EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Thursday 4 December 2014

የስልጤ ዞን በፈጣን የልማት ጎዳና

በፈድሉ ጀማል
እንደ ሌሎቹ የክልሉ ሕዝቦችና የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሁሉ የስልጤ ሕዝብም ያለፉትን የአፈናና የጭቆና ስርዓቶች አሜን ብሎ አልተቀበለም፡፡ ይልቁንም የድህነት፤ የብሔር ጭቆናና የፀረ ዴሞክራሲ መሰረት የሆኑትን ስርዓቶች መስዋዕትነት እየከፈለ ታግሏቸዋል፡፡ ከብሔራዊ ጭቆና ነፃ ከወጣ በኋላም ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት መላውን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ ባደረገው የሀገር ግንባታ እንቅስቃሴ ውስጥ ድርሻውን በመወጣት ላይ ነው፡፡ አሁን የስልጤ ህዝብ እንደ ሀገር በተመዘገበው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድል ተሳታፊና ተጠቃሚ በመሆን የትግሉን ትሩፋቶች እያጣጣመ ይገኛል፡፡
የስልጤ ዞን በተለይ በዞንነት ተደራጅቶ ራሱን ማስተዳደር ከጀመረበት ያለፉት 13 ዓመታት ወዲህ በጠራ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መስመራችን ታግዞ ስራ ወዳዱ የዞኑ ህዝብለውጥና በልማት ቁጭት ተነሳስቶ ባከናወናቸው በርካታ ተግባራት አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል፡፡ በስልጤ ዞን ባለፉት 10 ዓመታት ብቻ የግብርና ሰብሎች ምርታማነት በስድስት እጥፍ ያክል አድጓል፡፡ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የነበረው የግብርና ግብዓትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አሁን በእጅጉ ተቀይሯል፡፡
በተመሳሳይ በንፁህ መጠጥ ውሃ፣ በመንገድ፣ በቴሌኮምና በኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ሁሉንም የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በተደረገው ርብርብ አመርቂ በሚባል ደረጃ ውጤት ሊመዘገብ ችሏል፡፡ በባንክ አገልግሎት ረገድም አንድ ባንክ እንኳን ያልነበረበት ዛሬ በዞኑ ሁሉም ወረዳዎችና በዋና ከተማዋ ወራቤ 11 ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
1983. 9000 ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ 55 አንደኛ ደረጃ /ቤቶች ብቻ የነበሩበት ሁኔታ ተቀይሮ 288 አንደኛ ደረጃና 31 የሁለተኛ ደረጃ /ቤቶች በአጠቃላይ 319 /ቤቶች 226ሺ 662 ተማሪዎች በመማር ላይ የሚገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ አንድኢንዱስትሪ ኮሌጅም ተከፍቷል፡፡
ድርጅታችን ኢህአዴግ በሁሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዘርፎች እድገት ሊመጣ የሚችለው ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ ሲኖር ብቻ ነው ከሚለው ፅኑ እምነት በመነሳት ለጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱ ይታወቃል፡፡ በስልጤ ዞን በተደረገው ርብርብም የተሟላ ጤና ጣቢያ እንኳን ያልነበረው የዞኑ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት 197 ጤና ኬላዎችና 35 ጤና ጣቢያዎች ባለቤት ለመሆንና ዞናዊ የጤና ሽፋኑንም 95 በመቶ ለማድረስ በቅቷል፡፡
በሀገራችን የተመዘገበው ፈጣን እድገት ዜጎች ልማትን የሞት የሽረት ጉዳይ አድርገው እስከያዙና ክንዳቸውን እስካስተባበሩ ድረስ የማይናድ የድህነት ተራራ እንደሌለ ያረጋገጠ ሃቅ ነው፡፡ የስልጤ ሕዝብ መሰረታዊ የጤና አገልግሎትማይገኝበት ሁኔታ ተላቆ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአርሶ አደሩ የተባበረ ክንድ የገነባው የወራቤ ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዚህ እውነታ ሌላው ማሳያ ነው፡፡
