EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Wednesday 18 July 2018

ፕራይቬታይዜሸን ለምን?




 በወጋገን አማኑኤል
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ መደበኛ ስብሰባውን ካካሄደ በኋላ በአበይት ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ መሆኑ ይታወቃል:: ሰሞኑን የአገራችን አበይት አጀንዳ ሆኖ አለም እየተነጋገረበት ያለው የኤርትራና የኢትዮጵያ አዲስ የሰላም ግንኙነትን ጨምሮ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች መሬት እየያዙ እየሄዱ መሆኑን መመልከት ይቻላል፡፡ ከውሳኔዎቹ ውስጥ አንደኛው የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ የአክስዮን ድርሻ እንዲኖራቸውና በመንግስት ይዞታ ሥር ያሉ ድርጅቶች የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሆቴልና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግሉ ዘርፍ እንዲዘዋወሩ የተላለፈው ውሳኔ ነው፡፡ ይህን እንደ መነሻ በመወሰድ ስለ ፕራይቬታይዜሽን አንዳንድ ሃሳቦችን ማብራራት አስፈላጊ ነው፡፡ 


ምሁራን ፕራይቬታይዜሽንን ሲገልፁት በተለያየ መልኩ የሚያስቀምጡት ቢሆንም አብዛኛውን  የሚያስማማው የጋራ ትርጉም በመንግስት ተይዘው የነበሩ ምርትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ወደ ግሉ ዘርፍ በማስተላለፉ በግሉ ሴክተር እንዲተዳደር ማድረግ ነው ይላሉ፡፡ ዘመናዊ የፕራይቬታይዜሽን አካሄድ እንደ ኢኮኖሚ ፓሊሲ በመጀመርያ የተጀመረው በጀርመን በ1957 እ.አ.አ ቮልስዋገን ካምፓኒ ወደ ግሉ ሴክተር በማዛወር ነበር፡፡ ከዛ በኃላም እንግሊዝና ፈረንሳይ ተክትለዋቷል፡፡  
ፓል የተባለው ፃሃፊ እንደሚለው ፕራይቬታይዜሽን ሀገራት እዳቸውን እንዲከፍሉ፣ ወለድ እንዲቀንሱ እና የኢንቨስትመንት መጠንን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይገልፃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንዲያድግም አስተዋጽ ያደርጋል፡፡ ወደ ሀገራችን ነበራዊ ሁኔታ መለስ ብለን ስንመለከተ ሀገራችን አምባገነኑ የደርግ ስርዓት ተወግዶ የተዋቀረው አዲስ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መንግስት በተከተለው የልማታዊ መንግስት መስመር እየተመራች ላለፉት 26 አመታት በሁሉም ዘርፍ በሚባል ደረጃ ለውጥ ማስመዝገብ ችላለች፡፡ በተለይ ባለፍት 15 አመታት ሀገራችን ፈጣን የሚባል የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ሆኖም ባለፉት ሁለት ሶስት ዓመታት አገራችን የነበረችበት ቀውስ የአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገቷ ላይ ከባድ ጫና ከማሳረፉ ባሻገር  የአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ምጣኔዋ ወደ አንድ አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት ሊወርድ ችሏል፡፡  መንግስት ይህንን አጠቃላይ ሀኔታ ለመለወጥ እየሰራ ይገኛል፡፡ የአገሪቱ የብድር ጣራ አስጊ በሚባልበት ደረጃ ላይ መሆኑ በመንግስት ግልፅ ተደርጓል፡፡ ይህንን በመጠኑም ቢሆን መለወጥ የሚቻለው ደግሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚነስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር ወቅት እንደተገለፀው አጠቃላይ ኢኮኖሚው እንዲያገግም ማድረግና በመንግስት የተያዙ ሴክተሮችን በተጠና መንገድ ወደ ግል በማዞር፤ የግል ባለሃብቱን በበለጠ በማበረታታትና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እድገትን በማሳለጥ ነው፡፡ 

