EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Wednesday 5 October 2016

ያልተሳካው የእነ ጃዋር የጥፋት ድግስ!!


(በኢቢሲ)
የኢሬቻ በዓልን ባህላዊ አከባበር ጠብቆ ለማክበር የኦሮሞ ህዝብ፣ አባገዳዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሰፊ ዝግጅት ቢያደርጉም በሁከት ፈጣሪ ኃይሎች ምክንያት መስተጓጎሉ የሚታወስ ነው፡፡ በዓሉን ለማወክ አስቀድመው የተዘጋጁ ኃይሎች ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ ግርግር በመረጋገጥ የሰው ህይወት መጥፋቱ ይታወቃል፡፡
ከሁከቱና ብጥብጡ ጀርባ በጃዋር መሀመድ የሚመራው የጥፋትና ሀገር የመበታተን አጀንዳ ያለው ኃይል መኖሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የጥፋት ኃይሉ ከሁከቱና ግርግሩ በስተጀርባ መኖሩንና አመራር ይሰጥ እንደነበር የሚያሳዩ መረጃዎችን ከታች አንድ በአንድ እንመለከታለን፡፡
የጥፋት ሀይሉ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ብቻ አላበቃም፡፡ ሁከቱን ለማጉላትና በመንግስት ኃይሎች ላይ ለማላከክ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ነበር፡፡ የጥፋት ኃይሉ ተልእኮ የበዓል ስነ ስርዓት ላይ ታድመው የዘገቡ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋዜጠኞችንም እስከ መዝለፍ የደረሰም ነበር፡፡ በጃዋር የሚመራው የጥፋቱ ኃይል የውጭ ሚዲያዎችን ዘገባና ራሱ ዘጋቢዎችን ወይም የውጭ ሚዲያ ጋዜጠኞችን እንዴት ያጥላላ እንደነበር በማስረጃ በማስደገፍ እናሳያለን።
በኦሮሞ ህዝብ ልዩ የባህል መገለጫ በሆነው የኢሬቻ በዓል ከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ተውጣጥተው እንዲመጡ ያደረጋቸው የጥፋት ሃይሎች መታወቂያ ሳይዙ ወደ በአሉ እንዲገቡ ጃዋር ፖስት በሚያደርጋቸው ጽሁፎቹ በተከታታይ ሲያስጠንቅቅ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ በአሉ ላይ ሁከቱን እንዲመሩ ትእዛዝ የተሰጣቸው ሁከት ፈጣሪዎች ማንነት እንዳይታወቅ ለማድረግ እንደነበር ግልፅ ነው። ይህም ሁከቱ ታቅዶ ይከናወን እንደነበር አንዱ ማሳያ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሰላምና ልማት ከማይጥማቸው ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ያነገቡት እነ ጃዋር ለሁከት ተግባራቸው ያግዘናል ብለው ያሰቡትን ኃይል ከሌሎች ክልሎች ጭምር በማስመጣት ኢሬቻ በዓል ላይ እንዲሳተፉ አድርገዋል፡፡ ጃዋር በዓሉ ላይ የተገኙ የጥፋት ኃይሉ ወኪሎች ከሌሎች ክልሎች የመጡትን ተልዕኮ አስፈፃሚዎች ቃለ ምልልስ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ይወተውት ነበር፡፡
የውጭ ኃይሎችን ተልዕኮ ለማስፈፀም በጃዋር የሚመራው የጥፋት ኃይል ያነሳው ሁከትና ግርግር የተፈለገውን ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ የተፈጠረውን ጉዳትማጉላትና በፀጥታ ኃይሉ ለማላከክ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፡፡ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይል የኢሬቻ በዓል ክብርና ሞገስ እንዳይጐድፍ ሁከት ፈጣሪዎችን መታገስ ከሚገባዉ በላይ መታገሱ ከስፍራው የወጡ ቪዲዮዎች በግልፅ ያሳያሉ፡፡ እነሱ ግን አልተሳካካላቸውም እንጂ በሁከቱና ግርግሩ የተጐዱና ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎችን በፀጥታ ኃይል ተተኩሶ የተገደሉ ለማስመሰል ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡
የጥፋት ኃይሉ ይህ ሳይሳካለት ጊዜ በስፍራው ተገኝተው ትክክለኛውንና እውነተኛውን እማኝነት ይሰጡ የነበሩ ግለሰቦችን ለማሸማቀቅ እና ለማጥላላት ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ የማጥላላትና የማሸማቀቅ ዘመቻው በዜጐቻችን ላይ ብቻ የታጠረ አልነበረም፡፡ ሁነቱን ለመዘገብ በቢሾፍቱ የተገኙ አለም አቀፍ የሚዲያ አውታሮችንና ጋዜጠኞቻቸው ላይ ያነጣጠረም ነበር፡፡ የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች በህዝቡ ላይ ምንም ዓይነት ጥይት አለመተኮሳቸውና አደጋው የደረሰው በመረጋገጥ (Stampede) መሆኑ ሲዘገብ እንዲሁም ሁከት ፈጣሪዎቹ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ድንጋይ፣ ጠርሙስና የመሳሰሉ ቁሳቁችን ቢወረውሩም የፀጥታ ኃይሎች ግን በከፍተኛ ትእግስት ማሳለፋቸውን እማኝነታቸውን ሲገልፁ የስድብ ናዳ ወርዶባቸዋል፡፡ ለአብነት የጥፋት ኃይሎች መሪ ጃዋር መሀመድ በአለም አቀፍ ዜና አውታር ጋዜጠኞች ላይ የሰነዘረውን ስድብና ዘለፋ የሚከተለውን ይመስላል፡፡
“ቢቢሲዎች ማፈሪያ ናችሁ። እንዴት ዓይነት ቆሻሻ ሪፖርት ነው ያቀረባችሁት፡፡ የትኛው ሪፖርተራችሁ ነው እንዲህ ብሎ የዘገበው?”


