ከዛሬ
3 ዓመት በፊት ከአሸባሪው ኦብነግ ጋር በመቀናጀት ድንበራችንን አቋርጠው ከኤርትራ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሲገቡ በተያዙ ሁለት ሲውዲናውያን ጋዜጠኞች ጉዳይ
ራሱን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አድርጎ የሚጠራው አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ በጋዜጠኝነት ጥበቃና ተቆርቋሪነት ስም ራሳቸውን
ያደራጁ ዓለም አቀፍ ቡድኖች መነጋገሪያ ፈጥረው ነበር።
ሲውዲናውያኑ ጋዜጠኞች በመሆናቸው መያዝ የለባቸውም ከሚል ዓለም አቀፍ ህግን ያላከበረ መከራከሪያ ነጥብ ጀምሮ የሰዎቹን የጋዜጠኝነት ሙያ ሽፋን በማድረግ ድንበራችንን ማቋረጣቸው፣ ከአሸባሪው ኦብነግ ጋር ተቀናጅተውም መንቀሳቀሳቸው ኃጢዓት እንዳልሆነ በመቁጠር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ መለቀቅ አለባቸው የሚሉ መግለጫዎች ሲያወጡ ነበር።
በዚያን ወቅት ታላቁ መሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሁለቱን ግለሰቦች በሚመለከት ስለተነሳው ጉዳይ የሰጡት ምላሽ የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው የሚል ነበር። የሰዎቹን መታሰር ከነባራዊ ሁኔታውና ከሆነው ጉዳይ አንፃር ለመመልከት የማይሹ ወገኖች ከዘረኝነት እንዲታቀቡም ነበር በገለፃቸው ያሳሰቡት። የህግ የበላይነት በተከበረባት ሀገራችን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤቶች ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የተለያዩ ስያሜዎችን እየለጠፈ የህዝቦቻችንን ጥቅም በሚዳፈር መልኩ የሚንቀሳቀስ ማንም ጎትጓች በሀገራችን ጉዳይ ጣልቃ ሊገባ እንደማይችልና እንደማይገባም ነበር በአፅንኦት ያስረዱት።
ይህን ሀቅ እና እውነታ የኢፌዴሪ መንግስትና የሀገራችን ህዝቦች ዛሬም በፀና መልኩ እያረጋገጡት ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ጉዳይ ወሳኙ ኢትዮጵያዊው ዜጋ መሆኑን ሁሉም ወገን ሊገነዘብ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውንም ቀጥለዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም በ5ኛው አጠቃላይ ምርጫ ዋዜማ ለአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጠያቂያቸው ይህንኑ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ከተለያዩ የውጭ ሀይሎች የሚሰነዘር ጣልቃ ገብነትና የዜጎችን ሚና ለማሳነስ የሚደረግ ሙከራ ኢትዮጵያውያንን እንደ መናቅ የሚቆጠር መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በሀገራችን ጉዳይ የውጭው ኃይል የሚያናፍሰው የተሳሳተ መላምትና አንዳንድ ለፅንፈኝነት የቀረቡ ተቃዋሚዎች የሚያሰሙት መሰረተ ቢስ ስሞታ ሊዳኝ የሚችለው በህዝቡ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፤ ዳኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፤ ዳኝነቱ ለህዝቡ ሊተው ይገባል በማለትም አስገንዝበዋል።
