EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Wednesday, 22 July 2015

ክብራችን ሲታደስ


(በየማነ ገብረስላሴ)
ባሳለፍነው ሳምንት መዲናችን አዲስ አበባ 6ሺ ያክል ከአለማችን የተለያዩ ክፍሎች የመጡ እንግዶችን አስተናግዳለች፡፡ የበርካታ የአገር መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች አዲስ አበባ የመገኘታቸው ምክንያት ደግሞ ሶስተኛው ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ነው፡፡ ለአራት ቀናት ከቆየው ከዚህ ታላቅ ጉባዔ ጎን ለጎን 200 የሚሆኑ የጎንዮሽ ስብሰባዎችም ተካሂደዋል።

ጉባኤውን በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ያደረገው ዋና ምክንያት አገሪቱ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያስመዘገበች መሆኗና ይህን ጉባዔ ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም አስቀድማ እንደገነባች በጉባዔው አዘጋጆች በመታመኑ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በየጊዜው የምታስተናግደውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ጨምሮ በብቃት ያስተናገደቻቸው እንደ አለም አቀፍ የጤና ጉባዔመ፣ የአለም ኢኮኖሚክ ፎረምና ሌሎች አለም አቀፍ ስብሰባዎች አገራችን በስኬት ያስተናገደቻቸው ጉባዔዎች አስተዋፆ የላቀ ነው።
አገራችን በተለይ የሚሊንየሙን የልማት ግቦች በማሳካት በአርያነት የሚጠቀስ አፈፃፀም አሳይታለች፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሓፊ ባን ኪ ሙን ይህንን የሚያኮራ አፈፃፀም አድንቀው ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ያላትን መልካም ተሞክሮ ለሌሎች አገሮች እንድታካፍል ጠይቀዋል፡፡
ከጉባዔው ዋዜማ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የመገኛኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ስላለው ሁለንተናዊ ፈጣን ዕድገት ሰፊ ሽፋን እየሰጡ ነው፡፡ ከእነዚህም ቢቢሲ አንዱ ነው፡፡ የቢቢሲው ጋዜጠኛ አንድሬው ሀርዲንግ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ጉብኝት በማድረግ “ኢትዮጵያ ረሃብን ተሻገረች” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ዘገባ አገሪቱ በረኃብና ድርቅ የምትታወቅበትን ምዕራፍ መዝጋቷን አመልክቷል፡፡ በ1977ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለቁበት አካባቢ አሁን ሰፊ ልማት እየተከናወነበት መሆኑንም ጠቅሷል፡፡ የመስኖ ስራዎች እየተስፋፉ፣ ተራሮችም በደን እየተሸፈኑ መሆናቸውን በመግለፅ በአገራችን እየተመዘገበ ላለው ፈጣን ዕድገት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ድህነትን ለማጥፋትና ከውጭ ዕርዳታ ለመላቀቅ የተለጠጠ ህልም ያለው  መሆኑን ገልፆ ኢትዮጵያ አብዛኛዎቹን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች በማሳካት ረገድ በምሳሌነት የምትጠቀስ አገር መሆኗንም አብራርቷል፡፡

ኢትዮጵያ በብዙዎች ዘንድ የአፍሪካ የነፃነትና የስልጣኔ ተምሳሌት ተደርጋ ትወሰዳለች፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ስሟን ከድርቅና ረሃብ ብቻ አይይዘው የሚጠሯት ብዙዎች ነበሩ፡፡ አንድ ሰው ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር ሲጓዝ የሚበላና የሚቀመስ አገር ከሌላት አገር የመጣ አድርገው ከንፈራቸው የሚመጡ፣ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡም በርከት ያለ ምግብና እህል የሚሸከሙበት ወቅት የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከስልጣኔ ማማ ቁልቁል ወርዳ የረኃብና የድህነት ምሳሌ የሆነችበት ዋና ምክንያት ብዙኃነትን በአግባቡ ማስተናገድ አቅቷት ሰላሟ በመናጋቱ ነው። በስልጣን ላይ የነበሩ መንግስታትም አገሪቱን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችል ፖሊሲ ስላልነበራቸው የስልጣኔ ማማ ላይ የነበረችውን አገራችንን በብዙ ዘርፍ የአገራት ጭራ አድርገዋታል፡፡