“ቢቢሲዎች፣ እውነት እነዚህ ሰዎች ፖሊስ ላይ ድንጋይ ወርውረዋል? እውነት እነዚህ ሰዎች የሚተናኮሉ ይመስላሉ? ለመሆኑ ሄሊኮኘተሮች አስለቃሽ ጋዝና ጥይት ሲተኩሱ ጋዜጠኞቻችሁ የት ነበሩ?”

ጃዋር  ወደ ዋሺንግተን ፖስት ደግሞ ፊቱን ያዞራል
"ዋሺንግተን ፖስቶች ይህን ደደብ ሪፖርታችሁን አስተካክሉ፡፡ ዋናው ምክንያት የሰዎች መረጋገጥ አይደለም። ሰዎች ከጦር መሳሪያ ከሚወጣ ጥይትና ከሄሊኮፕተር ከሚረጭ አስለቃሽ ጋዝ ያደረጉት ሩጫ ነው። ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ በቪአይፒ ማረፊያቸው ተከማችተው የነበሩ ዲፕሎማቶችንና የውጭ ጋዜጠኞችን ጠይቁ፡፡ ሁሉንም ነገር አይተዋል፤ ቀርፀዋል። ለመናገር ፈቃደኛ አይደለም እንጂ፡፡"

በጃዋር የሚመራው የጥፋት ኃይል ሀገር ለማተራመስ የማይፈነቅለው ድንጋይ ላለመኖሩ ሌላ ማሳያ መቀመጫውን አሜሪካ ኒውዮርክ ባደረገው ብሉምበርግ ለተሰኘው አለም አቀፍ ሚዲያ ሪፖርተር ከሆነው ዊልያም ዴቪሰን ጋር በጃዋር ፌስ ቡክ ገጽ ያካሄዱት ክርክር ነው፡፡ በዚሁ በፌስቡክ ምልልስ የብሉምበርጉ ጋዜጠኛ ጃዋር "በሄሊኮኘተር በታገዘ ጥይት ታዳሚዎች ተደብድበዋል" ያለውን መሰረተ ቢስ ወሬ በእውነተኛ ማስረጃ አስደግፎ ይሞግታል፡፡ የጽሑፍ ምልልሱ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ጃዋር፣ "የፀጥታ ኃይሎች ከምድርና ከሰማይ ሆነው ደማቁን በዓላቸውን በማክበር ላይ ባሉ አራት ሚሊዮን ያልታጠቁ ሲቪሎች ላይ እየተኮሱ ይገኛሉ፡፡ ተመጣጣኝ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል።”


