የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች!
ሀገራችን
ኢትዮጵያ የየራሳቸው ቋንቋ፣ ባህል፣ ስነልቦናና መልክዓ ምድራዊ አሰፋፈር ያላቸው ከ75 በላይ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም
የኃይማኖት ብዝሃነት ያለባት ሀገር ናት። ይሁንና ያለፉት ስርአቶች ብዝሃነትን የሚያስተናግዱ ባለመሆናቸው ሀገራችንና ህዝቦቿን ለአስከፊ
ችግሮች ዳርገዋቸው ነበር፡፡ በቅድመ ፌዴራሊዝም የነበሩት መንግስታት በኃይማኖትም ይሁን በቋንቋና ባህል የሚገለፁ ብዝሃነቶችን እንደ
ስጋት ይቆጥሩ የነበሩ በመሆናቸው የማንነት ጥያቄዎችን በማፈንና በኃይል ለማጥፋት በህዝቦች ላይ ከፍተኛ ጭቆና አድርሰዋል። የብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ገፍፈው ከባርነት ያልተናነሰ ጭቆና አድርሰውባቸዋል።
ሀገራችን
ለረጅም ዘመናት ብዝሃነትን ያከበረ ስርዓት መመስረት ባለመቻሏ ገናና የስልጣኔ ታሪኳ በእርስ በእርስ የመሳፍንቶች ሽኩቻና በህዝቦች
ላይ በደረሰ የአምባገነኖች ጭፍጨፋ ሊወድም ችሏል። በዚህም የከፍታ ዘመኗ አብቅቶ ታታሪ የነበሩ ህዝቦቿ አሳፋሪ የድህነት፣ የተመፅዋችነትና
የጉስቁልና ኑሮ ውስጥ ለመግባት ተገደው እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።
ገዥዎች
የሀገራችን ዋነኛ መገለጫ የሆነውን ብዝሃነትን በመጨፍለቅና በማፈን ላይ የተመሰረተ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሀገር፣ አንድ ኃይማኖት
የሚል አሃዳዊ የመንግስት ስርዓት በመፍጠር በህዝቦች ላይ አስከፊ ጭቆናና በደል አድርሰዋል፡፡ ገዥዎቹ ለወጡበት ብሔርም ጭምር ከሌሎች
ህዝቦች ባልተለየ መልኩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጭቆናዎች አድርሰዋል። የሀገራችን ህዝቦች ግን ብዝሃነትን ያልተቀበሉትንና ጭቆናና
ግፍ ያደረሱባቸውን ገዥዎች አሜን ብለው ሳይቀበሉ ታግለዋቸዋል፡፡ የሀገራችን አርሶ አደሮች፣ የከተማ ነዋሪዎች፣ ተማሪዎች፣ ምሁራንና
ሌሎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ጊዚያት ገዥዎችን በመታገል መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡ ይሁንና በኢህአዴግ እና አባል
ድርጅቶቹ ትክክለኛ የትግል መስመር ከመመራታቸው በፊት የነበሩ ትግሎች በአግባቡ የተደራጁና በመሪ ድርጅት ያልታገዙ ስለነበር ገዥዎችን
ሊያስወግዱ አልቻሉም፡፡
ኢህአዴግ ህዝባዊ አላማን በማንገብ የህዝቦችን ትግል በጽናት መርቶና ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሎ የዘመናት የህዝቦች ሰቆቃና ስቃይ ምንጭ የነበረውን ብዝሃነትን የማያከብር አምባገነናዊ ስርአት ከህዝቦች ጫንቃ እንዲወገድ አድርጓል፡፡ በኢህአዴግ መሪነት የተካሄደው ትግልም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብቶች ያለ ገደብ የተከበሩባት ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሊተመን የማይችል መስዋዕትነት የጠየቀ መሆኑ ወዳጅም ጠላትም የሚገነዘበው ነው። በኢህአዴግ መሪነት በተካሄደው ትግል በአፍሪካ ወደር ያልነበረውን የጦር ሰራዊት የያዘ የጭቆና አገዛዝ ማፈራረስ የተቻለው የትግሉ አላማ ግፍና ጭቆናን የማስወገድ ህዝባዊ ስለነበረ ነው፡፡ በወቅቱ እጅግ ወደተካረረ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው የብሄር ቅራኔ ሀገርን የመበታተን አደጋ ሳያስከትል የህዝቦችን የበላይነት ባረጋገጠ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲቋጭ ኢህአዴግ ወሳኝ የመሪነት ሚና ተጫውቷል።
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች!ኢህአዴግ ህዝባዊ አላማን በማንገብ የህዝቦችን ትግል በጽናት መርቶና ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሎ የዘመናት የህዝቦች ሰቆቃና ስቃይ ምንጭ የነበረውን ብዝሃነትን የማያከብር አምባገነናዊ ስርአት ከህዝቦች ጫንቃ እንዲወገድ አድርጓል፡፡ በኢህአዴግ መሪነት የተካሄደው ትግልም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብቶች ያለ ገደብ የተከበሩባት ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሊተመን የማይችል መስዋዕትነት የጠየቀ መሆኑ ወዳጅም ጠላትም የሚገነዘበው ነው። በኢህአዴግ መሪነት በተካሄደው ትግል በአፍሪካ ወደር ያልነበረውን የጦር ሰራዊት የያዘ የጭቆና አገዛዝ ማፈራረስ የተቻለው የትግሉ አላማ ግፍና ጭቆናን የማስወገድ ህዝባዊ ስለነበረ ነው፡፡ በወቅቱ እጅግ ወደተካረረ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው የብሄር ቅራኔ ሀገርን የመበታተን አደጋ ሳያስከትል የህዝቦችን የበላይነት ባረጋገጠ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲቋጭ ኢህአዴግ ወሳኝ የመሪነት ሚና ተጫውቷል።
የአምባገነናዊ
ስርአት መወገድን ተከትሎ የሀገራችን ህዝቦች የዘመናት ጥያቄ ሊፈታ የሚችል ስርአት መከተል የግድ ይል ነበር፡፡ በሀገራችን ተጨባጭ
ሁኔታ ብዝሃነትን በኃይል የመጫን አማራጭ የጥፋት መንገድ መሆኑ በተግባር የተረጋገጠ ስለነበር ብዝሃነትን የሚያከብር አማራጭ የወቅቱ
አንገብጋቢ ጥያቄ ነበር፡፡ የአሃዳዊና የተማከለ የመንግስት አወቃቀር የhገራችን ብዝሃነት የማያስተናግድ መሆኑም ባለፉት መንግስታት
በተጨባጭ የታየ ስለነበር የቁልፍ ችግራችን መፍቻ አማራጭ አልነበረም፡፡ የሀገራችን ህዝቦች ከግዳጅ አንድነት ወጥተው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ
መብቶቻቸው የተከበረባት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለመመስረት ለብዝሃነታችን እውቅና የሰጠና ይህንኑ የሚያከብር
ፌዴራላዊ ስርዓት መመስረት ወሳኝ ነበር። በመሆኑም ሁሉም ህዝቦች
ወደውና ፈቅደው የሚኖሩበትን ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በህገ መንግስታቸው አፅንተዋል።
የፌዴራሊዝም
ስርዓት በብዙ ሀገሮች የተለመደ ነው። ከአለም ህዝብ 40 በመቶው የሚይዙ ሀገራት የፌዴራሊዝም ስርዓት ይከተላሉ። በጣም ሰፊ ግዛት
ወይም ህዝብ ያለቸው ዴሞክራሲያው ሀገራት ከሞላ ጎደል የሚከተሉት የፌደራል ስርዓትን ነው፡፡ ህንድ፣ ካናዳ፣ ብሪታንያና አሜሪካ
የፌደራል ስርዓት ከሚከተሉ ሀገሮች ተጠቃሾች ናቸው።
የእኛን
የፌዴራሊዝም ስርዓት ከሌሎቹ የሚለዩት የራሱ ባህሪዎች ግን አሉት። ከእነዚሁ ባህሪያቱ በተለይ ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የራስ
እድል በራስ የመወሰን መብት ለማስከበር ያለው ቁርጠኛ አቋም አንዱ ነው። የእኛ ፌዴራሊዝም ለህዝቦች ማንነት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ
ነው። ይህ የማይዋጥላቸው ያለፈው ስርዓት ናፋቂዎች የሆኑት ትምክህተኞች የፌደራል ስርዓቱ ከጅምሩ ሀገር ይበታትናል በሚል አሃዳዊ
አገዛዙ እንዲቀጥል ያላደረጉት ጥረት የለም፡፡ በሌላ በኩል የኪራይ ሰብሳቢነትና የስግብግብነት ፍላጎታቸውን ለማርካት ዝግጁ የሆኑ
ጠባብ ኃይሎች በህዝቦች ትግል ተንኮታኩቶ የወደቀ ስርዓት ሲፈጥራቸው የነበሩ ችግሮች አሁንም የቀጠሉ በማስመሰል የህዝቦችን መብት
ከሃዲዱ ወጥቶ ለቅራኔና ቁርሾ እንዲውል ጥረት አድርገዋል፡፡ የትምክህት ኃይሉና የጠባብ ኃይሉ የፌደራል ስርዓታችን መበታተንን ሳይሆን
ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እየፈጠረ መሆኑ በተረጋገጠበት በአሁኑ ጊዜም የማስመሰያ ጭምብላቸውን እየቀያየሩ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን
ጥላቻ ያንፀባርቃሉ፡፡
የትምክህት
አመለካከት ወኪል ሆነው የሚንቀሳቀሱ የሀገራችን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ በህዝቦች ትግል የተናደውን የግዳጅ አንድነት በመናፈቅ የፌዴራል ስርዓቱን
በታኝና ሀገር አጥፊ ነው በማለት በሀሰት ሲተቹና ሲያጣጥሉ ቆይተዋል። የጠባብነት አመለካከት ወኪል ተቃዋሚዎችም ባለፉት ስርዓቶች
የነበሩ ችግሮቸ እንዳሉ በማስመሰል የፌደራል ስርዓቱ ላይ ሲዘምቱ ይታያሉ፡፡ ላለፉት 23 ዓመታት በሀገራችን የታየው እውነታ ግን
የሀገራችን ተቀዋሚዎች፣ ብዝሃነትን የተቀበለው የፌደራል ስርዓታችን የህዝቦችን የራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ
እንዳስቻላቸው ነው። ዛሬ የሀገራችን ህዝቦች ህገ መንግስታዊ የፌደራል ስርዓታቸው መብቶቻቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ ያረጋገጠላቸው
መሆኑን አምነው እጅ ለእጅ ተያይዘው የጋራ ፕሮጀክታቸው የሆነውን የኢትዮጵያ ህዳሴ ለማሳካት በመረባረብ ላይ ናቸው፡፡
ህገ
መንግስታዊ የፌዴራላዊ ስርዓታችን አጠቃላይ ዓላማ የህዝቦችን ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ የማስፈን እንዲሁም
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን የሚያፋጥን አንድ የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ መገንባት ነው። ፌዴራላዊ ስርዓታችን የዜጎች ህገ
መንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ አድርጓል። በህገ መንግስቱ በተደነገጉ አንቀፆች የህግ የበላይነት በማንም ሊጣስ እንደማይችል በግልፅ
በማስቀመጥ የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ መብቱን የሚጥስ ማንኛውም አካልም በህግ እንዲጠየቅ የሚያደርግ አሰራር ፈጥሯል።
ይህም ህገ መንግስትን በማክበር፣ በማስከበርና ለህጉ ተገዥ በመሆን እንዲፈፀም አድርጓል። የክልሎችና ብሔር ብሔረሰቦች ጥቅሞችን
ከማረጋገጥ አኳያም በህገ መንግስታችን አንቀፅ 89 ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሀገሪቷ የተጠራቀመ እውቀትና ሀብት ተጠቃሚ የሚሆኑበት፣
ሀብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የሚከፋፈልበት እንዲሁም ወደ ኋላ ለቀሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መንግስት ልዩ ድጋፍ የሚያደርግበት
አሰራር እንዲዘረጋ ደንግጓል። ከዚህ አኳያ በተሰሩ ስራዎች ክልሎች የመልማት እድል አግኝተው አቅማቸው እያደገተ በህዝቦቻቸው ኑሮ
ላይ የተሻለ ለውጥ እያመጡ መጓዝ ችለዋል። የሀገራችን ፌዴራሊዝም በፉክክር ላይ ሳይሆን በትብብር ላይ የተመሰረተ አብሮ የመልማትና
የማደግ አቅጣጫን የሚከተል በመሆኑ የህዝቦችን እኩል የመጠቀም መብት እያረጋገጠ ይገኛል። በትብብር ላይ የተመሰረተ መሆኑ በህዝቦች
ሁለንተናዊ እድገት የተገኘውን ስኬት ከፍ እንዲል አድርጎታል።
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፣
ፌዴራላዊ
ስርዓታችን ለህዝቦች እኩልነት፣ ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት የሰጠ ነው። አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባት ጉዞ
ያለ ፖለቲካዊ ተሳትፎና እኩልነት ስለማይረጋገጥ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በእኩል የሚያከብር ስርዓት እንዲመሰረት
አስችሏል። ፌዴራላዊ ስርዓታችን እነዚህ አጠቃላይ መብቶች እንዲከበሩ በማድረጉ በሀገራችን ላለፉት 23 ዓመታት አስተማማኝ ሰላም
ማስፈን ተችሏል። ለሰላም እጦትና አስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት መንስኤ የነበሩ የህዝቦች መብቶች ያለማክበር ችግር በመሰረቱ በመፈታቱ
በሀገራችን አስተማማኝ ሰላም ሰፍኗል። በህዝቦች መካከል የሚነሱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበት አማራጭ በማስቀመጡም ሰላማዊና
ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች መጎልበት ችለዋል።
የፌደራል
ስርዓታችን በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ህዝቦች ዋነኛ ጠላታቸው በሆነው ድህነት ላይ እንዲዘምቱ አስችሏቸዋል፡፡ በኢህአዴግ ትክክለኛ
ፖሊሲና ስትራቴጂ በመመራትም ፈጣን፣ ተከታታይና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ላይ ናቸው፡፡ ፌዴራላዊ ስርዓታችን የህዝቦችን
ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሰረተ ሰፊ ማህበራዊ ልማትና የመሰረተ ልማት እድገት ያስመዘገበም ነው። አንድ ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ በመገንባት
ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ የህዝቦችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡና የህዝቦችን ትስስር ያጠናከሩ ዘርፈ ብዙ የመሰረተ ልማት ግንባታቸው
ተካሂደዋል፡፡ በመካሄድም ላይ ናቸው፡፡
በማህበራዊ
ልማት በትምህርትና በጤና ዘርፎች እየተመዘገበ ባለው ውጤት የዜጎች ተጠቃሚነት በእጅጉ ጨምሯል። የፌደራል ስርዓታችን ስኬቶች በድምሩ
ሲታዩ ዛሬ የሀገራችን ህዝቦች ተባብረው የሚያድጉበትና አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ገንብተው ታላቅ ህዝብና ሀገር የሚሆኑበት እድል
በእጃቸው መሆኑን በተጨባጭ አረጋግጠዋል። ብዝሃነትን ባከበረ ፌዴራላዊ ስርዓት መጓዝ በመቻላቸውም የቀደመውን የሀገራችን ስልጣኔ
የማስመለስ ጉዞ ጀምረዋል። ዛሬ የሀገራችን ህዝቦች ከጎረቤት ሀገር ህዝቦች በጋራ የመልማት ተጨባጭ እንቅስቃሴ የጀመሩና ከእራሳቸው
ለጎረቤቶቻቸውና ለሌሎች ህዝቦች ሰላም መረጋገጥ እየተጉ ይገኛል፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝቦች ልዩነታችን ውበታችን አንድነታችን ጥንካሬያችን
በሚለው መርሃቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው የጋራ ሀገራቸውን እየገነቡ መገኘታቸው ብዝሃነትን ያከበረ ፌደራላዊ ስርአት የቁልፍ ችግሮቻችን
መፍቻ ሁነኛ መሳሪያ እንደሆነ አሳይቷል፡፡
የፌደራል
ስርዓታችን ለስኬት የበቃው የሀገራችን ህዝቦች አምነው ስለተቀበሉትና በኢህአዴግ ቁርጠኛ አመራር ሰጭነት በሁሉም መስኮች ተሳትፎአቸው
ስለተረጋገጠ ነው፡፡ የፌደራል ስርዓታችን አሁን ከደረሰበት ደረጃ የደረሰው ኢህአዴግ በበሳል ሃሳቦቹ እየመራ በየጊዜው ለሚያጋጥሙ
ችግሮች መፍትሄ እየሰጠና እራሱን ለቀጣይ ለውጥ እያዘጋጀ በመቀጠሉ ነው፡፡ አሁንም በፈደራል ስርዓታችን የሚታዩ ከማስፈጸም አቅም
ውስነት ጋራ የተያያዙ ችግሮች ለመፍታት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል መፍታት እንደሚያስፈልግ ኢህአዴግ ያምናል፡፡
ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የሚነጩ አልፎ አልፎ የህዝቦችን መብቶችን የሚጋፉ ድርጊቶችን ለማረም ኢህአዴግ ከመላ ህዝቡ
ጋር በመሆን የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል፡፡
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች!
