EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Thursday, 8 February 2018

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ተቋማት እይታ

(በስንታየሁ ግርማ)
የኢትዮጵያ እድገትና ልማት እውቅና በአለም አቀፍ ደረጃ እንደቀጠለ ነው፡፡ግሎባል ሪስክአለም አቀፍ ሁኔታዎችን በጥልቀት እየዳሰሰ በየአመቱ ሪፖርት የሚያዘጋጅ በለንደን የኢኮኖሚ /ቤት የተቋቋመ ተቋም ሲሆን የፖለቲካ ስጋቶችን፣ ዜናዎችንና ትንታኔዎችን የሚያቀርብበት ህትመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ከቀዳሚዎቹ የሚመደብ ነው፡፡ ይህ ተቋም በዚህ ሳምንት “Under the radar; Ethiopia’s Economic Growth Offers Opportunities and challenges” በሚል ርዕስ ባወጣው መጣጥፍ ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ... 1945 ሲቋቋም ከመስራች አገራት መከከል አንዷ መሆኗን ብዙዎች ይዘነጉታል ብሏል፡፡

እናም የአለም የገንዘብ ድርጅት ማኔጅንግ ዳይሬክተርን ወደ አዲስ አበባ ለመሣብ 72 አመታት ፈጅቶባታል ይላል፡፡ በቅርቡ የክርስቲያን ላግራድ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ግን የኢትዮጵያን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማሣያ ነው ብሏል ተቋሙ፡፡ አክሎም ... 217 ጀምሮ ኬንያን በመብለጥ የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ሃያል መሆኗን ገልፆ 225 ወደ መካከለኛ ኢኮኖሚ ለመግባት ትክክለኛው ጐዳና ላይ ትገኛለች ሲል መስክሯል፡፡
ግሎባል ሪስክ አያይዞም ለኢኮኖሚው እድገት የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ሀገሪቱን ከድህነት የማላቀቅ ራዕይና በልማታዊ መንግስት መርህ የሚመራ የተለጠጠ እቅድ ከፍተኛውን አስተዋፅኦ አድርጓል ብሏል፡፡ አክሎም በኢትዮጵያ 2ዐዐዐ የነበረው 44%  የድህነት መጠን 215-16 ወደ 23.5% ዝቅ ማለቱን የአለም የገንዘብ ድርጅትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል መመዘኛ የሆነውን የሰው ሀብት ልማት መለኪያዎችን በማሻሻል በኩል ጥሩ ውጤት አስመዝግባለች ይላል ግሎባል ሪስክ የሴቶች ተሣትፎ እና ድሀ ተኮር ፖሊሲዎችን በመጥቀስ፡፡
በከፍተኛ የመሠረተ ልማት ወጪ በማተኮር ኢትዮጵያ የቀጠናው የማምረቻ ኢንዱስትሪ ማዕከል እየሆነች ነው ሲልም አክሎበታል ግሎባል ሪስክ፡፡ ይህ ደግሞ በተፈጥሮ ሀብት ላይ ከተንጠለጠለው  የሌሎች ሀገራት እድገት የተለየ እንደሚያደርገው፤ ትምህርትም ሊወሰድበት እንደሚገባ ያስገነዝባል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በምሣሌነት በማንሳት ግድቡ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኤክስፖርት በማድረግ ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ አገር ያደርጋታል ብሏል፡፡

የአገሪቱ መሠረተ ልማት ኢንቨስመንት የቻይና ኢንቨስተሮችን ተመራጭ ማድረጉን በማተት ግሎባል ሪስክ 218 የተመረቀውን የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር 4 ቢሊዮን ዶላር በቻይና የባቡር እና የኮንስትራክሽን ድርጅት መገንባቱን በምሣሌነት ይገልፃል፡፡ ከቻይና የመንግስት ኩባንያዎች በተጨማሪ የግል የቻይና ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ 28,000 ኢትዮጵያውያን የሥራ እድል ፈጥረዋል ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ጉልበት ተኮር የኢንዱስትሪ ፖሊሲ በመቅረፅና በመተግበር ብዛት ላለው ህዝቧ የሥራ እድል ለመፍጠር ተጠቅማበታለች ያለው ትንታኔው፤ የኢንዱስትሪ ፓርክ በመመስረትና የአንድ መስኮት አገልግሎትን በመተግበር አላስፈላጊ የቢሮክራሲ ውጣ ውረድን በመቀነስ  ላይ እንደሆነች አትቷል፡፡

