪ ተዋንያን የትምክህት ኃይሎች በአደረጃጀት እና በገንዘብ የፈረጠሙ ስለሆኑ ህዝቡን የማወናበድ አቅማቸው ከባድ ነው፡፡ ከዚህ ጐን ለጐን የጠባብነት አቀንቃኞችም ህዝቡን የማደናገር ስልታቸው የዋዛ አይሆንም፡፡ በአጭሩ የበሰበሰውን የትምክህትና የጠባብነት አስተሳሰብ ጭቃን በውሃ አጥቦ የማፅዳት ያህል በቀላሉ ከሰው ጭንቅላት ማራገፍ የሚቻል አይሆንም፡፡ ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ በከፍተኛ የዓላማ ፅናትና በእልህና በወኔ መታገል ይጠይቃል፡፡ እንዴትና ለምን ቢባል እኛ የምንከተለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ አንድም ለሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ መሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ርዕዮቱ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ብቻ ተከልሎ በመቆየቱ ይህንን የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ የሚወስነው አማራጭ የሌለው ተራማጅ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የዕለት ተዕለት መመሪያ አድርገው እንዲንቀሳቀሱ የማድረጉ ጉዳይ ራስ ዳሽን ተራራ ላይ እንደመውጣት ያህል ከባድና አድካሚ ነው፡፡ ሆኖም ከብዙ መውጣትና መውረድ በኋላ የትምክህትና ጠባብነት አመለካከት እየሟሸሹ ሄደው የእኛ አስተሳሰብ የበላይነት ማግኘቱ አይቀሬ ነው ብሎ ነበር።”
ታላቁ
መሪ
ታጋይ
መለስ
ዜናዊ
ከ26
ዓመት
በፊት
እንዳለው ባለፉት 24 ዓመታት በተደረገው ትንቅንቅ
የትምክህትና ጠባብነት አስተሳሰቦች እየተደረመሱ
መጥተዋል፡፡ ሆኖም አሁንም ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የበላይነት /hegemony/ አልያዘም፡፡ አሁንም ቢሆን
የትምክህትና የጠባብነት አስተሳሰብና ተግባሮች እንደ እስስት ቀለማቸውን እየቀያየሩ
በኪራይ ሰብሳቢነት የፖለቲካል ኢኮኖሚ ጉያ
ተወሽቀው
የሥርዓቱ አደጋ መገለጫ
ሆነዋል።
ታላቁ
መሪ
ታጋይ
መለስ
ዜናዊ
በ1968
ዓ.ም
የኤርትራ ሀርነት ግንባርን
/ጀብሃ/ ፀረ-ህዝብ
ተፈጥሮ አስመልክቶ የተናገረውም
ለአርቆ ተመልካችነቱ ማሳያ ነው። የጀብሃን እኩይ ተግባራት የታዘበው መለስ ከ40 ዓመታት በፊት
“ግድ የለም አሁን
ለጊዜው እነ ጀብሃ
ይፈንጩ፣ ማን እንደ
ብረት ጠንክሮ እንደሚቀጥልና
ማን ደግሞ መሃል
ሜዳ ላይ እንደሚቀር
ወደፊት ታሪክ ያሳየናል፡፡
እኛ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች
የጠራ የትግል መስመራችንን
ጨብጠን መላ ህዝባችን
ከጐናችን አሰልፈን እነሱ
ቁልቁል፣ እኛ ሽቅብ እንደምንወጣ
ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም፡፡”
ብሎ
ነበር፡፡
መለስ
እንዳለውም ጀብሃ
በዋነኛነት ከራሱ ተፈጥሮ
በመነጨው ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ውስጣዊ ችግር፣
የኋላ
ኋላም
ደግሞ
የህወሐት ዱላ አርፎበት በ1973 ዓ.ም
ተፈራካክሶ ተበታትኗል፡፡
በተመሳሳይ ሌሎች ፀረ-ሰላም እና
ፀረ-ዴሞክራሲ ኃይሎችም ባለፉት 40 ዓመታት በየትግል ምዕራፉ ቁልቁል እየወረዱ ተራግፈዋል፡፡
አሁንም የትምክህትና የጠባቡ ጐራ ያለማቋረጥ የቁልቁለት መንገዱን ይዞ
በፍጥነት ጭቃ ውስጥ በመስመጥ ላይ ነው፡፡ በአንፃሩ የኢህአዴግ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመር በየጊዜው እየጐመራና እየሰፋ ሽቅብ በመውጣት የ90
ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋሻ መከታ ሆኖ በማገልገል ላይ መሆኑ የማይታበል ሐቅ ነው።
ታላቁ
መሪ
የቀየሰውና አሁን መሠረተ ሰፊ፣
ፈጣን፣ ተከታታይና ህዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ
የሆነበትና እየሆነበት ያለው እድገታችን ምንጭ የሆነው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመር በ1994 ዓ.ም የመላ ኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና አባላት እንዲሁም ደረጃ በደረጃም የአብዛኛው የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች
እየሆነ በመሄድ ላይ በነበረበት ወቅት ፈጣን ልማት መቼ ነው የሚረጋገጠው?
ምልዓተ ህዝቡስ
መቼ
ነው
የመስመሩ ውጤት ተቋዳሽ የሚሆነው?
ተብሎ
ተጠይቆ ነበር፡፡ ታላቁ መሪ
መለስ
ዜናዊም እንዲህ ብሎ መልሶ ነበር “እውነተኛ የወይን ጣዕም
የሚታወቀው በተጠመቀ ማግስት
ሳይሆን እየዋለ እያደረ
ከዓመታት ቆይታ በኋላ
ነው። የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ የህዳሴ
ፍሬና ትሩፋትም በዋነኛነት
ማጣጣም የሚቻለው በሁለት
ዓመታት ጊዜ ሳይሆን
ከዓመታት በኋላ ነው” በማለት በርቱዕ አንደበቱ ምላሽ ሰጥቶ ነበር።
መለስ
ዜናዊ
አስቀድሞ እንደተናገረው በእሱ ቀማሪነትና መሃንዲስነት ዕውን የሆነው
ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመር ባለፉት 12 ዓመታት በመላ
ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ድፍን ዓለምን ጭምር ያስደነቀና በአደባባይም ምስክርነት የተሰጠበት ዘርፈ ብዙ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በዓለም ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉት ብሪክስ (ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ) በመባል የተሰባሰቡትን አገራት ቀድመው የዕድገቱን ምህዋር ይቆጣጠሩታል ከተባሉትና
emerging countries በመባል እየተጠሩ ካሉት አራት
ሀገራት
(ፊሊፒንስ፣ ኢንዶኔሽያ፣ ናይጄሪያና ኢትዮጵያ) መካከል አንዷ ነች፡፡
ታላቁ መሪ ምስጋና ይግባውና
በሀገራችን ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ370 ቢልዮን ብር
በላይ
ካፒታል ያስመዘገቡ 3,522 የውጭ
ቀጥታ
ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተመዝግበዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት መካከል በኢንቨስትመንት መዳረሻነት ምርጥ አራተኛ ለመሆን በቅታለች። በአፍሪካም ከቀዳሚዎቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች አንዷ
ነች።
የሀገር ፍቅር ማለት የህዝብ ፍቅር ነው፡፡ ሀገር ማለት ህዝብ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ትርጉም የለውም፡፡
የሚል
ፅኑ
እምነት ይዞ ለአፍታ እንኳን ከህዝባዊ ዓላማው ግራና ቀኝ ሳይል
ለ37 ዓመታት ያህል በቆራጥነት የታገለውን
የታላቁ
መሪ
መለስ
ዜናዊን አርማ ያነገቡት፣
የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀድና በመተማመን ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ገንብተው፣
አንድ
የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት
የሚያስችላቸውን ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትም የኋሊት እንዳይመለስ እንደ ዓይናቸው ብሌን ጠብቀው እያስቀጠሉት ይገኛሉ።
መለስ
ዜናዊን ዘንድሮ የምንዘክረው ከሦስት ዓመታት በፊት አጋጥሞን በነበረው የሀዘን ድባብ ላይ ሆነን አይደለም፡፡ ይልቁንም መላ የኢትዮጵያ ብሄር፣
ብሄረሰቦችና ህዝቦች በኢህአዴግ የሚመራው የኢፌዴሪ መንግሥት አዝማችነት የታላቁን
መሪ
አደራ
ጠብቀው የመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በስኬት በፈፀሙበት
ወቅት ላይ ሆነን ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለህዝብ ተፈጥሮ
ከዓላማው ዝንፍ ሳይል
ለህዝብ የኖረውንና ክቡር
መስዋእትነት ከፍሎ በአካል የተለየንን የታላቁን
መሪ 3ኛ
ዓመት የሚዘክሩት እሱ አምርሮ የሚጠላውን ድህነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳይመለስ ከወዲሁ ለመደቆስ ወገብ የሚያጐብጡ ዓበይት ተግባራት ያካተተው ሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዝግጅት ዋዜማ ላይ ሆነው
ነው፡፡ እንደ
ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2017 ዓ.ም ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለማሰለፍ ወሳኝ ምዕራፍ የሆነውን
እና
ሀገሪቷንና ህዝቧን ወደ ከፍታ ማማ ይበልጥ ሽቅብ የሚያወጣውን
የሁለተኛውን ዙር
የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
በኢህአዴግ 10ኛ ጉባኤ የሚፀድቅበትን ቀን በጉጉት ይጠብቁታል።
በአጭሩ የታላቁ መሪያችንን
3ኛ
ዓመት
የመስዋእትነት ዕለት
የምንዘክረው ሀዘን ላይ ሆነን ሳይሆን ፀረ-ሰላምና ፀረ-ዴሞክራሲ ኃይሎች ቁልቁል እያዘገሙ ባሉበት በአንፃሩ በኢህአዴግ የሚመሩ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ደግሞ ዕለት በዕለት ሽቅብ እየወጡ ድርብ ድርብርብ ድሎች ጨብጠው
የመለስን ሌጋሲ ለማስቀጠል ብሩህ ተስፋ ያሰነቃቸውን ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በእልህና በወኔ ለማጠናቀቅ ቀበቶአቸውን ጠበቅ አድርገው
ነው።
No comments:
Post a Comment