EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Monday, 10 October 2016

ኒዬ ሊበራሊዝም ሊክደው ያልቻለ እድገት

(በስንታየሁ ግርማ)
ዘኢኮኖሚስት መፅሄት የኒዬ ሊበራሊዝምን ሀሳብ በማፍለቅና በማቀንቀን ቀዳሚ ነው፡፡ የሳይንስ አምዱ ሳይቀር በቀላል ቋንቋ የሚፃፍ በመሆኑ በአለም ላይ ተነባቢነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ .. 2014 ብቻ 59 ሚሊዬን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን መረጃዎች ያሳያሉ። በዚህ በኦንላይን የሚዲያ ዘመን ይህንን ያህል ትርፍ ማግኘት ምን ያህል ተነባቢ መፅሄት እንደሆነ ያሣያል፡፡ መፅሄቱ ተነባቢነት ያለው በኒዬ ሊበራሊዝም ርዕዬተ አለም ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ከዚህ ተቃራኒ ርዕዮተ አለም በሚከተሉትም ነው፡፡

ዘኢኮኖሚስት ነፃ ንግድን፣ ግሎባላይዜሽንን ነፃ የጉልበትና የፋይናንስ ዝውውርን እንደሚደግፍ ከፅሑፋ መረዳት ይቻላል፡፡ ካርል ማርክስ ዘኢኮኖሚስትን “The European organ of the aristocracy of finance” ይለው ነበር። ለሮናልድ ሬጋን እና ማርጋሬት ታቸር ዘኢኮኖሚስት ከፍተኛ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡ አሜሪካ በቬትናም፣ በኢራቅ እና በአፍጋኒስታን ያደረገቻቸውን ጦርነቶች ደግፎ ፅፏል።
መፅሄቱ የዋና አዘጋጁን ወይምሪፖርተሩን፣ ወዘተ.. ስም አያወጣም፡፡ ይህ የሚያሣየው በመፅሄቱ የሚወጡ መጣጥፎች የግለሰቦች ሳይሆኑ የመፅሄቱ መሆናቸውን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ የኒዮ ሊበራሊዝም አቀንቃኝ የሆነው መፅሄት ከሚመራበት አስተሳሰብ እጅጉን በራቀው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ፍልስፍና እየተመራን ያስመዘገብነውን ሁሉን አቀፍ እድገት በግንቦት ወር እትሙ እንዲህ ሲል አወድሶታል።
.. 2016 የአፍሪካ ኢኮኖሚ 3.7% ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምስራቅ አፍሪካ ከአህጉሩ ከፍተኛውን እድገት ታስመዘግባለች፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ 2005 ጀምሮ ባለሁለት አሀዝ እድገት እያስመዘገበች ሲሆን 2016 እድገቱ ይቀጥላል፡፡ የእድገቱ ዋንኛ መሠረት ደግሞ ሰፊ የመንግስት ኢንቨስትመንት ነው፡፡ The Economist, Africa growth May 28, 2016 

ዘኢኮኖሚስት ብቻ ሳይሆን ዘቴሌግራፍ ጋዜጣም ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፍጥነት በማደግ ቁጥር አንድ ሀገር እንደሆነችና ለቱሪዝም ምቹ እንደሆነች ‘Where to stay in Ethiopia The best lodges and hotels’ በሚል ርዕስ ባወጣው ኦገስት 4, 2015 እትሙ አስነብቧል። ዘቴሌግራፍ ጋዜጣ በእንግሊዝ የሚታተም ሲሆን ከወግ አጥባቂ ፖርቲ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለው ሲሆን በቀኝ ዘመም ደጋፊነቱም ይታወቃል።
ታዋቂው ፋሪድ ዘካሪያ የሚፅፈበት የታይም መፅሄት በየአመቱ 100 ተፅእኖ አሳዳሪ ሰዎችን እና 20ኛው /ዘመን 100 ተፅእኖ አሳዳሪዎችን በአንባቢ በማስመረጥ እና በማሳተም የሚታወቅ ነው፡፡ ‘Forget the BRICS, Meet the PINEs’ በሚል ርዕስ ማርች 13/ 2014 ባወጣው ፅሑፍ የፊሊፒንስ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ናይጄሪያ እና የኢትዮጵያ እድገት ከብራዚል፣ሲያ፣ ህንድ እና ቻይና እየበለጠ ነው በማለት ፅፏል፡፡
ዘወል እስትሬት ጋዜጣ ስያሜው የወሰደው ከፋይናንስ ገበያ ማዕከሉ ነው፡፡ በአሜሪካ በስርጭት የመጀመሪያው ነው፡፡ ኒዬ ሊበራሊዝም ለገነነበት የሬገን ዘመን Supply side Economics ማለትም አቅርቦት ገበያን ያረጋጋል የሚለውን ሀሣብ ያቀነቅን ነበር፡፡ ዘወል እስትሬት በኒዬ ሊበራል ሀሳብ አራማጅነቱ የታወቀ ጋዜጣ ነው፡፡ እሱም “WhY made in Ethiopia could be the next made in China’ በሚል ርዕስ በሜይ 15/ 2014 ባወጣው ፅሑፍ ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ አውሮፖ እና አሜሪካ ለመላክ ዋንኛ አማራጭ እንደምትሆን ምስክርነቱን ሰጥቷል። በአለም ታዋቂ የሆነው ሑጃን የተባለ የቻይና ኩባንያ በሚቀጥሉት አመታት 2 ቢሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ በጫማ ፋብሪካ ኢንቨስት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለዚህ በማሳያነት አቅርቧል።