ዊሊያም ዴቪሰን ጃዋር፣ እስኪ በመረጃ አስደግፈህ ተናገር፤ ሄሊኮኘተር በታዳሚዎቹ ላይ ሲተኩሱ የሚያሳይ ምን መረጃ አለህ?”
ዊሊያም ዴቪንሰን በፌስ ቡክ ገፁ እንዲህ ሲል ሁኔታውን ለጃዋር ገልፆታል።
“ጃዋር መሃመድ፤ እኔ እዛው ቦታው ላይ ነበርኩ፣ ሰዎች ሲረጋገጡ በአይኔ አይቻለሁ። ይህን የማይካድ ሃቅ ብለው ስህተት አይሆንም። ሲቀጥል ደግሞ。。እዚህ ጋር ዋናው ጉዳይ ምንደን ነው? ፖሊስ ጥቃት እየደረሰበት አልነበረም እያልክ ነው እንዴትልቅና ጉልበት የተቀላቀለበት ስሜታዊ ተቃውሞ ነበር። ፖሊስ ተው በሚልበት ጊዜም ተቃዋሚዎቹ አሻፈረኝ ብለው ሃያ ሜትር ያክል ወደፊት በመቅረብ መድረኩ ስር ደርዋል። እንደውም አዘጋጆቹ የተቃዋሚዎች ስሜት ያን ያክል ይደርሳል ብለው ስላልገመቱ ይመስለኛል ያን ያክል አሰቃቂ አደጋ የደረሰው።”

ጃዋር በነዚህ ሚዲያዎች የተበሳጨው እሱ የፈለገውን ሳይሆን በስፍራው የነበረውን እውነታ ብቻ በመዘገባቸው ነው። ይህን የሃሰት ውንጀላውን ለመደበቅ ሲል ደግሞ ሌላ ፈጠራ ተጠቅሟል፤ መንግስት በገንዘብ ደልሏቸዋው ነው የሚል። ይህ ክስ ፈጠራ እንጂ እንዳለው መረጃ ቢኖረውማ ያንኑ ይዞ ለማራገብ ማንም ባልቀደመው ነበር።

"በውጭ ጋዜጠኞች በጣም የተበሳጨሁት ለምን መሰላችሁ? 30 በላይ ጋዜጠኞች በስፍራው ተገኝተው ጭፍጨፋውን አይተዋል፤ ግን አንዳቸውም ያዩትን ነገር አልዘገቡም፡፡ ለምን? የሆቴልና የጉዞ ወጪ በመንግስት ስለተሸፈነላቸው ነው። እስኪ አልተሸፈነልንም ይበሉኝ። በመረጃ አጋልጣቸዋለሁ።”
በጃዋር የሚመራውን የጥፋት ኃይል ጨምሮ የውጭ ኃይሎች ተልዕኮ ተቀብለው ሀገር የማተራመስ ተግባር የሚያከናውኑ ኃይሎች ግባቸውን ለማሳካት ምንም ዓይነት ነገር ከማድረግ ስለማይቦዝኑ እንደ አይን ብሌናችን የምንሳሳላትን  ሀገራችንን ለመጠበቅ ከምንም ጊዜ በላይ ትኩረት የምናደርግበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡

6 comments:

  1. Why tear gassing at all? Is that not possible for the security officers just to go away from the place??

    ReplyDelete
  2. Do you have any idea how important the Aba Gedas and the elders on that stage are for their followers and the majority Oromos in general? More important than the country's leader! Who knows what could have happened if those agitated gangsters left unchecked when they rushed to the stage so crazily? Firing tear gas was the best option the security forces had to disperse the unruly crowd and to protect those very important community leaders

    ReplyDelete
  3. Do you have any idea how important the Aba Gedas and the elders on that stage are for their followers and the majority Oromos in general? More important than the country's leader! Who knows what could have happened if those agitated gangsters left unchecked when they rushed to the stage so crazily? Firing tear gas was the best option the security forces had to disperse the unruly crowd and to protect those very important community leaders

    ReplyDelete
  4. Nothing would have happened, if there hadn't been any security officers at all. People may chant, scream, travel singing & sleep like a baby at his home.

    ReplyDelete
  5. WHY DO YOU NEED A SECURITY POLICE IN THE WEST , YOU ARE SAYING NO NEED FOR A POLICE WHEN THERE IS BIG EVENT LIKE THAT? ???? COME ON! I LIVE IN EUROPE AND I KNOW WHAT IS GOING ON HERE EVEN FOR A LOCAL EVENTS,,,

    ReplyDelete