ከውድቀታቸው
የማይማሩት የድሮ ስርዓት ናፋቂ የሆኑት የሀገራችን ተቃዋሚዎች ዛሬም ከ23 የሰላምና የእድገት ዓመታት በኋላ የፌደራል ስርዓቱ የህዝቦችን
መብት ማክበሩ ሀገር ይበትናል የሚለውን መሰረተ ቢስ ውንጀላቸውን አላቆሙም፡፡ የሀገራችን ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያ ህዝቦች ሀቀኛ ትግል
በተግባር በውጤት እያደገና እየጎለመሰ የመጣበትና ኢህአዴግ የታገለለት የህዝቦች የበላይነትና ወሳኝነት የነገሰበት ስርዓት ነው።
ብዙ ብሔሮች፣ ብዙ ቋንቋዎች፣ ብዙ ባህሎችና ኃይማኖቶች ያሏቸው የሀገራችን ህዝቦች እነዚህ እሴቶቻቸው በእኩል እንዲከበሩ መጠየቅ
ቀርቶ መብቶቻቸውን ማሰብ የማይችሉበትን የአምባገነኖች ስርዓት እንዲቀየር ያደረገው ብዝሃነትን ያከበረው ፌዴራላዊ ስርዓታችን መሆኑን
ተቃዋሚዎችም ሊክዱት የማይቻላቸው ሀቅ ነው።
የሀገራችን
ተቀዋሚዎች ለምትገነቡት ስርዓት ያለችሁ አማራጭ ምንድነው ሲባሉ አንዳንዶቹ በፌደራል ስርዓታችን የመጣውን ለውጥ ፊት ለፊት መካድ
ሲከብዳቸው አልሸሹም ዘወር አሉ እንዲሉ ፌደራሊዝምን እንከተላለን ግን አከላለሉን መልክዓ ምድራዊ እናደርገዋለን ይላሉ፡፡ ይህ አማራጭ
የህዝቦችን ማንነትና መብት የማይቀበለው ያው ያለፉት አገዛዞች አቋም በፌደራሊዝም አስመሳይ ጭምብል ተሸፍኖ የቀረበ ነው፡፡ አንዳንዶቹ
ደግሞ አማራጭ ብለው የሚያቀርቡት ከየትም ቃርመው የሰበሰቡትን ወክለው የቆሙለትን የትምክህተኞችና የጠባቦችን የተሳሳተና የበሬ ወለደ
ወሬን ነው፡፡ ለዚህም ነው የሀገራችን ተቀዋሚዎች አማራጭ ብለው የሚያቀርቡት ሃሳብ ያለፉት ስርዓቶችን መልሶ ለማምጣት ያለመ ለሀገርና
ለህዝብ የማይጠቅም የጥፋት መንገድ ነው የምንለው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ባለፉት 23 አመታትም በኢህአዴግ መሪነት መብቶቻቸው ተከብሮ
እጅ ለእጅ ተያይዘው ሀገራችንን ወደ ነበረችበት የስልጣኔ ማማ የሚያስወጣ የህዳሴ ጉዞ ጀምረው በስኬት ታጅበው እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡
ለዚህም ያበቃቸው ትክክለኛው የኢህአዴግ አብዮታዊና ዴሞክራሲያዊ ወይም ልማትዊ ዴሞክራሲ መስመር መሆኑ የሀገራችን ህዝቦች እንደሚገነዘቡት
ኢህአዴግ ያምናል፡፡
ለዚህም
ነው የኢህአዴግ መስመር ብቸኛው የህዳሴ መስመር ነው የምንለው፡፡
ለዚህም
ነው ኢህአዴግ መምረጥ ፈጣኑንና ቀጣይነት ያለው ልማትን፣ አስተማማኝ ሰላምን እና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲን ማስቀጠል ነው የምንለው፡፡
ኢህአዴግ
የሚያስተላልፋቸውን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶች ከቴሌቪዥን፤ ሬዲዮና ጋዜጣ በተጨማሪ በድረ ገፃችን www.eprdf.org.et እና በፌስቡክ ገፃችን EPRDF
official ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
No comments:
Post a Comment