በእርግጥም ዳኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በ5ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የወሳኝነቱን ሚና በብቃት ተወጥቷል። በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላምና እየጎለበተ ያለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በትክክለኛው አቅጣጫ እየሄደ መሆኑንም አሳይቷል። ዴሞክራሲ በሂደቱ የሚለካና የህዝቡን ውሳኔ ሰጪነት በማክበር የሚመዘን በመሆኑ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች የህዝቡን ድምፅ ሊያከብሩ፣ ህዝቡም በጀመረው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ አግባብ ሰላሙን ሊያደፈርሱ የሚሞክሩ ወገኖችን እንደወትሮው ሊታገላቸቸው ቃል እየገባም ይገኛል።

ህዝቡ
በጣልቃ ገብ ወገኖች አሉባልታና በአንዳንድ ተቃዋሚዎች የበሬ ወለደ ውዥንብር ሳይዘናጋ የሀገሩ ባለቤት ራሱ መሆኑን በምርጫው እንዳረጋገጠውና
ዳኝነቱን እንደሰጠ ሁሉ አሁንም ሰላሙን በማስጠበቅ የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤትነቱ በተረጋገጠበት 5ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሰጠው
ድምፅ እንዲከበር ማድረግ ይኖርበታል። የዴሞክራሲያዊ መብቱ አንዱና ዋነኛ መገለጫ በሆነው የመራጭነት መብቱ በካርዱ ያፀናው ሀሳብና
በየ5 ዓመቱ የሚመሰርተው ህዝባዊ መንግስት በእሱ ፍላጎት እንጂ በሌሎች አዛዥነት ወደፊትም እንደማይሆን በድጋሚ ሊያረጋግጥ ይገባል።
ህዝቡ በታላቅ ትዕግስትና ሰላማዊ መንፈስ ይበጀኛል ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ ወኪል በመምረጥና ለሰጠው ድምፅ በመታመን አሁንም ለሰላም፣ ለልማትና ለዴሞክራሲ መጎልበት የሚያደርገውን ሁሉ አቀፍ አስተዋፅኦ ማጠናከሩ የግል ፍላጎታቸውን በደም መፋሰስ ለማሳካት ሲቋምጡ የነበሩ አፍራሽ ኃይሎች ቁርጣቸውን እንዲያውቁና እርማቸውንም እንዲያወጡ አድርጓል።
በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ግንቦት 16 ቀን 2007ዓ.ም በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ወጣት ከአዛውንት ባልለየ ሁኔታ በረጃጅም ሰልፎች ርዝማኔ ያልተሰላቸው መራጩ ህዝብ ያሻውን የመምረጥ መብቱን አስከብሯል። ከምርጫው መካሄድ አስቀድሞ በነበሩ ጊዜያት ፅንፍ የወጡ ግለሰቦችና ቡድኖችን የፀብ ጫሪነት አዝማሚያ በማሳየት ምርጫው ላይ ያልተገባ ጥላ ያርፋል ብለው የሰጉ ወገኖች በሰላም ወዳዱ የሀገራችን ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተደምድሟል፡፡
ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን በምርጫው እለትም ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ረጃጅሞቹ ሰልፎች ያላሰለቿቸው አዛውንቶች ሳይቀሩ እድሜ ትኩሳቱን እንዳልነፈጋቸው ወጣቶች በጋለ አገራዊ ስሜት ይበጀኛል፣ ያስተዳድረኛል ያሉትን መንግስት በመምረጥ በአመርቂ ሁኔታ መሳተፋቸውን ለመዘገብ ተገደዋል።
ይህ የሀገራችን ህዝቦች በዴሞክራሲያዊ መብታቸው የመጠቀም ዝንባሌያቸውና ግንዛቤያቸው በተገቢው ማደጉን ያስረዳል። ለድምፅ መስጫዋ ካርድ ልዩ ዋጋ በመስጠትና በሰላማዊ ሁኔታ በመምረጥ ለሀገራቸው ሁለንተናዊ ጉዳዮች ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች መሆናቸውን በግላጭ ያስመሰከሩት የሀገራችን ህዝቦች ፅንፈኝነትና ብጥብጥ የናፈቃቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች አጉል ህልም ከማጨለም ባለፈ የሁሉም ህዝቦች ፍላጎት በራሳቸው በህዝቦቹ ውሳኔ ብቻ የሚዳኝ መሆኑን ለመላው ዓለም አስረግጠው ነግረዋል።