በአለም በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት አየር መንገዶች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሌላው መተማመኛ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ አየር መንገዱ በገቢም በትርፍም የደቡብ አፍሪካን አየር መንገድ በመብለጥ ከአፍሪካ የመጀመሪያ ደረጃውን ይዟል በማለት ግሎባል ሪስክ እማኝነትን ይሠጣል፡፡ አየር መንገዱ አለምን ማዳረስ የሚለው ፖሊሲው ውጤታማ አድርጓታል፡፡ ከ12ዐ በላይ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በአለም ላይ ያሉ ቁልፍ ከተሞች ለምሣሌ ሪዮ ዲ ጄኔሮ፣ ለንደን፣ ሻንጋይ፣ ቤጂንግ፣ ዋሽንግተን ዲሲ እና ወደ መሣሠሉት ከተሞች ቋሚ በረራ ያደርጋል፡፡


ይሁንና ግሎባል ሪስክ በኢትዮጵያ የግሉ ሴክተር ደካማ መሆን ስጋት ነው ይላል፡፡ በቴሌ እና በመሣሠሉት ዋና ዋና የኢኮኖሚ ተቋማት ኢትዮጵያ በሯን ለውድድር ክፍት ማድረግ ይገባታል ሲልም ይሞግታል፡፡ በአገሪቱ እያጋጠመ ያለው የሠላም መደፍረስ ከመካከለኛ እና ከረጅም ጊዜ አኳያ አደጋው የከፋ ስለሆነ በኢኮኖሚ እድገቱ የታየውን ተስፋ ለማስቀጠል ስጋቶችን መቀነስ እና ማስወገድ እንደሚገባ አስቀምጧል፡፡ 

ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ዘገባ ይዞ የወጣው የቴዲ ተርነር ንብረት የሆነው .ኤን. ኤን ነው፡፡ ስለ አዲስ አበባ 1 ምርጥ ነገሮች በሚል ርዕሰ አንቀጽ ጀምስ ጀፋሪ ፌብርዋሪ 6/2018 ባወጣው የጉዞ ማስታወሻ መጣጥፍ የኢትዮጵያን ቡና ጥቁሩ ወርቅ” በማለት የገለጸው ሲሆን የኢትዮጵያ ባህል በቡና ይገለጻል ብሎታል፡፡ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው አረቢካ ቡና መገኛ መሆኗንም በማተት በአዲስ አበባ ውስጥ ምርጥ ባህላዊ የቡና ካፊቴሪያዎችና መሸጫዎችን ይዘረዝራል፡፡ ከቡና በተጨማሪ ሀገራዊ ስነ ጥበብ የኢትዮጵያውያን አስደናቂ የባህል ጭፈራ፤ ታሪካዊ ሙዚየሞች፣ የኢትዮጵያውያን ምግቦች፣ የምዕራባውያን ምግቦችም በአማራጭነት መኖራቸው፣ ቅዳሜና እሁድ የሚካሄድ የብስክሌት ስፖርት፣ ምቹ ሆቴሎች፣ በአዲስ አበባ ያሉ ባህላዊና ታሪካዊ የማንነት መገለጫ የሆኑ የመስህብ ቦታዎች እና አማርኛ በአዲስ አበባ በስፋት የሚነገር ቋንቋ መሆን ሌሎች የአዲስ አበባ ከተማ ልዩ መገለጫዎች ናቸው ብሏል፡፡