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሰራው በስልጤ ልማት ማህበር አስተባባሪነት ሲሆን 251ሚሊዮን 539ሺ 29 ብር ወጪ ተደርጎበታል። ከዚህ ውስጥ 80 በመቶው አካባቢው የተሸፈነው በአርሶ አደሩ ነው፡፡ ከአርሶ አደሩ በመቀጠል በዞኑ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ከለት ጉርሳቸው በመቀነስ ያበረከቱት ድጋፍ ለግንባታው ትልቅ አስተዋፅኦ የነበረው ነው፡፡ የአካባቢው ተወላጅ ባለሃብቶች ምንም እንኳን ከአርሶ አደሩና ከመንግስት ሰራተኛው እንዲሁም ካላቸው አቅም አንፃር ሲታይ ያበረከቱት አስተዋፅኦ በቂ እንዳልሆነ ቢታወቅም የተወሰነ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ሆስፒታሉ 14 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በድምሩ 691 ዘመናዊ የታካሚ መኝታ ክፍሎችን ይዟል። ሁለት የኤሌክትሮኒክስ እና የኬሚስትሪ ላብራቶሪዎች ሲኖሩት የቀዶ ጥገና ክፍሉ በአንድ ጊዜ አራት ሰው ማስተናገድ ይችላል። ሆስፒታሉ 11 ትልልቅ ህንፃዎች ያሉት ሆኖ ለተጎዱ ታካሚዎች እናተመላላሽ ታካሚዎች መግቢያ የተለያዩ በሮች አሉት። ሶስት ፋርማሲዎችን የያዘው ይህ ሆስፒታል በየጊዜው የሚመጡ ቴክኖሎጂዎችን፤ አዳዲስ አሰራሮችንና ግኝቶችን ለማካተትና ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ ታስቦ የተገነባ ነው።
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህዳር 20/2007 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሊቀ መንበር ጓድ ይለማርያም ደሳለኝና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስትና የድርጅት ስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የዞኑ ነዋሪዎችና የአካባቢው ተወላጆች በተገኙበት ተመርቋል፡፡
በምረቃው ወቅት የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ / ከሰተብርሃን አድማሱ ሆስፒታሉ እስከ አሁን በሀገር ውስጥ የማይሰጡ የህክምና አይነቶችን በመስጠትና በተወሰነ መልኩም ወደ ውጭ የሚደረገውን የህክምና ጉዞ በመቀነስ ከዞኑ ሕዝብ አልፎ ለአካባቢውና ለመላ ሀገሪቱ ህዝብ ጠቀሜታው ከፍተኛ እንደሚሆን አረጋግጠዋል፡፡
ከሆስፒታሉ ምረቃ ቀደም ብሎ በስልጤ ልማት ማህበር አዘጋጅነት በተካሄደ ሲምፖዚየም በዞኑ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን አስመልክቶ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ ውይይቱ እስከ አሁን በተከናወኑና በቀጣይ ሊከናወኑ በታቀዱ ስራዎች ዙሪያ እንዲሁም በባለድርሻ አካላት ሚና ላይ መግባባት የተደረሰበት ነው፡፡ በተለይ ባለሃብቱ ዞኑን ለማልማት ካለው ትልቅ አቅም አንፃር እስከ አሁን ያደረገው ድጋፍ ተመጣጣኝ እንዳልነበር የተነሳ ሲሆን ይህንንም ባለሃብቱም በመቀበል በቀጣይ ድርሻውን ለመወጣት በቁጭት ቃል የገባበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
በዚሁ ወቅት ከልማት ስራዎች ምረቃ በተጨማሪ በዞኑ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነ ስርዓትም ተከናውኗል፡፡ ይህም ቀደም ብሎ በህዝቡ ሲጠየቅ የነበረመሆኑ በነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ደስታን ሊፈጥር ችሏል፡፡ የዩኒቨርሲቲው መገንባት ለወራቤ ከተማና አካባቢው እድገት ትልቅ አስተዋጾ እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባደረጉት ንግግር በዞኑ ልማት ሊፋጠን የቻለው በዋናነት የኢትዮጵያን ህዝቦች የዘመናት ጥያቄ መመለስ የቻለው ዴሞክራሲያዊ ህገ-መንግስት ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት እድል ስለተፈጠረ በመሆኑ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የመጠበቅ ሃላፊነት የሁሉም ዜጋ መሆን እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡

በልማታዊና  ዴሞክራሲያዊ መንግስታዊ የተገኙ ድሎችን ጠብቆ በማስቀጠል ለተጨማሪ ድሎች የላቀ ርብርብ እናድርግ በሚል መሪ ቃል የተከበረው የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ሌሎች የልማት ስራዎች ምረቃ በዓል ዋነኛ ዓላማ በልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመር የተገኙ የህዝብ ድሎችን በማስታወስና በመገምገም ለተጨማሪ የላቀ ድል ህዝባዊ መነሳሳትን መፍጠር ነው፡፡

No comments:

Post a Comment