EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Sunday, 2 November 2014

የዲፕሎማሲያችን ትሩፋቶች


ከረድኤት ልጅ
በዓለም ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያ በቀደምት ስልጣኔያቸው ከሚታወቁት ሀገራት መከከል ትመደባለች፡፡ ኢትዮጵያ በ3000 ዓመታት የስልጣኔ ታሪኳ ከውጭው ዓለም ጋር በተለይም ንግድን መሰረት ያደረገ የውጭ ግንኙነት ስራዎችን ታከናውን ነበር፡፡ ከአፍሪካ ሀገራት፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከሩቅ ምስራቅ አካባቢዎች ጠንካራ ግንኙነት ነበራት። በአክሱም ስልጣኔ ዘመን በውጭ ንግድና በጦር ስምምነቶች ላይ የተመሰረቱ በርካታ የውጭ ግንኙነቶች እንደነበሯት ታሪኳ ያስረዳል።
የኢትዮጵያ ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ታሪክ ከ19ኛ ክ/ዘመን አጋማሽ እንደሚጀምር ታሪክ ያወሳል፡፡ በዚህ ዘመንም ከነበሩ የሀገሪቱ ነገስታት መካከል አፄ ቴዎድሮስ ከውጭው ዓለም በተለይም ከምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ጋር ጠንከር ያለ ግንኙነት እንደነበራቸው በርካታ ፀሃፊዎችና የታሪክ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡ በአፄ ምኒሊክ የንግስና ዘመንም የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጠነከሩ የመጡበትና ኢትዮጵያም አብዛኛዎቹን የአውሮፓ ሀገራት መድረስ የቻለችበት ወቅት ነበር፡፡ በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ሚሽኖች ከሁሉም የዓለም ክፍሎች ወደ ኢትዮጵያ የመጡበትና ይፋዊ ግንኙነቶች ከጣሊያን፤ ከጀርመን፤ ከታላቋ ብሪታኒያ፤ ፈረንሳይና ራሺያ እንዲሁም ከሌሎች በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ጋር የተከናወኑበት ወቅት ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ቀድማ ብትጀምርም የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት ዘመናዊነትን የተላበሰው በንጉሱ ዘመን እንደሆነ ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያነት የተፃፈ አንድ ፅሁፍ ይገልፃል፡፡ በወቅቱ ሀገሪቱን በቋሚነት የሚወክሉ ዲፕሎማቶችን መሰየም እንደተጀመረና በተለያዩ ሀገራትም የዲፕሎማቲክ ሚሽን የሚያስፈፅሙ ተቋማት እንደተከፈቱ ያነሳል፡፡ ይሁንና በእነዚያን ጊዜያቶች የነበሩ የውጭ ግንኙነቶች በጠራ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሩና የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስከብሩ ነበሩ ለማለት አያስደፍርም። በመሆኑም አብዛኛዎቹ ግንኙነቶች የውጭ ኃይሎችን ጥቅምና ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ነበሩ ማለት ይቻላል።
ያለፉት መንግስታት ይከተሏቸው የነበሩት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች በአንድ በኩል ለአገራዊ ህልውናችን ወሳኝ የሆኑትን ውስጣዊ ችግሮቻችንን ወደ ጎን በመተው ከውጭው ወደ ውስጥ የመመልከት ሁኔታ ጎልቶ የሚታይባቸው በሌላ በኩል መነሻቸው በውጭ ጠላቶች የመከበብና የጠላትነት ስሜት ጎልቶ የሚታይበት ነበር፡፡ ይህ አገራዊ ጥቅማችንና ህልውናችንን በተገቢው ደረጃ እንዳይረጋገጥ ከማድረጉም በላይ ከውጭው ዓለም ጋር በነበረን ግንኙነት ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ በተከታታይ ዋጋ አስከፍሎናል፡፡
የተሳሳተው የውጪ ግንኙነት አካሄድ ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ እንዳስከፈላትና ብዙ እንዳሳጣት የተረዳው በኢህአዴግ የሚመራው የኢፌዴሪ መንግስት ይህን የሚያርም የውጭ ግነኙነትና የደህንነት ፖሊሲ አውጥቷል፡፡ የፖሊሲው ዋናው ትኩረት በሀገር ውስጥ በሚሰራው ስራ ላይ እንዲሆን፣ ኢኮኖሚውን ማዕክል እንዲያደርግ፣ በበቂ ጥናት ላይ ተመስርቶ ከውጭ የሚገኙ ጥቅሞችን አሟጦ መጠቀምና አደጋዎችን መቀነስ እንደሚገባ፣ ብቃት ያለው የመከላከያ ዓቅም እና ጠንካራ የማስፈፀም ዓቅም መገንባት እንዳለብን በግልፅ በማስቀመጥ ከውስጥ ወደ ውጭ የሚመለከት ጤናማ የውጭ ግንኙነት ፖለሲ በማዘጋጀት ለተፈፃሚነቱ ሌተ ቀን እየተረባረበ ይገኛል።
ፖሊሲው ከምንም በላይ የአገሪቱን ሉዓላዊነት መጠበቅን፣ ፍትሐዊ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ በህዝቦች ተሳትፎና መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ግንባታን፣ አገራዊ ክብርን ማስጠበቅን በሚያስችል መልኩ በከፍተኛ ጥንቃቄና ህዝባዊ ኃላፊነት የተዘጋጀ ነው።
ፖሊሲና ስትራቴጂው የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን በማዕከልነት ሲያስቀምጥ በዋነኝነት በአገር ውስጥ የሚካሄደውን የልማት እንቅስቃሴ በእጅጉ የሚረዱ፤ የስራ እድልን ሊፈጥሩ የሚችሉና ከፍተኛ ካፒታልና እውቀትን ሊያሸጋግሩ የሚችሉ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ዋና ተግባሩ በማድረግ ነው፡፡ ለዋና ዋና የውጪ ምርቶቻችን ገበያ ማስፋትና ለአዳዲስ የውጭ ምርቶቻችን ገበያዎችን ማፈላለግ፤ ከውጭ ንግድ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ማሳደግ፣ የቱሪዝም መስህቦቻችንን በአግባቡ በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ እንዲሁም ከአገሪቱ ነባራዊና ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አብረው የሚሄድና ልማቱን ሊደግፍ የሚችል የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግን እንደ አቅጣጫ በማስቀመጥ በርካታ እንቅስቃሴዎች ተደርገው ስኬታማ ሆኗል፡፡
በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ለዜጎች በርካታ የስራ እድሎችን የሚፈጥሩ፣ የአገሪቱን ልማት በዘላቂነት የሚደግፉና የሚያፋጥኑ፣ ከፍተኛ ካፒታልና መለስተኛ ቴክኖሎጂዎችን የሚያሸጋግሩ እንዲሁም የስራ አመራር ጥበብና ክህሎት ያላቸው፣ የአገር ውስጥ ምርትን በግብዓትነት የሚጠቀሙና መሰረታዊ የገቢ ምርቶችን በአገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሬን የሚያሳድጉና ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ኢንቨስትመንቶች ወደ አገራችን መሳብ ተችሏል፡፡ ይህም በኢኮኖሚው ውስጥ የድርሻውን በማበርከት የፀረ ድህነት ትግሉን በከፍተኛ ደረጃ በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡
አገራችን የውጭ ግንኙነቱን ጨምሮ በሌሎች ፖሊሲዎቻችንና ስትራቴጂዎቻችን እየተመራች በረሀብ፣ ቸነፈርና ጦርነት የዓለም አቀፉን ሚዲያ ዘገባ ከማድመቅ ተላቅቃ የፈጣን ልማትና እድገት አርአያ ሆና መጠቀስ ከጀመረች እነሆ ከአስር ዓመታት በላይ ተቆጥሯል በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ጥቂት ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍም በቅታለች፡፡ ይህን የሀገራችንን ዕድገት በቅርበት ተከታትለው ሃቁን የተገነዘቡ በርካታ የውጭ ባለሃብቶች ዓይናቸውን ሀገራችን ላይ በመጣል በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ከፍተኛ ፍላጎትማሳየት ላይ ናቸው።
ለምርቶቻችን አስተማማኝ የውጭ ገበያ ማፈላለግና የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያች አንዱ ዓብይ ተግባር ነው፡፡ ኤምባሲዎችና ዲፕሎማቶቻችን የአገራችንን ምርቶች በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በማስተዋወቅ፣ ገዢዎችን ከአገራችን ላኪዎች ጋር በማስተሳሰራቸው ግብይቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአይነትና በመጠን እያደገ ነው፡፡ 