ዊክኮም የተባለ ተቋም በድረ ገጹ ፌብርዋሪ 5/2018 በአለም ላይ ያልተነካ የወርቅ ሃብት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ባወጣው መጣጥፍ ላይም ብሉክ በተባሉ ፀሃፊ በአሶሳ ዞን የሚገኘው የወርቅ ማውጫ 6000 አመታት በፊት እንደተጀመረና በአለም ላይ ከመጀመሪያዎቹ የወርቅ ቁፋሮ ቦታዎች አንዱ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡ ይህ ቦታ ለጥንታዊቷ ግብጽ የወርቅ ምንጭ እንደነበረ ጸሃፊው አስታውሶ ንግስት ሳባም ለንጉስ ሰለሞን 3000 አመታት በፊት ያቀረበችው ወርቅ ስጦታ ከአሶሳ ዞን እንደተገኘ ያስረዳል፡፡ ከታሪካዊ ዳራ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ያሉ የወርቅ ክምችቶች በአሁኑ ወቅት አለም አቀፍ ኩባንያዎችን እየሳቡ እንደሆነ አስነብቧል፡፡  ዊክኮም አክሎም በኢትዮጵያ ያልተነካ የወርቅ ክምችት በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ ደቡብ አፍሪካን በመተካት ከአለም እስከ 5 ያለውን ደረጃ ለመያዝ ያላትን አቅም በመረጃ አስደግፎ አስቀምጧል፡፡ ይሁንና የመንግስት አላስፈላጊ ቢሮክራሲን መፍታት ዋነኛው ተግዳሮት ነው ይላል፡፡
ብዙውን ጊዜ በህዳሴው ግድብ ምክንያት የተንሸዋረረ ሀሳብ የሚያቀርበው የግብፅ ኢንዲፔንደንት ፌብርዋሪ 1/2018 ግን አወንታዊ ዘገባ ይዞ ወጥቷል፡፡ ጋዜጣው ግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በባቡር መንገድ ለማስተሳሰር ተስማሙ በሚል ርዕሰ ባወጣው መጣጥፍ መሰረት ሦስቱ ሀገራት ለመሰረተ ልማቶች የጋራ ፈንድ አቋቁመዋል ብሏል፡፡ ጋዜጣው አክሎም የህዳሴው ግድብ ሊያስከትል የሚችለውን ቀውስ በመፍታት የኢትዮጵያ መሪዎች ስኬትን አስመዝግበዋል ይላል፡፡ የጋራ የፖለቲካ፣ የፀጥታና የቴክኒክ ኮሚቴ ለማቋቋም ሶስቱ አገራት መስማማታቸውን በተጨማሪ ዘግቧል፡፡ 
ዘገባዎቹ በየተቋማቱ ላለን የህዝብ ግንኙነት መዋቅሮች የሚያስተላልፉት መልዕክት አላቸው፡፡ የመጀመሪያው በአለም አቀፍ ደረጃ ለምናካሂደው የህዝብ ግንኙነት ስራ ሊያግዙን የሚችሉ ተቋማት እና ሰዎች /ጋዜጠኞች/ እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ማስቻሉ ነው። በሁለተኛ ደረጃ እነዚህን ተቋማት በተለይም ጋዜጠኞችን በመለየትና ሀገራችንን እንዲጎበኙ በማድረግ ሰፊ የዜናና ፕሮግራም ሽፋን እንዲሰጡን እድሉን መፍጠር እንዳለብን የሚያስገነዝበን ነው።  በሦስተኛ ደረጃ ከመሰል ከአለም አቀፍ ተቋማት የሚወጡ ዜናዎችን እና ትንታኔዎችን በመከታተል በአገር ውስጥ ባሉ የመገናኛ ብዙሃን ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ የዘነጋንውን ሃላፊነታችንን የሚያስታውሱ ናቸው። በየተቋሞቻችን ባሉን ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ተደራሹን ማእከል ያደረጉ መረጃዎችን ለማቅረብ በምናደርገው ጥረትም ጠቃሚ ግብዓት ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው፡፡

3 comments: