(በወጋገን አማኑኤል)
አዳራሹ “ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል የሰማዕታትን
አደራ እንጠብቃለን!” በሚልና ሌሎች መፈክሮች፣ በሰማእታት ፎቶ እንዲሁም
ሰማእታትን የሚዘክር አለባበስ በለበሱ ከህፃናት እስከ አዋቂዎች አሸብርቃል፡፡ ትግሉ የሚስታውሱ ዘፈኖች፣ ዶክመንተሪዎች ከመድረክ
ሲለቀቁ የታዳሚው ስሜት የሚነኩ ነበሩ፡፡ ሰዓቱ ደርሶ በመድረክ መሪው የዝግጅቱ መጀመር አበሰረ፡፡ ይህ የሆነው ሰኔ 15 ቀን
በሚሊንየም አደራሽ በተከበረው 29ኛው የሰማእታት ቀን በዓል ላይ ነው፡፡
ውድ አንባቢያን የሰማእታት
ቀን ሰኔ 15 ቀን ሲከበር ያ ጀግና ህዝብና ልጆቹ የሰሩት ዘመን የማይሽረው ታሪክ ለማሰብ ብቻ ሳይሆን አዲሱ ትውልድ ልምድ
ወስዶበት፣ ተምሮበት እንዲያልፍም አስፈላጊ በመሆኑም ጭምር ነው ፡፡ የትግራይ ህዝብ እና ሀገር ወዳድ ልጆቹ ወደ ትግል የገቡት ወደው አልነበረም፡፡
ሁሉንም አማራጮች የዘጋ አምባገነን መንግስት በመሆኑ እንኳንስ የብሄር መብት ይከበርልን፣ በቋንቋችን እንነጋር ብለው ጥያቄ
አቅረበው መብታችን ይከብር ሊሉ ይቅርና እነዚህን መብቶች ለማሰብ ጭምር የማይፈቅድ ስርዓት የነበረበት ወቅት ስለሆነ ነው፡፡ ከዚህ
የከፋ ነገር ሊኖር አይችልም ብሎ በመሪ ድርጅቱ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እልህ አስጨራሽ ትግል ለ17 አመታት
ታግሏል፡፡
በህዝቡ ላይ ካደረሰው
ብሄራዊና መደባዊ ጭቆና በላይ ሰራዊቱ ባለፈበት አካባቢ ቤቶች እያቀጠለ፣ በተደጋጋሚ በአየር እየደበደበ “አሳን ለማጥፋት ባህሩን ማድረቅ” የሚለውን የተሳሳተ የአምባገነኖች
አቅጣጫ ተግብሯል፡፡ በሓውዜን
ምድር ላይ ማንም በራሱ ዜጋ ላይ ያደርገዋል ብሎ የማይገመትን ግፍ በዚህች ታሪካዊ ቀን ሰኔ 15/ 1980 ዓ.ም ፈፅሟል፡፡ ከ2500
በላይ የሃውዜን ህዝብ በራሱ መንግስት በገበያ ቀን በጠራራ ፀሀይ ተጨፍጭፏል፡፡ አምባገነኑ ደርግ ትግሉን ለማዳከም ምንጩን
ማድረቅ እንደሚገባው አምኖ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ ቢፈፅምም ቅሉ በጥቂት ቆራጥ ወጣቶች የተጀመረው ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየጠነከረ የመጣበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡ በትግራይ የተካሄደው ትግል ለሌሎች የአገራችን ህዝቦች ትግል ብርታት ሆኖ የኢትዮጵያ
ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተጭኖባቸው የነበረውን አምባገነናዊ ስርዓት በተባባረ ክንዳቸው እንዲገረስሱት አስችሏል፡፡
አዲስቷ ኢትዮጵያ እውን የሆነችው ብዙ መስዋእትነትን በጠየቀ የረጅም ጊዜ የህዝቦች
እልህ አስጨራሽ ትግል ነው፡፡
ጀግኖች ሰማዕታት በምንም
ሊገመት ወይም ሊከፈል የማይችል መስዋእትነት ከፍለው አሁን በእድገት ጎዳና በፍጥነት እያደገች ያለች፣ ዘርፈ ብዙ መሰረታዊ ለውጥ
በህዝቦችዋ ተሳትፎ እያስመዘገበች ያለች ሀገር፣ ለአድልዎ በር የዘጋ የፌደራል ስርዓት ባለቤት እንድንሆን አስችለውናል፡፡
ውድ አንባቢያን፣
የሰማዕታትን ቀን ስንዘክር አሁን ባለው የፀረ ድህነት ትግል እያንዳንዳችን ያለብንን ሃላፊነት ለመወጣት ቃላችንን በማደስ መሆን
አለበት፡፡ አሁን ትግላችን ራሳችንን ከድህነትና ከኋላቀርነት ለማላቀቅ ነውና ከሰማዕታት ህዝባዊነትን፣ የሀገር ፍቅርን፣ የአላማ
ፅናትን፣ ወዘተ መልካም እሴቶች ተላብሰን በእስካሁኑ ጥረታችን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ጠብቀንና አጠናክረን መዝለቅ ይገባናል፡፡
አዲሱ ትውልድንም ታሪኩ
በአግባቡ አውቆ አሁን ሀገራችን የጀመረችው የህዳሴ ጉዞ ለማስቀጠል ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ከአደጋ መጠበቅ አለበት፡፡
ያ ትውልድ ህዝቡ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የህዳሴ መሰረት ጥሏል፡፡ አዲሱ ትውልድ በበኩሉ የህዳሴውን ጉዞ ከግብ ለማድረስ
ከሚያደርገው ርብርብ ጎን ለጎን ለሰማእታትና በህይወት ያሉ ታጋዮች የሚገባቸው ክብርና ድጋፍ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡
ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!
No comments:
Post a Comment