EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Sunday 14 September 2014

በየምሽቱ ከጎጆው ደጃፍ



በየምሽቱ ከጎጆው ደጃፍ፤ የአርሶ አደሮች እንጉርጉሮ
የስነቃል ምንጩ፤ የስነ ግጥም መፍለቂያው ገጠር ነው፡፡ አርሶ አደሮች እርሻ አብቅተው ለበሬዎቻቸው ገለባና ጭድ በግርግም ውስጥ አፍስሰው በርኖስ ወይ ጋቢ ተከናንበው የሚያቀነቅኑት ቅኔ፤ የሚወጣቸው ዜማ ተፈጥሯዊ ውበት የተላበሰ ነው፡፡ ብሶታቸውን በስነ ግጥም እንጉርጉሯቸውን በዜማ በምሽት ሲያወርዱት ልብ ይነካል፤ ይመስጣል፡፡ ጢስ ከሚጤስበት ጎጇቸው ደጃፍ ላይ በምሽቱ አረፍ ሲሉ እልሃቸውን በወርቃማው ዘይቤያቸው ለማቲዎቻቸው ያወርሳሉ፡፡ በተለይ ኢሕአዴግ ደርግን ደምስሶ የወሎና የጎንደር አካባቢዎች የነፃነት አየር መተንፈስ እንደጀመሩ የአርሶ አደሮች የቅኔ አዝመራ በእጅጉ አብቦ ነበር፡፡ ለቅምሻ ያህል እነሆ፤
የደርግ አስከፊ ስርዓት ወድቆ የነፃነት አየር መተንፈሳቸውን ለመግለፅ እንዲህ ብለዋል፤
የጭቆና ቀንበር ከብዶ በላያችን
በግብር በጉቦ አልቆ ንብረታችን
በጦር በሰፈራ አልቆ ወገናችን
መጣልን ኢሕአዴግ የነፍስ አባታችን፡፡

ለደርግ የቀይ ሽብር ዘመቻ ደግሞ፤
ለገዥ መደቦች ደንታ ለሌላቸው
እዳ በዝቶብናል ይቀነስ ቢሏቸው
እንኳን የመፍትሄ መልስ ሊሰጧቸው
ባደባባይ መሃል ቀይ ሽብር መቷቸው፡፡
የሚል ስንኝ ሰፍሮለት ነበር፡፡ 1977 የድርቅ ወቅት የኢሠፓ ሹማምንት የእርዳታውን እህል ሲዘርፉ በግላጭ የተመለከተ አርሶ አደር ትዝብቱን 6 ስንኝ ቋጥሮ ጨርሶታል፡፡
ርሃብ ፀንቶብን በሰባ ሰባት
እርዳታ ቢመጣ ባማራ ሳይንት
ሳያሳዝናቸው የፍጥረቱ እልቂት
የኢሠፓ አባላት በስንዴው ዱቄት
እያለቀ ሕዝቡ ቤት አሰሩበት
ውስኪ ጠጡበት፡፡
ጉቦ ሲበሉ ከርመው ኢሕአዴግ ሲመጣ የሹመት መንደራቸውን ጥለው በፈረጠጡ ባለስልጣኖች ላይ ደግሞ አርሶ አደሩ እንዲህ ሲል አላግጦባቸው ነበር፡፡
የኢሠፓ አባላት አነምስ ቀበር
የሰው ፊት እያዩ ትልቅ አይከበር
የሚመለከቱት እጅ ብቻ ነበር፡፡
ለጭቁን አይራሩ ለድሆች አይረዱ
በየመስሪያ ቤቱ ሰውን ሲያዋርዱ
ብር ብር ሲሉ በጉቦ ሲፈርዱ
እዩት ምኞች አይቀር ብር ብለው ሄዱ፡፡

ሳይሰሩ ሳይለፉ ሕዝቡን ገፈው ገፈው
ኢሠፓ ነን ብለው እነሱው ለፍልፈው
እግራቸውን እንጨት ድንገት ቢያነቅፈው
እንዴት ብለው ሄዱ እንቁላል ታቅፈው
ኢሕአዴግ በጥይት ቢያሳጣው መድረሻ
ተሯሯጠ ደርጉ እንዳበደ ውሻ፡፡
እንዲያም ሆኖ የደርግ ባለስልጣናት አምልጠው እንደማይቀሩና ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው በተለመደው ውብ ልሳኑ አርሶ አደሩ ያስጠነቅቅ ነበር፡፡
አጥንታችን ሲቀር ስጋችን ተልጦ
ጅማታችን ሲቀር ደማችን ተመጦ
መናገር ቀርቶብን ቋንቋችን ተረግጦ
የት ነው የሚያመልጠን ደርጉ ተሯሩጦ፡፡
ወጣት በጦርነት እንደ ጥሬ ታፍሶ
የእናት የአባት እንባ እንደ ውዮ ፈሶ
እንግዲህ መንግስቱ አይመጣም መልሶ፡፡

እንኳን መሪ አግኝተን ትጥቃችን ሲሟላ
ደርግን ለመደምሰስ ይህን የሰው በላ
እንታገላለን በድንጋይ በዱላ፡፡
ደርግ የወሎና የጎንደር አካባቢዎችን ለቆ የወጣ ሰሞን በሄሊኮፕተር የሚበትናቸውን የቅስቀሳ በራሪ ፅሁፎች አርሶ አደሩ አላግጦባቸዋል፡፡ ለእነሱም ቢሆን የፈገግታ ቅኔ አላጣላቸውም፡፡ እንዲህ ሲል፤
መንግስቱ ሲዳከም ሲታየው ድቀት
አይሉት ሰላምታ አይሉት ናፍቆት
ይነሰንስ ጀመር ብጣሽ ወረቀት
አንዳትቀበለው ሕዝቡ ንቃበት፡፡
ደብዳቤስ ለመፃፍ የኔም ልብ ይመኛል
ታዲያ ወረቀቱን ማን ያደርስልኛል?

አትጨነቅ ደርጉ አይሸበር ሆድህ
አትርጭ ወረቀትህን በወዲያ በወዲህ
እጅን የሚያወጣው እጅ ነው እንግዲህ
ኢሕአዴግ ላይተውህ እኛም ላንሰድህ፡፡

ምንጭ፤ ሶረኔ የግጥም መድብል፤ ሁለተኛ እትም

No comments:

Post a Comment