በልጅ አኪናሆም
በአለማችን ውስጥ ከ194 በላይ ሀገራት እውቅና አግኝተው ህዝባቸውን እያስተዳደሩ ይኖራሉ። እነዚህን ሀገራት ለማስተዳደር እድሉን ያገኙ አንዳንድ መሪዎች ለህዝባቸው ጠብ የሚል ነገር ሳይተዉ ለራሳቸው እንደባዘኑ፤ ሀገራቸውን በልማት ወደ ፊት መግፋት ሳይችሉ ያልፋሉ። ሌሎች ደግሞ ለህዝባቸው ሰርተው የተመዘገበውን ልማታዊ ለውጥም በአይናቸው ተመልክተው ይቺን አለም ይሰናበታሉ። ጥቂቶች ግን ለህዝባቸው እንደባተሉ፤ ከሀገራቸው አልፈው አለምአቀፋዊ ተፅዕኗቸው ድንበር ሳይገድበው አሻራቸው በጉልህ የሚታይ ሆኖ እናገኘዋለን። ለዚህ አገላለፄ የቀድሞው የሀገራችን ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡ አቶ መለስ ብዙ በሚሰሩበት እድሜያቸው ከአጠገባችን የራቁ ቢሆንም አይረሴና ዘመን ተሻጋሪ ስራቸው ዛሬም ነገም የሚታወሱ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህንንም እንኳን እኛ ኢትዮጵያውያን መልካምነታቸውን ማጣጣም የቻልነው ይቅርና የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ታላላቅ ሰዎች አቶ መለስ አይረሴ መሪ መሆናቸውን ደጋግመው መስክረውላቸዋል፡፡ ስለእርሳቸው የተባሉትን ነገሮች በሙሉ መዘርዘሩ አዳጋች ቢሆንም በወፍ በረር ጥቂቶቹን ላስቃኛችሁ፡፡
በአለማችን ውስጥ ከ194 በላይ ሀገራት እውቅና አግኝተው ህዝባቸውን እያስተዳደሩ ይኖራሉ። እነዚህን ሀገራት ለማስተዳደር እድሉን ያገኙ አንዳንድ መሪዎች ለህዝባቸው ጠብ የሚል ነገር ሳይተዉ ለራሳቸው እንደባዘኑ፤ ሀገራቸውን በልማት ወደ ፊት መግፋት ሳይችሉ ያልፋሉ። ሌሎች ደግሞ ለህዝባቸው ሰርተው የተመዘገበውን ልማታዊ ለውጥም በአይናቸው ተመልክተው ይቺን አለም ይሰናበታሉ። ጥቂቶች ግን ለህዝባቸው እንደባተሉ፤ ከሀገራቸው አልፈው አለምአቀፋዊ ተፅዕኗቸው ድንበር ሳይገድበው አሻራቸው በጉልህ የሚታይ ሆኖ እናገኘዋለን። ለዚህ አገላለፄ የቀድሞው የሀገራችን ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡ አቶ መለስ ብዙ በሚሰሩበት እድሜያቸው ከአጠገባችን የራቁ ቢሆንም አይረሴና ዘመን ተሻጋሪ ስራቸው ዛሬም ነገም የሚታወሱ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህንንም እንኳን እኛ ኢትዮጵያውያን መልካምነታቸውን ማጣጣም የቻልነው ይቅርና የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ታላላቅ ሰዎች አቶ መለስ አይረሴ መሪ መሆናቸውን ደጋግመው መስክረውላቸዋል፡፡ ስለእርሳቸው የተባሉትን ነገሮች በሙሉ መዘርዘሩ አዳጋች ቢሆንም በወፍ በረር ጥቂቶቹን ላስቃኛችሁ፡፡
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርና የቤኒን ፕሬዚዳንት ቦኒ ያያ የአቶ መለስ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ ለአፍሪካና ለአለም የነበራቸውን አስተዋፅኦ ሲናገሩ “ለአፍሪካ ሁለተናዊ ነፃነትና ብልፅግና የታገሉ በዚህ ድንቅና ወደር የማይገኝለት አስተዋፅኦም የአፍሪካ ህብረት የተመካባቸው የፓን አፍሪካኒስት ኃይል” በማለት ገልፀዋቸው ነበር። ሊቀመንበሩ አቶ መለስ አፍሪካ የራሷ የፖሊሲና አማራጭ የእድገት መስመር እንዲኖራት ለማድረግ ብዙ ሞግተዋል፤ ሳይሰለቹ ለማስረዳትና ለማሳወቅ ደፋ ቀና ብለዋል ነበር ያሉት። በበርካታ አለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካን ልኡካን ቡድን በመምራትም አፍሪካን ወክለው በቡድን 8፤ በቡድን 20፤ በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድሮች፤ በአፍሪካ ቻይና፤ አፍሪካ ህንድና የአፍሪካ አውሮፓ ብሎም የአለም የኢኮኖሚ መድረኮች ላይ በመሳተፍ የሀገራቸውና የአፍሪካ መብት እንዲጠበቅና ባንዲራችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ማድረግ ችለዋል በማለት ነበር ቦኒ ያያ ስለአቶ መለስ ምስክርነታቸው የሰጡት።
ለአፍሪካ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በተመለከተ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሚሶቬኒም ይህን አሉ “ የኔፓድ ሊቀ መንበር ሆነው ያገለገሉት መለስ ዜናዊ አፍሪካ የእድገት ማዕከል ሆና እንድትወጣ ያስቻሉ መሪ ናቸው” በእርግጥም ከአድዋ የነፃነት መንደር ብቅ ያሉት የያኔው ጨቅላው መለስ አድገውና ተመንድገው ሀገራቸው በልማት ጎዳና እንድትራመድ ከማስቻል አልፈው ለአፍሪካውያን የልማት መፍትሄ ይሆን ዘንድ የኔፓድን ሀሳብ በማመንጨትና በመምራት ብዙ ተራምደዋል፤ ብዙ ሰርተዋል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጃኮቭ ዙማ ደግሞ በአቶ መለስ ሞት ላይ ተገኝተን እየሰጠነው ያለነው ክብርና አድናቆት በህይወት ስለተለየን ብቻ የምንናገረው አይደለም በማለት አፅንኦት በመስጠት ንግግራቸውን ጀምረዋል። “ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በህይወት ዘመናቸው ለሚሊዮን አፍሪካውያን እና ለአለም ህዝቦች ህይወት መሻሻል ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ስናከብረው እንኖራለን” ሲሉም ዙማ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። አቶ መለስ ተጋባዥ በሆኑባቸው አለም አቀፍ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተገኝተው የሚሰጧቸው ገንቢ ትችቶች፤ የሚያቀርቧቸው የመፍትሄ አማራጮች፤ የቃላት አጠቃቀማቸው፤ የመሪነት ግርማ ሞገሳቸው፤ እንግዳ አቀባበላቸው፤ ፈገግታቸውና ሰው አክባሪነታቸው በሁሉም ሰው ልብ ውስጥ እንዲታወሱ የሚያደርጋቸው ነውና የህልፈተ ህይወታቸው ዜና መሰማት ለእኛና ለበርካታ ሃገራት መሪዎች ሀዘናችንን መሪር አድርጎታል። በእለተ ህረፍታቸው ጃኮቭ ዙማ ያደረጉት ንግግርም ይህን ነው የሚያመላክተው፡፡ “ማንኛውንም ችግር በፅናት ለማለፍ በወኔ የተሞላ ምሁራዊ እሳቤውና ጥበቡ ለማንኛውም ችግር መፍትሄ የሚያመጣ ታላቅ ባለራዕይ ነው። ይህንን ሰው አህጉራችን በማጣቷ የተፈጠረውን ክፍተት ሁላችንም ለመሙላት መረባበር አለብን” ነበር ያሉት፡፡ አቶ መለስ አንድ ቢሆኑም እንደ ብዙ ማሰብ፤ እንደ ብዙ መስራት፤ እንደ ብዙ መጣርና ለውጥ ማምጣት የቻሉ ፅኑ መሪ ናቸው። ለዚህም ነው ኢትዮዽያውያን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ መሪያቸው የልባቸውን ከመናገር ያልተቆጠቡት።
ባለፉት 3 ዓመታት ነፃነቷን የተቀዳጀችው ደቡብ ሱዳን በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ሞት ብሄራዊ የሀዘን ቀን ያወጀችው የታላቁን መሪ ህልፈት መራር መሆኑን በመገንዘብ ነበር። የአዲሲቷ ሀገር መሪ ሳልቫኪር ማያርዴትም “የወጣትነት ጊዜውን በነፃነት ትግል ያሳለፈው መለስ የታላቋ ሀገር ኢትዮዽያ መሪ ከሆነ በኋላ ባለው ብሩህ አዕምሮ ምክንያት ከፖሊሲ አውጪዎች፤ ከዲፕሎማቶችና ከምሁራን ጋር ለመወያየት ሁሌም ዝግጁ ነው።” ሲሉ አቶ መለስን በአጭር ቋንቋ ገለፁ፡፡ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር አቶ መለስ በታላላቅ ሀገራት ጉባኤዎች እንዲሳተፍ ይጋበዝ የነበረው የታላቅና ታሪካዊ ሀገር መሪ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የትልቅ ብሩህ አዕምሮ ባለቤት መሆኑና የእርሱ ማለፍ ትልቅ ጉዳት፤ ሁሌም የሚያንገበግብና ቁጭት ውስጥ የሚከት ነው ሲሉም ህልፈታቸው የፈጠረባቸውን የሀዘን ስሜት በምሬት ገለፁ። አቶ መለስን በቅርበት እንደሚያውቋቸው የሚያረጋግጥ እማኝነት የሰጡት ሳልቫኪር “በፍትህ፤ በነፃነት እና በልማት ላይ የሚነሱ ችግሮችን ለመጋፈጥ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በምንም መልኩ እጅ የሚሰጥ አይደለም። ችግር በሚፈጠርበት ወቅት በርካቶች ምን ማድረግ አለብን ብለው ግራ ሲጋቡ መለስ በፍጥነት ትክክለኛ የመፍትሄ እርምጃ ያፈልቃል” ሲሉም ሳልቫኪር የአቶ መለስን መፍትሔ አመንጭነት አረጋገጡ፡፡ አዎን! አቶ መለስ በትግል ወቅትና በመሪነት ዘመናቸው ያረጋገጡት ይህንን ነው፡፡ በልማትና በነፃነት ጉዳይ የማይደራደሩና ለምርጫ እንኳን የማያቀርቡ ብልህና ሩቅ አሳቢ መሪና ነበሩ።
የሀገራቸውን ዙሪያ መለስ ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ለበርካታ አመታት በጥናትና ምርምር እየታገዙ ለአዲሲቷ ኢትዮዽያ የሚሆኑ ፖሊሲዎችን፤ ስትራቴጂዎችንና ፕሮግራሞችን በማመንጨት ወደ ተግባር አስገብተዋል። ሀገራቸውንና አለምን በተሻለ ለመረዳትም የእድሜ ዘመናቸውን በማንበብና ተማሪ በመሆን ማለፋቸው የተሻለች አለምና ሀገር እንዲኖር ስለሚፈልጉ መሆኑን የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቡ ኤምቤኪ ጥልቅ ሀዘናቸውን በገለፁበት ወቅት ተናግረዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሱዛን ራይስ በተከፋው አንደበታቸው፤ በተስረቅራቂውና ቢደመጥ በማይሰለቸው ለዛቸው መለስ “በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት መሆኑ ህይወቱን በሙሉ ራሱን በማስተማርና በማብቃት ያመጣው እንደሆነና ይህን እውቀቱንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሙሉ ጊዜውን ለሀገሩ ያዋለ ግን ደግሞ ራሱን የማይወድ ለህዝብ የኖረ መሪ” ሰሊ ስለታላቁ መሪ ተናግረዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ጆሴ ማኑኤል ባሮሶ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ለአፍሪካ የዋሉት ውለታ ላቅ ያለ ነበር ለዚህም ትልቅ ክብር የነበራቸው መሪ ሲሏቸው፤ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ደግሞ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሙሉ ኃይላቸውን ሲጠቀሙና ሲጥሩ የነበሩ፤ ከሀገራቸው አልፈውም ጠንካራና የተባበረች አፍሪካን ለመፍጠር በታማኝነትና ከልብ በመነጨ ፍቅር በመስራት ምስጋና የተቸራቸው መሪ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የተረጋጋችና የበለፀገች አህጉር ለመፍጠር አፍሪካውያን ከእርሳቸው እውቀትና ልምድ ለመቅሰም በተነሱበት ወቅት ማረፋቸው ሀዘናችንን ጥልቅ አድርጎታል ሲሉም ህልፈተ ህይወታቸው ልባቸውን እንደነካው ገልፀው ነበር።
ቶኒ ብሌር፤ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ፤ ኮፊ አናን፤ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ፤ የሶማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት አህመድ መሀመድ፤ አሜሪካዊው ቢሊየነር ቢል ጌትስ፤ የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ኸርነስት ቤይኮሮማን፤ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖልካጋሜ፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፤ የተባበሩት መንግስታት ድረጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪ-ሙን፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ የኬንያው ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ፤ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን፤ የላይቤሪያዋ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰንና ሌሎች ያልጠቀስኳቸው የሀገራት መሪዎች በአንድ ድምፅና በአንድ ምልከታ ስለ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የመጠቀ አስተሳሰብና የሀሳብ ልዕልና መስክረዋል፡፡ ስለ ብሩህ አዕምሯቸው፤ ፓን አፍሪካኒስትነታቸው፤ ለሚሰነዘሩ ጥያቄዎች የሚሰጧቸው አጥጋቢና አሳማኝ መልሶቻቸው፤ አንደበተ ርቱዕነታቸው፤ ሀገራቸውን ከድህነት ለማላቀቅ የተከተሏቸው የልማት መስመሮች፤ ልማትን፤ ሰላምንና ዴሞክራሲን የሁሉም ነገር መነሻም መድረሻም አድርገው መከተላቸው፤ በአየር ንበረት ለውጥ ልዩ ተደራዳሪ ሆነው መቅረባቸው፤ ባለራዕይነታቸው በቻሉት ሁሉ አገላለፅ ብዙ እጅግ ብዙ ብለዋል።
በእርግጥም አቶ መለስ የሀገራት መሪዎች ከገለጿቸው በላይ የእውነት የህዳሴ መሪ ነበሩ።
የአቶ መለስ ህልፈተ ዜናቸው ከታወጀ በኋላ የአለም አቀፍ በርካታ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ከጫፍ ጫፍ ተቀባብለው የዘገቡላቸው በእርግጥም ለህዝብ የኖሩ፤ አደባባይ የወጣ፤ በአይን የሚታይ ሚዛን የሚደፋ አሳማኝ የልማት ስራን እየሰሩ ግን ደግሞ ጉዟቸውን ሳይጨርሱና የአዕምሯቸውን ልቀት ጫፍ ሳይደርሱ፤ የሀገርና ለአለም የሚጠቅመው ማንነታቸው ያለ ጊዜው መገደቡ አስቆጭቷቸዋል።
የአቶ መለስ ህልፈተ ዜናቸው ከታወጀ በኋላ የአለም አቀፍ በርካታ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ከጫፍ ጫፍ ተቀባብለው የዘገቡላቸው በእርግጥም ለህዝብ የኖሩ፤ አደባባይ የወጣ፤ በአይን የሚታይ ሚዛን የሚደፋ አሳማኝ የልማት ስራን እየሰሩ ግን ደግሞ ጉዟቸውን ሳይጨርሱና የአዕምሯቸውን ልቀት ጫፍ ሳይደርሱ፤ የሀገርና ለአለም የሚጠቅመው ማንነታቸው ያለ ጊዜው መገደቡ አስቆጭቷቸዋል።
ታዋቂው ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ፤ሱዳን ትሪቢዩን፤ዘጋርድያን፤ዴይሊ ስታር፤ቢቢሲ፤ዘ ቴሌግራፍ፤ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያን፤ኒውስቫይን፤ቪኦኤ፤ ፋይናንሻል ታይምስ እና ሌሎች በርካታ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ አይረሴውና የህዝብ ልጅ ስለሆኑት መሪያችን በተባ ብዕራቸው፤ በአንደበታቸው፤ በገላጭ የዜና ዘገባቸው፤ በሰበር ዜናቸው፤ በልዩ ፕሮግራሞቻቸውና በትንታኔዎቻቸው ስለ አስደንጋጩና ቀስም ሰባሪው የመሪያችን ህልፈት ለአለም አሰምተዋል።
አለም ኢትዮጵያ ለየት ባለ እውቀትና የአመራር ፍልስፍና ይመራት የነበረውን መሪዋን አጣች አሉ፤ አፍሪካ ተደራዳሪዋን አጣች፤ የላቀ አዕምሮ ባለቤቷን፤ ሀገራቸውን ከእርስ በእርስ ጦርነት ፍርስራሽ አውጥተው በአፍሪካ እጅግ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እንድታሳይ ያደረጉ፤ በህመማቸው ላይ ሆነው እንኳ በግጭት ውሰጥ የሚገኙ ሀገራትን የማሸማገልና የማደራረር ሂደት ያላቋረጡ፤ የፖለቲካ መረጋጋት የፈጠሩ፤ ለአፍሪካ አሳቢ መሪ፤ ለአፍሪካ ራዕይ የቆሙ፤ የምስራቅ አፍሪካ የሰላም አራማጅ ሲሉ አወድሰዋቸዋል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ የበሰሉ የፖለቲካ ሰው፤ ለአፍሪካ ጥብቅና የቆሙ፤ አስገራሚ የማስታወስ ችሎታ የነበራቸው፤ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው ምንም አይነት ፈታኝ ጥያቄ ቢቀርብላቸው ፊታቸው ላይ ፈገግታ የማይጠፋባቸው፤ በስራቸው ጠንቃቃና ሰዓታቸውን የማያዛንፉ፤ ራሳቸው ትክክል ነው ባሉት የስነ ልቦና መርህ ያመኑና በዚያው የሚገፉና በቅኝ ግዛት ድሪቶ ስር ሲማቅቁ ከኖሩ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች መካከል ጎላና ለየት ብለው የታዩ መሪ ሲሉ በአራቱ የዓለማችን አቅጣጫዎች የሚገኙ ሚዲያዎች ህልፈታቸውን ለመሪው ካላቸው አድናቆት ጋር ለአለም ህዝቦች አድርሰዋል።
በእርግጥም ታላቁና አርቆ ተመልካቹ መሪ አቶ መለስ አርፈዋል። ለኢትዮዽያውያን በተለይ ለዓለማችን ጭቁንና ድሃ ህዝቦች ደግሞ በአጠቃላይ የሚሆን ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቻቸው ግን አንገታችንን ቀና አድርገን እንሄድ ዘንድ መንገድ ሆኖናል። ታላቁ መሪ የሀገራችህ የህዳሴ መሰረት የሚጣልበት ፅኑ መሰረት በግልፅ አሳይተውንና አስተምረውን አልፈዋል። አዎን ዛሬ በአቶ መለስ ለማመን ከራሳችን በላይ እማኝ የሚሆን ሌላ ማንም የለም። ከስራ ስብዕናቸው እስከ ተምሮ አስተማሪነታቸው ሙሉ የእድሜ ዘመናቸውን ለህዝብና ለሀገራቸው ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ፤ ድህነትን አምርረው በመጥላት በድህነት ላይ የሚደረገው ትግል ከፍ እንዲል ያደረጉ፤ በኢትዮዽያ የነገስታትና መንግስታት ታሪክ ውስጥ የተለየና ለንፅፅር የማይቀርብ ስራን ሰርተው ያለፉ ልዩ ስብእና የነበራቸው የቁርጥ ቀን መሪ ነበሩ። ይህ ጎልቶ የወጣው ማንነታቸውም በእኛ በኢትዮጵያውያን፣ በአፍሪካውያንና በመላው ዓለም ህዝብ ዘንድ ሲወሳና ሲዘከር ይኖራል፤ እንርሳው ብንል እንኳን እውነታው በራሱ መንገድ እየተመላለሰ እንዳንረሳው ያስገድዳልና!
No comments:
Post a Comment