EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Wednesday, 20 May 2015

ለፈጣን ልማት፣ ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ላለው ዴሞክራሲ - ኢህአዴግ!!


ፈጣን  ልማት፣ ዘላቂ ሰላም እና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ የሚተጋውን ኢህአዴግ በመምረጥ የሀገራችን ህዳሴ እናረጋግጥ!!
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፦
በአዲሲቷ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ስልጣን የሚያዝበት ብቸኛው መንገድ በምርጫ የህዝቡን ይሁንታ በማግኘት ብቻ እንዲሆን በማያሻማ ሁኔታ በሕገ መንግስታችን ተደንግጓል። መቼም ቢሆን የህዝቡን ፍላጎትና ውሳኔ የሚያስቀድመው ኢህአዴግ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ፣ ፍተሓዊ፣ ሰላማዊ እንዲሁም በመላ ህዝባችን ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ ወደ ተጨባጭ ስራ ገብቷል። እስካሁንም በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው።
ምርጫው የተሳካ እንዲሆን መላው የሀገራችን ህዝቦች የመራጭነት ካርድ በማውጣትና በሂደቱ በንቃት በመሳተፍ እንዲሁም የቅድመ ምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን ያደረጋችሁትን ከፍተኛ አስተዋፅ ድርጅታችሁ ኢህአዴግ በክብርና አድናቆት ይመለከተዋል። በእስካሁኑ ተሳትፏችሁ የሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይበልጥ እየጎለበተ እንዲሄድ የማይተካ ሚና እንደተጫወታችሁት ሁሉ በምርጫው እለትም የስልጣን ባለቤትነታችሁ መገለጫ የሆነውን ካርዳችሁን ለኢህአዴግ በመስጠት የሀገራችንን ፈጣን ዕድገት እንድታስቀጥሉ ኢህአዴግ ጥሪውን ያቀርብላችኋል።
ሀገራችንን ከፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ በማላቀቅ ዋስትና ወዳለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ያሸጋገራትን ኢህአዴግን በመምረጥ የሀገራችን ህዳሴ እናረጋግጥ!
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፦
ከፍፁም አምባገነናዊ ስርዓት ተላቀን በህዝቦች መፈቃቀድ፣ መከባበርና መተማመን ላይ የተመሰረተ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት የቻልነው መላው የሀገራችን ህዝቦች ባካሄዱት መራራ ትግልና ብርቅዬ ልጆቹ በከፈሉት ክቡር መስዋትነት ለድል ከበቃንበት ግንቦት 20/1983 በኋላ ነው፡፡ ስለሆነም ይችን የድል ቀን በጉጉት በምንጠብቀው ምርጫ ዋዜማ ላይ ሆነን ማስታወሱ እጅግ ጠቃሚ ነው። ስለ ምርጫና ስለህዝብ ወሳኝነት ለመነጋገር የበቃነውም ግንቦት 20 ባስገኘችልን ፍሬ ነውና።
ግንቦት 20 ከፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ወደ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት፣ ከአሃዳዊ አምባገነናዊ ስርዓት ወደ መድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ከቁልቁለትና የኋልዮሽ ጉዞ ወደ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ያሸጋገረችን የትግላችን የመጀመሪያው ምዕራፍ ማብቂያና የሁለተኛው ምዕራፍ መጀመሪያ ናት። በመሆኑም ድርጅታችሁ ኢህአዴግ እንኳን ለግንቦት 20 የድል በዓላችሁ አደረሳችሁ እያለ በየምዕራፉ በስኬት እየታጀበ የተጓዘውን ድርጅታችሁ በመምረጥ የህዳሴ ጉዟችንን እንድታስቀጥሉ ጥሪውን ያቀርብላችኃል።
ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ጥቅም የሚበጅ ምንም ዓይነት የፖሊሲ አማራጭ ሳይኖራቸው ምርጫ በተቃረበ ጊዜ የማደናገሪያ አጀንዳ ይዘው በሚቀርቡ የሀገራችን ተቃዋሚዎች እና በድርጅታችሁ ኢህአዴግ መካከል ያለውን መሰረታዊ ልዩነት ይበልጥ እንድትገነዘቡት ለማድረግ ኢህአዴግ በርካታ የቅስቀሳ ፕሮግራሞችን ሲያቀርብላችሁ ቆይቷል። በዚህም በተግባር ተፈትነው ስኬታማ ውጤቶች እያስመዘገቡ ያሉትን የኢህአዴግ ፖሊሲዎች በተመለከተ የተሻለ ግንዛቤ ከመያዛችሁ በተጨማሪ የሀገራችን ተቃዋሚዎች አማራጭ የጥፋት አማራጭ እንደሆነ ለመረዳት እንደቻላችሁ ኢህአዴግ ይተማመናል። በመሆኑም ድምፃችሁን ሁሌም ለለውጥ ለሚተጋው ድርጅታችሁ ኢህአዴግ በመስጠት የተቃዋሚዎች የጥፋት አማራጭ በካርዳችሁ መና እንደምታስቀሩት ድርጅታችሁ ኢህአዴግ በፅናት ያምናል።
ኢህአዴግ በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የተገነባባት፣ የህዝቡ የስልጣን ባለቤትና ወሳኝነት የተረጋገጠባት እንዲሁም የሕግ የበላይነት የሰፈነባት፣ እኩልነትና ነፃነት እውን የሆነባት አዲሲቷን ኢትዮጵያን ለመገንባት መላ የሀገራችን ህዝቦች በማሰለፍ የታገለና ስኬታማ ውጤቶች እያስመዘገበ ያለ ህዝባዊ ድርጅት ነው። በእስካሁን ሂደቱም ብዝሃነቷን በአግባቡ ማስተናገድ ተስኗት ስትንገዳገድ ከቆየችበት የመበታተን ቋፍ በመታደግ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ፍትሐዊ ዕድገት በማረጋገጥ እጅግ ፈጣን እድገት እያዝመዘገቡ ካሉ ጥቂት የዓለማችን ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ችሏል። የምርጫ ካርዳችሁ ተጠቅማችሁ የጀመርነው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስራ ከእናንተው ጋር ዳር የሚያደርሰውን ኢህአዴግ እንድትመርጡ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርብላችኋል።
የግብርናና ገጠር ልማት ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ እየተጋ ያለውን ኢህአዴግ በመምረጥ የሀገራችን ዕድገት እናፋጥን!
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፦
ኢህአዴግ በተከተለው ትክክለኛ ሀገር በቀል ፖሊሲና በወሰደው ቁርጠኛ አመራር አማካይነት በግብርናና ገጠር ልማት ዘርፍ እመርታዊ ስኬቶች አስመዝግበናል። አርሶ አደሩንና አርብቶ  አደሩን የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጥ በመቻላችንና የተለያዩ አማራጭ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለማቅረብ ባደረግነው ከፍተኛ ርብርብ ለዘመናት ከእጅ ወደ አፍ አልፎ የማያውቀው ግብርናችን የሚሊዮኖችን ህይወት ቀይሯል፡፡
1983ዓ.ም በዋና ዋና ሰብሎች 52 ሚሊየን ኩንታል ብቻ የነበረውን ዓመታዊ የምርት መጠን ባሳለፍነው አመት ወደ 269 ሚሊየን ኩንታል አድጓል። ይህም በተበጣጠሰ የአርሶ አደር ማሳ የግብርና ዕድገት ማረጋገጥ አይቻልም እያሉ ሲወተውቱን የነበሩ አክራሪ የኒዮ-ሊበራል ሃይሎችና የሀገራችን ተላላኪ ተቃዋሚዎች አስተሳሰብ ምን ያህል የተሳሳተ እንደሆነ በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነ ህዝባችን ይገነዘበዋል።
1988 .ም በገጠር ከሚኖረው ህዝብ 47 ነጥብ 5 በመቶው በአሰቃቂ ድህነት ውስጥ ይኖር የነበረ ሲሆን የድህነትን ተራራ ለማፈራረስ በቀየስናቸው ፖሊሲዎችና በተግባር ባደረግነው ሁሉን አቀፍ ርብርብ ሀገራዊ የድህነት መጠኑ በ2005 .ም ወደ 26 በመቶ ማውረድ ችለናል፡፡ በ1994 ዓ.ም 14 ሚሊየን ገደማ የነበረው የተረጂዎች ቁጥር ባለፈው ዓመት ወደ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ማውረድ የተቻለ ሲሆን ይህ ቁጥር በቀጣይም ወደ ዜሮ ለማድረስ ከመላ ህዝባችን ጋር በመሆን እየተረባረብን እንገኛለን።
በርካታ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮቻችን ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ገንብተው የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ አስችሏቸዋል፤ በአለባበስ፣ በአመጋገብና በአኗኗር ዘይቤም ትርጉም ያለው ለውጥ በማስመዝገብ ላይ ናቸው። ተንቀሳቃሽና መደበኛ ስልክ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል፣ መገናኛ ብዙሃን መጠቀም ጀምረዋል። ባፈሩት ሃብት በተለያዩ የልማት መስኮች የሚሳተፉ ኢንቨስተሮች መሆን የጀመሩ አርሶና አርብቶ አደሮቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል። በመሆኑም በዚህ ወሳኝ ምርጫ ድምፃችሁን ለኢህአዴግ በመሰጠት የሀገራችን ህዳሴ በጋራ እንድናሳካ ድርጅታችሁ ኢህአዴግ ጥሪውን ያቀርብላችኋል።
በመሰረተ-ልማት ግንባታ እመርታዊ ለውጥ እያስመዘገበ ያለው ኢህአዴግን በመምረጥ የሀገራችን ህዳሴ እናስቀጥል!