በተለይም ለዘመናት ነግሶ የነበረው ጭቆና ዜጎች ሰርተው ስለመለወጥ ሳይሆን ቅድሚያ ለመብታቸው እንዲታገሉ የሚገፋፋ ነበር፡፡ ይህ በመሆኑም ዜጎች ለመብታቸው መከበር በጋራ ታግለው አምባገነናዊውን ስርዓት እስካስወገዱበት 1983ዓ.ም ድረስ አገራችንን ለተራዘመ ግጭትና ጦርነት እንዲሁም ረኃብና ድንቁርና ተዳርጋ ቆይታለች፡፡ በተወሰኑ ዓመታት ልዩነት ብቅ የሚለው ድርቅም የከፋ ሞትና ስቃይ አስከትሏል፡፡ በተለይ በ1977ዓ.ም በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተከሰተው ድርቅ በአስከፊነቱ ወደር አልነበረውም፡፡ ይህን ተከትሎም አብዛኛው የውጭው ማህበረሰብ ድርቅና ኢትዮጵያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ አድርጎ እንዲመለከት ምክንያት ሆነ፡፡ ዛሬ ግን ትናንት አይደለም፡፡

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እና በእሱ የሚመራው መንግስት መላ የአገራችን ህዝቦችን በማስተባበር ባደረጉት ርብርብ ሁኔታዎች ተቀይረዋል፡፡ የዜጎች የልማት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በእጅጉ አድጓል፡፡
ኢትዮጵያ በድርጅታችን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመር እየተመራች ዘርፈ ብዙ ድሎችን አስመዝግባለች፡፡ ዓመታዊ የሀብት መጠኗን 1.5 ትሪሊዮን በላይ፣ የዜጎቿን አመታዊ አማካይ የነፍስ ወከፍ ገቢ ደግሞ 1983 . ከነበረበት 70 የአሜሪካን ዶላር አሁን 636 ዶላር አድርሳለች። 5 ሚሉዮን ኩንታል ዘሎ የማያውቀው ሃገራዊ የግብርና ምርት መጠን አሁን 254 ሚሊዮን ኩንታል ደርሷል፡፡ በዚህም በምግብ ሰብል ራሷን መቻሏ እንደ ፋኦ ባሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር የተረጋገጠ ሃቅ ሆኗል፡፡ 1984 . 19 ሺህ ኪሎ ሜትር ያክል ብቻ የነበረውን ጠቅላላ የመንገድ ርዝመት 86 ኪሎ ሜትር ማድረስ ችላለች፡፡ ኢህአዴግ ሀገሪቱን ሲቆጣጠር 300 ሜጋ ዋት ያልሞላውን ሃይል የማመንጨት አቅም አቅም አሁን 2 ሜጋ ዋት በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን ይህንኑ አቅም በቅርብ ጊዜ 10 ሜጋ ዋት ሊያደርሱ የሚችሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንም በስኬት በማከናወን ላይ ትገኛለች።
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ቁጥራቸው 22 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጐች በትምህርት ገበታ ላይ መገኘታቸው ኢትዮጵያ በትምህርት ልማት ያስመዘገበችውን ድንቅ ውጤት ያሳያል። ለበርካታ ዓመታት በሁለት ዩኒቨርስቲዎች ሲንገዳገድ የቆየው የትምህርት ሥርዓት በአሁኑ ወቅት በመንግስት ብቻ 33 ዩኒቨርስቲዎች ያሉትና ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎችን የያዘ ሆኗል፡፡ የሀገሪቱ የመሠረታዊ የጤና አገልግሎት ሽፋን 1983 ከነበረበት 41 በመቶ በአሁኑ ወቅት ወደ 93 ነጥብ 4 በመቶ አድጓል፡፡ የዓለም ባንክ የቅርብ ጊዜ ጥናት ውጤት እንደሚያሣየው የኢትዮጵያውያን የነፍስ ወከፍ አማካይ የህይወት ዘመን 23 ዓመታት በፊት ከነበረበት 49 ዓመት ወደ 64 ዓመት ከፍ ብሏል፡፡ በየዘርፉ የተገኘው ስኬት ድምር ኢትዮጵያን በአለም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አገራት ተርታ ሲያሰልፋት በአፍሪካ ቀዳሚዋ የኢንቨስትመን መዳረሻ ለመሆንም በቅታለች፡፡
ኢትዮጵያ በልማት ብቻ ሳይሆን በዴሞክራሲም ረጅም ርቀት የተጓዘች ሀገር ነች፡፡ ከአንድ ፓርቲ ወደ ብዙ ፓርቲ ዴሞክራሲ፣ በሃይል ስልጣን ከሚያዝበት ወደ ስልጣን በምርጫ ብቻ የሚያዝበት ዴሞክራሲ፣ ከጥቂት ብሄሮች፣ እምነቶች፣ ቋንቋዎችና ባህሎች የበላይነት ወደ ብዝሃነት የሚያስተናግድ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ፣ ከመሪዎች አምባገነንነት ወደ ህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲ ስርዓት ተሸጋግራለች፡፡ ይህ ሲባል ግን ኢትዮጵያ ፍፁም ዴሞክራሲያዊት ነች ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ምክንያቶቹ ዘርፈ ብዙ ቢሆኑም በልማቱ ካስመዘገበችው ስኬት ይልቅ የዴሞክራሲ ውጤቶቿ በፈተና የተሞሉ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዜጎች በረሃብ የሚያልቁባት ሳትሆን ሰርተው የሚለወጡባት፣ መንደሮችና ቀበሌዎች የጦርነት አውድማ መሆናቸውን አብቅቶ ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት የሚስፋፉባቸው፣ እንደ መንገድ፣ የኃይል ፕሮጀክቶች፣ ስልክና ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮች የተስፋፉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት አዲስ አበባን በቂ መሰረተ ልማት የላትም በሚል ሰበብ ለአፍሪካ ህብረት መዲናነት አትመጥንም ሲሏት የነበሩ ግለሰቦችና የመገናኛ ብዙኃን ዛሬ ”ቀጣይዋ ዱባይ” በማለት ከተማዋ እያስመዘገበችው ላለው ፈጣን ዕድገት ምስክርነታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በድህነት የተዘባበቱብን ዓለም አቀፍ ተቋማት ባለፉት 12 ዓመታት ባስመዘገብነው ፈጣን ዕድገት ተደምመው ሳያበቁ ”በቀጣዮቹ ዓመታት የኢትዮጵያን የሚያክል ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያስመዘግብ አገር የለም” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እኤአ እስከ 2017 ፈጣን ዕድገት ከሚያስመዘግቡ አገሮች ኢትዮጵያን በአንደኝነት አስቀምጧታል፡፡ በፋይናንስ ጉባኤው ላይ የተሳተፉት የዓለም ባንክ ፕሬዚዳነት ጂም ዮንግ ኪም “ኢትዮጵያ ከ15 ዓመታት በፊት የነበረችበትን ሁኔታ የሚገነዘብ ሰው ከ15 ዓመታት በኋላ የት ልትደርስ እንደምትችል መተንበይ አያቅተውም” በማለት የአገራችን ዕድገት ሩቅ አዳሪ መሆኑን በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡

ዓለም በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ላለው ፈጣን ዕድገት ምስክርነቱን እየሰጠ ባለበት ወቅት ሌላ የምስራች ከአውሮፓ የንግድና የቱሪዝም ምክር ቤት ተሰምቷል፡፡ ኢትዮጵያን ‘የዓመቱ ምርጥ የባህል ቱሪዝም መዳረሻ’ በማለት ከ31 አገሮች መካከል መርጧታል፡፡ ሲኤን ኤን በድረ ገፁ ኢትዮጵያ ያላት ጥንታዊ ባህልና አስደናቂ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ በምክር ቤቱ እንድትመረጥ እንዳስቻላት አስነብቧል፡፡

ኢትዮጵያ ድህነትን ለማሸፍ ባካሄደችው እልህ አስጨራሽ ትግል አመርቂ ውጤቶች እያስመዘገበች የምትገኝ አገር ብትሆንም ለዘመናት የተከማቹ ችግሮቿ ግን በአጭር ዓመታት ትግል የሚፋቁ አይደሉም፡፡ አሁንም ድህነት ቀነሰ እንጂ አልጠፋም፡፡ ገፅታዋ እየተሻሻለ ነው እንጂ ሙሉ በሙሉ አልተቀየረም፡፡ የረከሰው የአገራችን ስምና፣ የተዋረደው ክብራችን በአዲስ መልክ እየታደሰ ነው፡፡ ይህ ግን ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል፡፡

ድርጅታችን ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት እስካሁን ያስመዘገባቸውን መልካም ተግባራት ቀምሮ ለበለጠ ድል እየተረባረበ ይገኛል፡፡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ወይይት እየተደረገበት የሚገኘው ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አገራችን በ2017ዓ.ም ከመካከለኛ ገቢ ታችኛው ረድፍ ለማሰለፍ ያለመ ነው፡፡ በሁሉም መስኮች እየተመዘገበ ያሉ ለውጦች ተጠናክረው ከቀጠሉ የአምስት አመቱ እቅድ መሳካት ብቻ ሳይሆን አገራችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከበለፁ አገሮች ተርታ እንደምትሰለፍ አያጠራጥርም፡፡ ለዚህ ግን ወገብን የሚያጎብጡ የተለጠጡ እቅዶችን በቁርጠኝነት ለመተግበር ለየራሳችን ቃል መግባት አለብን።

No comments:

Post a Comment