ኒዮርክ ታይምስ በአሜሪካ ከዎል ስትሬት ጆርናል ቀጥሎ በስርጭት ሁለተ ነው። የተለያዩ ሽልማቶችን በማግኘት ግን የመጀመሪያ ነው፡፡ ባለሪከርዱ ጋዜጣ በመባል ያንቆለጷጵሱታል፡፡ ጋዜጣው ‘Is the era of great famine over?’ በሚል በሜይ 8/ 2016 ባወጣው ፅሑፍ ኢትዮጵያ ድርቅ ወደ ረሃብ እንዳይቀየር የረዳት ሰላም ያለባት፣ ግልፀኝነት የሰፈነባትና፣ በጥንቃቄ የታቀዱ እቅዶች ባለቤት በመሆኗ ነው ብሏል፡፡ ጋዜጣው አክሎም ድርቅ ወደ ረሃብነት የሚቀየረው በህዝብ ብዛት እና በተፈጥሮ ችግር ሳይሆን በፖለቲካ ጉድለት መሆኑን ኢትዮጵያ አሳይታለች ይላል፡፡ “Famine is Not caused by over population, and as Ethiopia experience shows, it is not a necessary consequence of drought, politics creates famines, and politics can stop it.”
የአለም ባንክ በማደግ ላይ ላሉ ሀገሮች ለካፒታል ኘርግራም የገንዘብ ድጋፋ ለመስጠት በሚል አላማ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ ይሁንና  በውሳኔ አሰጣጡ የአሜሪካ ከፍተኛ ተፅእኖ ያለበት እንደሆነና የምዕራባውያንን በተለይም የአሜሪካ መንግስትን ጥቅም በሌሎች ሀገሮች ላይ እንደሚጭን የቀድሞው የባንኩን ኢኮኖሚስት ጁሴፍ ስትግሊዝ ጨምሮ በምሁራን ይተቻል። ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ባልተገነባበት ሁኔታ የባንኩ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች ተግባራዊ የሚሆኑ ከሆኑ ከፍተኛ ጉዳቶች ያደርሳሉ በሚል የኢኮኖሚስት ባለሙያዎች ይወቅሱታል።
ያም ሆኖ የቀድሞው የባንኩ ዳይሬክተር ኤነረስ ስብተር በተለምዶ የኢኮኖሚ እድገት የሚለካበትን መንገድ በመሞገት አዲስ 49 መለኪያዎችን በመጠቀም 149 ሀገሮችን ሁኔታ ዳስሰዋል፡፡ ስብተር እንደሚሉት የኢኮኖሚ እድገት መለካት ያለበት ለሰዎች ሁለንተናዊ እድገት ባደረገው አስተዋፆ ልክ መሆን አለበት፡፡ እድገቱ ለህዝቡ ጥቅም አስገኝቷልን? የሚለው መታየት አለበት ይላሉ። በእሳቸው መለኪያዎች መሠረት በተለያዩ ሀገሮች አስገራሚ ውጤቶች ቢኖ ሁለንተናዊ ለውጦችን በማስመዝገብ ኢትዮጵያ ቀዳሚ ናት ይላሉ፡፡ ይህንንም ሌላው የኒዮ ሊበራሊዝም አቀንቃኝ ሚዲያ የሆነው ቢቢሲ በጁላይ 2016 ዘገባው ‘The Economic league table where Rwandans and Ethiopian Shine’ በማለት አስፍሮታል።

የኢትዮጵያ እድገት እና ልማት የበርካታ ሀገር ኢንቨስተሮችና መሪዎችን ትኩረትም እየሳበ ነው፡፡ የተለየ ርዕዮተ አለም ያላቸው ሀገሮች መሪዎች ከባለሀብቶቻቸው ጋር በመሆን ሀገራችንን በመጐብኘት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ልማት ተሰሚነቱና ተቀባይነቱ እያደገ ነው፡፡ ሀገራችን የፀጥታው /ቤት ተለዋጭ አባል ሆና መመረጧ ለዚህ ማሳያ ይሆናል፡፡ እስራኤል በአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ለመሆን ኢትዮጵያን ማሣመን አስፈላጊ መሆኑን በማመኗ // ኔታናንያሁን ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት ልካለች፡፡ ህንድ እና ብራዚል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው /ቤት አባል ለመሆን ለአፍሪካ ህብረትም አንድ ድምፅ በመስጠት ይገባል ይላሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያን ማሣመን የአፍሪካ ህብረትን ማሳመን ነው ብለው ያምናሉ፡፡
የኢኮኖሚ እድገታችንም ሆነ አለም አቀፍ ተሰሚነታችን መሠረቱ ኢህአዲግ በተለይም በታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ መሪነት የነደፋቸው እና ተግባራዊ ያደረጋቸው ሀገር በቀል ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ናቸው፡፡ በተሃድሷችን ነጥሮ በወጣው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሰት አስተሳሰብ እንዲሁም በተግባር ተፈትነው ስኬታማ መሆናቸው በተረጋገጡት ፖሊሲና ስትራቴጂዎቻችን እየተመራን መጓዝ ከቻልንና በአፈፃፀም ረገድ ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች ማስወገድ ከቻልን የተለምነው ራዕይ ከዳር የማይሳካበት፣ ሕዳሴያችንንም የማይረጋገጥበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡

No comments:

Post a Comment