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፦
የህዳሴ ጉዞአችንን ለማሳካትና የህዝባችንን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ መሰረተ ልማትን ፍትሐዊ በሆነ አኳኋን ለመላው ህዝባችን ለማቅረብ ባደረግነው ርብርብ ስኬታማ ውጤቶች በማስመዝገብ ላይ እንገኛለን። የመሰረተ ልማት ስራዎቻችን የወቅቱን የሀገራችን የልማት ጥያቄዎች ከመመለስና የህዝባችንን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር የቀጣይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገታችን ዋስትና ናቸው ብሎ የሚያምነው ኢህአዴግ ስኬት ካስመዘገበባቸው አውታሮች አንዱ መንገድ ነው፡፡ በ1983.ም በመላ ሀገሪቱ 18 81 ኪሎ ሜትር ብቻ የነበረው የመንገድ አውታር  ከ105 ሺ ኪ.ሜ በላይ ደርሷል። በዚህም 10 ሺ 765 የሚሆኑ የገጠር ቀበሌዎቻችን ከዋና መንገዶች ጋር ማገናኘት ተችሏል።
በባቡር መሰረተ-ልማት ዘርፍም እንዲሁ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን 2 ሺህ 395 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ለመዘርጋት የተያዘው ዕቅድ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል። ዘርፉ ከፍተኛ የፋይናንስ፣ የቴክሎኖጂና የሰው ሃይል የሚጠይቅ በመሆኑ በአንዳንድ የፕሮጀክቶቹ አካባቢዎች ዘግይቶ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም ፈተናዎቹ በቀጣይነት እየፈታን ወደ ተጨባጭ ስራ በመግባታችን በአሁኑ ጊዜ ግን በተሻለ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል። ኢህአዴግ በቀጣይም የሀገራችን ወጪና ገቢ ንግድ በማሳለጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለንን የመወዳደር ዓቅም ለማጎልበትና የህዝባችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማጠናከር ለባቡር መሰረተ-ልማት ስራ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል።
ኢህአዴግ የሀገራችን የሃይል አቅርቦት ከመሰረቱ ለመቀየር የተከተለው የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ በስኬቶች ታጅቦ ወደ ፊት እየገሰገሰ ይገኛል። በዚህም እስከ 1983 ዓ.ም በአገራችን የነበረው የሀይል አቅም ከ370 ሜጋ ዋት ያልበለጠ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 2 ሺህ 313 ሜጋ ዋት ማድረስ ተችላል። ጊቤ ሶስት እና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቁ ደግሞ አገራችን ከ10 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ሃይል ይኖራታል። በኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎች እንዳሉ ኢህአዴግ በውል ይገነዘባል፡፡ የእነዚህና መሰል ጥያቄዎች ከመሰረታቸው ለመፍታትም ኢህአዴግ ትክክለኛ የሆኑ ዘላቂ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አስቀምጦ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በዘላቂነት እንደሚፈታቸውም ጥርጣሬ የለውም፡፡
በቴሌኮምና የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ረገድም የኢህአዴግ ፖሊሲዎች በተግባር ተፈትሸው ውጤታማነታቸው ተረጋግጧል። በዚህም በ1982 .ም በመላ ሀገሪቱ የነበረው የቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 56 ሺህ 557 ብቻ የነበረ ሲሆን በአሁን ጊዜ በተንቀሳቃሽ ስልክ ብቻ 33 ሚሊዮን ደንበኞች አሉ፡፡ ከምንም የተነሳው የገጠር ቴሌኮም ሽፋንም በከፍተኛ መጠን አድጓል፡፡ የኒዮሊበራል ሃይሉና የውስጥ ተላላኪዎች የቴሌኮም ዘርፉን ወደግል እንድናዞር ጫና ለማሳደር ቢረባረቡም ዘርፉ ለህዝባችን ያለው ከፍተኛ ጥቅም በመረዳት ኢህአዴግ ጫናውን ተቋቁሞ የህዝባችንን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ችሏል። በመሆኑም መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማስፋት እየተጋ ያለውን ኢሕአዴግን ምረጡ፡፡
የከተሞቻችን ዕድገት በቀጣይነት በማፋጠን የነዋሪዎቻቸው ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ያለው ኢህአዴግን በመምረጥ የህዳሴ ጉዞአችን እናፋጥን!