በ5ኛው አጠቃላይ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡ 36 ነጥብ
8 ሚሊየን መራጮች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት መሳተፋቸውና ያሻቸውን ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲ በነፃነት መምረጣቸው ለኢትዮጵያና
ኢትዮጵያውያን ኩራትና ክብር ነው።
5ኛው አጠቃላይ ምርጫ መምረጥም፣ መወሰንም የማንችል አድርገው
በመቁጠር ሊወስኑልንና ያሻቸውን ርዕዩተ ዓለማዊ አተያይ ከራሳቸው ጥቅም አንፃር ሊያዙልን የሞክሩ ኒዮሊበራል ኃይሎች ይህ በኢትዮጵያ
ምድር ሊሆን እንደማይችል ህዝባችን ዳግም ትምህርት የሰጠበት ሉዓላዊ መድረክ ነው።
የነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫው ሰላማዊነትና ዴሞክራሲያዊነት ባለ ድሉ የሀገራችን ወጣቶች፣ ሴቶችና አጠቃላዩ መራጩ ህዝብ ነው። የምርጫው ሰላማዊነትና ዴሞክራሲያዊነት ባለ ገድሉ በሰላማዊ መድረክ ተወዳድረው ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ህዝቡ የሰጠንን ድምፅ በፀጋ ተቀብለን ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለው የወሰኑና ለዚሁ አስተዋፅኦ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ጭምር ናቸው።
ዛሬም የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነውና ለሽብርና ብጥብጥ የማትመች ሀገር በመፍጠር በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ አግባብ ምርጫውን ያከናወነው የሀገራችን ህዝብ በሰላሙ ጉዳይ ያለውን አቋም ይበልጥ ማጠናከር ይኖርበታል። ህዝብ እንዲመርጣቸው አማራጮቻቸውን አቅርበው፣ ተከራክረውና ራሳቸውን በበቂ መጠን አስተዋውቀው ለምርጫ የቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የህዝቡን ድምፅ ሊያከብሩ ግድ ይላል። የህዝብ ወሳኝነትና ዳኝነትን በመቀበልና በማመን በሀገራችን ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ ወገኖችም ለዚህ የተመቸ ምህዳር በኢትዮጵያ ያለመኖሩን፣ አስተሳሰቡም ጊዜ ያለፈበት መሆኑን ሊረዱ ይገባል።
የምርጫውን ነፃና ፍትሃዊነት በማስከበር ሰላም እንዲያሸንፍ፣ ዴሞክራሲ እንዲጎለብት ታላቁን ሚና የተጫወተው የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ከምንም በላይ ክብር ይገባዋል። የሀገራችን ህዝቦች በሀገራቸው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተማምነው፣ ለሰላሙ ዋጋ ሰጥተውና መብታቸውን በካርዳቸው ብቻ እንደሚያስከብሩ አቋም ይዘው መብታቸውን ሊቀሟቸው የተዘጋጁ ኃይሎችን በማሳፈር ያሳዩትን አቋም፣ ከምርጫው ውጤት መገለፅ በኋላም በተመሳሳይ አቋምና በፅናት በማረጋገጥ ብጥብጥ ናፋቂዎችን ሊያሳፍሯቸው ይገባል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በይፋ በሚገልፀው ውሳኔ መሰረት የሚቋቋመው መንግስትም ህዝቡ ምርጫውን ለማደናቀፍ የሞከሩ ኃይሎችን አሉባልታና ሽለላ ከቁብ ባለመቁጠርና በመምረጥ መብቱ በመጠቀም በራሱ የውሳኔ ሰጪነት ላፀናው ሰላምና በውስጡ ላሰረፀው በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ እጅ ሊነሳው ይገባል!

ክብርና ምስጋና ሰላሙን ላስከበረው፣ ለዴሞክራሲያዊ መብቱ መከበር ዘብ ለቆመው የኢትዮጵያ
ህዝብ!
This comment has been removed by the author.
ReplyDelete