ይህንና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ወስጥ በማስገባት የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ እና መንግስት በመንግስት እጅ ያሉ ድርጅቶች እንደ የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሆቴልና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች በከፊል እና በሙሉ ወደ ግሉ ሴክተር ለመዛወር መወሰኑን ይፋ አድርጓል ፡፡
ምሁራን እንደሚሉት ፕራይቬታይዜሽን ምርታማነትን ይጨምራል፣ ሰፊ የባለቤትነት ስሜት ይፈጥራል፣ ለግሉ ሴክተር የበድር አገልገሉት ያመቻቻል፣ ለመንግስት የገቢ ማስተንፈሻ ይሳጣል፡፡ ከዚህ በመነሳት መንግስት ያስተላለፈው ውሳኔ አንድ እርምጃ ወደፈት የሚያረምደን መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይ በመንግስት እጅ ተይዘው ያሉ ነገር ግን አገሪቱ የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ የማይመጥን አፈፃፀም ያላቸው ተቋማት ወደ ግል ሴክተሩ መዛወራቸው ምርታማነት እና አገልግሎት አሰጣጣቸው የተሻለ ለማድረግ አስፈለጊ ወሳኝም ጭምር  ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የወጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በማምጣት ረገደም ከፍተኛ ሚና ስለሚጫወት ሀገሪቱ ለምታደርገው የኢንድስትሪ፤ ኢኮኖሚ ሽግግር እና የውጭ ምንዛሪ ገቢንም በማሳደግ ረገድም ተጠቃሚ ያደርጋታል፡፡
የዓለምም ተሞክሮም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው፡፡  የላቲን አሜሪካ ሀገራት በተለይ እንደ ሀንጋሪ ያሉ በእዳ ተዘፍቀው የነበሩ ሀገራት ከነበሩበት የእዳ ማቅ በመውጣት  የገቢ ምንጫቸውን ማሳደግ የቻሉት የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል በማዛወር ነው፡፡  እነ ቻይና እና ኩባም ለረዥም ጊዚያት በራሰቸው ዘግተው ያቆይዋቸውን ሴክተሮች አስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት ሲሉ ከውጭም ከውስጥም ሴክተሮቻቸውን ለግሉ ዘርፍ ከፍት በማድረግ አሁን ለደረሰቡት የእድገት ደረጃ መብቃት ችለዋል፡፡
 
በሀገራችንም በመሪ ድርጅቱና መንግስት የተወሰነው ውሳኔ አንዳንዶች እንደሚሉት የርዕዮተ አለም ለውጥ ሳይሆን አሁን በልማታዊ መንግስት አማካኝነት እንደ ድልድይ ተጠቅመን ለመድረስ ከሚታሰበው በካፒታል ከበለጸጉ ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የምታደርገው የህዳሴ ጉዞ አንድ አካል ነው፡፡ የሀገራችን የመጨረሻ አላማ እና ግብም ከድህነት ተላቃ በካፒታሊዝም ከበለፀጉ ሀገራት ተርታ መስለፍ ስለሆነ ከልማታዊ መንግሰት ባህሪ ጋር የሚጋጭ እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ በመሆኑም ይህ የፕራቬታይዜሽንም ሆነ እንደ አገር እየተካሄደ ያለው የለውጥ አንቅስቃሴ የመንግስትን ልማታዊ ባህሪ ይበልጥ የሚያረጋግጥ እንጂ ሌላ አንድምታ የሚሰጠው አለመሆኑን ግልፅ ነው፡፡ በተጨማሪም ሀገሪቱ አሁን ለገጠማት ወቅታዊ የኢኮኖሚ ጫናም እንደ መፍትሄ ከመሆን ባለፈ ላለፉት 15 አመታት የተመዘገበውን የለውጥ ጉዞ አሁን ካለበት ደረጃ በተሻለ ፍጥነት እንዲፈጻም የሚያሰችል ነው፡፡

No comments:

Post a Comment