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፦
ለዘመናት ተረስተው የነበሩ የሀገራችን ከተሞች በኢህአዴግ ትክክለኛ ፖሊሲና በህዝባችን ያላሰለሰ ጥረት በአሁኑ ጊዜ የፈጣን ዕድገታችን አካልና የህዳሴያችን የለውጥ ማዕከላት ወደመሆን ተሸጋግረዋል፡፡ ነባር ከተሞች ወደ አዲስ የለውጥ ንቅናቄ እንዲገቡና በከፊል በአዲስ መልክ ፈርሰው እንዲገነቡና አዳዲስ ከተሞች እንዲያብቡ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የአስተዳደር ማእከላት ሆነው የቆዩ ከተሞቻችንን ከኢንዱትሪ ልማት ጋር በማስተሳሰር ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጠርባቸው፣ የከፍተኛ ኮንስትራክሽን ማዕከላት እንዲሆኑና ለነዋሪዎቻቸው ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለማድረግ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎችም ውጤታማ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ ናቸው፡፡
የሀገራችን ከተሞች ዕድገትና የነዋሪዎቻቸው ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው ከገጠር ልማት ጋር በማስተሳሰር መሆኑን የሚገነዘበው ኢህአዴግ የገጠሩን ልማት የሚደግፉ ከተሞች በየእርከኑ እንዲቋቋሙ አድርጓል። በዘፈቀደ ሲካሄድ የቆየውን የከተሞች አሰፋፈርና አከታተም ግልፅ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመቅረፅና የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የከተሞች ፕላንና ደረጃዎች ምደባ በማካሄድ የሃገራዊ ልማትና ለውጥ ማዕከላት እንዲሆኑ በተደረገው ርብርብ አመርቂ ስኬቶች ማስመዝገብ ጀምረናል፡፡ አሁንም ለተሻሉ ስኬቶች እየተጋ ላለው ኢህአዴግ ድምፃችሁን በመስጠት የከተሞችን እድገት ያፋጥኑ፡፡
በማሕበራዊ ልማት ዘርፍ ፈጣንና ፍትሐዊ ዕድገት እያረጋገጠ ያለው ኢህአዴግን በመምረጥ የሀገራችን ህዳሴ እናረጋግጥ!
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፦
ኢህአዴግ  በማሕበራዊ ልማት ዘርፍ ያስመዘገባቸው ስኬቶች በበርካታ አለም አቀፍ መመዘኛዎች አመርቂ ናቸው። ኢህአዴግ የተከተለው ትክክለኛ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ሀገራችን የምእተ ዓመቱን ግቦች ከሚያሳኩ ጥቂት ሀገራት መካከል እንድትሰለፍ አስችሏታል። የትምህርት ተደራሽነት በማረጋገጥ ረገድም ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባሉ እርከን ፍትሐዊ በሆነ አኳኋን በመገንባት ስኬታማ ተግባራት ማከናወን የተቻለ ሲሆን ስራው በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። በዚህም ከ24 ሚልዮን በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ሲሆን ይህም የሀገራችን የህዳሴ ጉዞ ለማሳለጥ የሚያስችለን የሰው ሃይል እየገነባን እንደምንገኝ የሚያረጋግጥ ነው።
መከላከልን ማዕከል ያደረገው የኢህአዴግ የጤና ፖሊሲም ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው ነው። የመሰረታዊ ጤና አገልግሎት ሽፋንን በ1983ዓ.ም ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ በአሁኑ ጊዜ 100 ፐርሰንት ማድረስ ተችሏል። የዜጎች አማካይ በሕይወት የመኖር ዕድሜም ከ45 ወደ 64 አመት አድጓል፡፡ አሁንም ቀጣይ ስራና ርብርብ የሚያስፈልገን ቢሆንም የእናቶችና የህፃናት ሞት በመቀነስ ረገድም የኢህአዴግ መስመር ስኬታማ ነው። ኢሕአዴግ በመምረጥ ፍትሃዊ የማህበራዊ ዘርፍ ልማትን እንዲያረጋግጡ ኢሕአዴግ ጥሪውን ያስተላልፍላችኋል፡፡
አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ ሌት ተቀን የሚተጋውን ኢህአዴግን በመምረጥ የሀገራችን ፈጣን ዕድገት እናስቀጥል!
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፦
ብዝሃነታችን በአግባቡ ያስተናገደ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት በመቻላችን ሀገራችን ሁከትና ብጥብጥ በማይየለው የአፍሪካ ቀንድ ያለች የሰላምና መረጋጋት ደሴት መሆን ችላለች። ሰላም የአማራጭ ጉዳይ ሳይሆን የህልውናችን አንዱ አካል ነው ብሎ የሚያምነው ኢህአዴግ ሕዝባችን ተደራጅቶ የአካባቢውን ፀጥታ የሚያስጠብቅበት ሁኔታ በመፍጠራችን ከተራ ወንጀል መከላከል እስከ ፀረ ሽብርተኝነት ትግል አብሮን የሚሰለፍና በባለቤትነት የሚያንቀሳቀስ የሰላም ዘብ ሆኗል። የራሳችን ሰላምና መረጋጋት ከማረጋገጣችን በተጨማሪ የጎረቤቶቻችንን ሰላም በማረጋገጥ በኩል ባደረግነው አስተዋፆ በጎረቤቶቻችንና ሌሎች ወንድም ህዝቦች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አስገኝቶልናል።  
በአንፃሩ አንዳንድ የአገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ከመስራት ይልቅ ሁከትና ብጥብጥ ከሚሰብኩ ሃይሎች ጋር እጅና ጓንት ሆነው በመንቀሳቀስ የሀገራችን ሰላምና የህዝባችን ደህንነት ሲያውኩ ይታያሉ። በመሆኑም ኢህአዴግን በመምረጥ የፀረ ሰላም ሃይሎችን ሕልም በካርዳችሁ እንድታከሽፉ ድርጅታችሁ ኢህአዴግ ጥሪውን ያቀርባል።
ችግሮቹን ለመፍታት ብቃቱና ቁርጠኝነቱ በተግባር የተረጋገጠው ኢህአዴግን በመምረጥ ህዳሴአችን እናስቀጥል!
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፦
ኢህአዴግ የስራዎቹን አፈፃፀም በየምዕራፉ እየገመገመ ስሕተቱን ለማረምና ጥንካሬዎቹ ይበልጥ አጎልብቶ ለመቀጠል የሚያስችለው ዴሞክራሲያዊ ባህርይ ያለው ነው፡፡ ስሕተቱንም በግልፅ ለህዝብ አቅርቦ የሚያስተች፣ ከህዝቡ የሚቀርብለትን ተጨማሪ ሂስና ትችቶችንም ሳያቅማማ በመቀበልና በማረም ለበለጠ ልማትና ዕድገት የሚተጋ ህዝባዊ ድርጅት ነው። የሀገራችን ተቃዋሚዎች ይህ ነው የሚባል ጠጨባች የፖሊሲ አማራጭ ማቅረብ ሳይችሉና ለማቅረብም ብቃቱና ዝግጁነቱ ሳይኖራቸው ጥቃቅን ስሕተቶችን አጋንነው በማቅረብ በኢህአዴግ ጉድለቶች ላይ ሲንጠለጠሉ ይታያሉ። በመልካም አስተዳደር የሚስተዋሉ ችግሮች፣ የስራአጥነት ችግሮችን እና ሌሎችንም ኢህአዴግ ከህዝባችን ጋር በመሆን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚፈታቸው መሆኑን በድጋሜ ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል፡፡ ኢህአዴግ ምንጊዜም እራሱን በራሱ የማረምና ከተጨባጭ ተግባሩ እየተማረ የመሄድ ልምድ ያለው መሆኑን ህዝባችን ይገነዘበዋል።
ኢህአዴግን በመምረጥ የህዳሴ ጉዟችን እናስቀጥል!!

No comments:

Post a Comment