የአገራችንን ደህንነት ለማረጋገጥ የምንከተለው  በውጭ ጉዳይና አገራዊ ደህንት ፖሊሲና ስትራቴጂ እየተመራች ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ደሴት የሚል ስያሜ አትርፋለች፡፡ ይህ ሰላማዊ ሁኔታ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው የሚጠይቀው ቀዳሚው መስፈርት በመሆኑ የቱሪዝም ልማቱ እያበበ ይገኛል፤ ከዘርፉ የሚገኘው ጥቅም ለኢኮኖሚያችን አጋዥ ሆኗል፡፡
በውጭ ጉዳይና አገራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነድ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው ከማንኛውም አገር ጋር የሚኖረን ግንኙነት በመሰረታዊ አገራዊ ጥቅማችንና ደህንነታችን ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ በዚሁ ዲፕሎማሲያዊ ስራችን ለዘመናት ወንዙን በብቸኝነት የመጠቀም መብት አለኝ በሚል ኢ-ፍትሓዊ አቋምና የተሳሳተ እምነት ስትመራ የነበረችው ግብጽ ይዛው የነበረውን ኢ-ፍትሐዊ አቋም ቆም ብላ እንድትፈትሽ እያደረግን እንገኛለን። በዓለም አቀፍ መድረኮችም ተሰሚነታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና ተደማጭነት እያተረፍን ነው። ይህ ደግሞ በኢህአዴግ የሚመራው የኢፌዴሪ መንግስት በሀገራችን የተፋጠነ ልማት ለማምጣት የሚያስችል ትክክለኛ ሀገር በቀል ፖሊሲና ስትራቴጂ ውጤት እንደሆነ ከማንም የሚሰወር አይደለም፡፡
ወደነበርንበት የስልጣኔ ማማ ለመድረስ ብዙ ጊዜ እንደማይወስድብን ከተስፋ ሰጪው ጅማሯችን ተነስተን መደምደም እንችላለን። በዚህ ታሪካዊ የህዳሴ ጉዟችን እያንዳንዱ ዜጋ ታሪካዊ አሻራውን ለማኖር እየተረባረበ መሆኑ ስንረዳ ደግሞ የሀገራችን ህልም በእውነትም በቅርብ ጊዜ እንደሚሳካ የሚያረጋግጥ ነው።

1 comment:

  1. Subject:IN THE COMING ELECTION IN ETHIOPIA, 2010 e.c concern issue.

    Ethiopia government is doing radical Change for democracy after derg rigme.peoples are taking different benefits for Change for new life.coming election 2010 government will implement for justice and good governance and benefits for peoples.so, government prepare for coming election for peoples are insure for justice and good governance implementation according to international law for all peoples besides government initiative election programmed to success of election result and people vote will gaining in 2010 election.so. government concern for peoples benefit of justice and good governance in the coming election. peoples are need justice and good governance for implement in our current situation.to promote democracy and civil right.government expect to gate more vote government should be insure justice equal for all and good governance implementation in Ethiopia peoples and representatives.B/c Ethiopian peoples and representative having more concern for justice and good governance in the coming election to besides with government election vote in 2010.so, government concern for those two things for peoples issue.
    Thanks!
    Ethiopia live for ever!
    Long live for EPDRF!
    we wish!

    ReplyDelete