በኢህአዴግ መሪነት አንፃባራቂ
ድል ከተመዘገበባቸው የማህበራዊ
ልማት መስኮች የጤናው
ዘርፍ አንዱ ነው፡፡
በሀገራችን በመከላከል ሊቀሩ
በሚችሉ በሽታዎች የተነሳ
ዜጎች ለህልፈት ይዳረጉ
እንደነበር መላው ህዝባችን
የሚያስታውሰው ነው፡፡ ባለፋት
ሁለት አስርት ዓመታት
በኢህአዴግ መሪነት ስራ
ላይ የዋለው መከላከልን
ማዕከል ያደረገው የጤና
ፖሊሲ ግን ይህን
ስር የሰደደ ችግር
በመሰረታዊነት ቀይሯል፡፡
ፖሊሲው ቀደም ሲል
ህዝቡን ሲያጠቁ የነበሩ
በሽታዎችን በመከላከል አምራች
ማህበረሰብን በመፍጠር ረገድ
ስኬታማ ስራ እንዲከናወን
ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፡፡
የጤና ኬላዎች እስከ
ሩቅ ገጠሮች ድረስ
በማዳረስና የጤና ኤክስቴንሽን
ባለሙያዎችን በሁሉም ቀበሌዎች
በመመደብ ህብረተሰቡ ጤናውን
እንዲጠብቅ ማስገንዘብ፣ የጤና
ክትትል እንዲደረግለትና ህክምናም
እንዲያገኝ ማድረግ ተችሏል፡፡
የእናቶችና ህፃናት ሞት
በመቀነስ እንዲሁም ተላላፊ
በሽታዎችን በመከላከል ረገድ
መላው ህዝባችንን ተጠቃሚ
ያደረጉ አንፀባራቂ ድሎች
ተመዝግበዋል። የእነዚህ ድምር
ውጤትም አርሶ አደሩ
ሙሉ ጊዜውንና ጉልበቱን
በስራ ቦታው ላይ
እንዲያውል ያስቻለ ነው።
ይሁንና ተቃዋሚ የፖለቲካ
ፓርቲዎች በተለመደ ‹‹ሁሉንም
ነገር መቃወም›› መርሃቸው
እየተመሩ በመስኩ የተገናፀፍናቸውን ድሎች
ሲክዱ ይታያሉ፡፡ በጤና ልማት መስክ ላይ
ትኩረት አድርጎ በተደረገው
የፖለቲካ ፓርቲዎች
ክርክር ላይም ተቀዋሚዎቹ
ይህንኑ አንፀባርቀዋል፡፡ ፓርቲዎቹ
መከላከልን ማዕከል ያደረገውን
ፖሊሲ የተቹ ሲሆን
አማራጭ ብለው የሚያቀርቡት
ደግሞ የህክምና ተቋማትን
መገንባት ላይ ትኩረት
ያደረገ ነው፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲዎች አማራጭ
የጤና ሳይንሱን ቀርቶ
ህዝባችን በተለምዶ "ታሞ
ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ" በሚል ተመራጭነቱን ያረጋገጠውን
አስቀድሞ የመከላከል ስልት
ምንነት እንኳን ጠንቅቀው
ያልተረዱት መሆናቸውን ያሳያል።
መከላከልን መሰረት ያደረገ
የጤና ፖሊሲ ማለት
የህክምና አገልግሎትን የማይፈቅድ
ወይም የማያሟላ ማለት
አይደለም። አንድ ሰው
ጤናው ሳይታወክ መከላከል
የተሻለ አማራጭ ሲሆን
ቢታመም ደግሞ ተገቢውን
ህክምና የሚያገኝበት የህክምና
ተቋም መኖር አለበት፡፡
ኢህአዴግ የተከተለው ፖሊሲ
የህክምና አገልግሎትን ለማስፋፋትም
ትልቅ ትኩረት የሰጠ
በመሆኑ በዚህ ረገድም
ትልቅ ስኬት የተገኘበት
ነው፡፡
በአገራችን በ1983 ዓ.ም የነበሩትን 72 ሆስፒታሎች
በአራት እጥፍ አድገው
311 የደረሱት፤
በዚሁ ወቅት የነበሩት
153 ጤና
ጣቢያዎች ከሃያ ሁለት
እጥፍ በላይ አድገው
3 ሺህ
541 የደረሱት፣
ከ16ሺ251 በላይ
የጤና ኬላዎች ተገንብተው
አገልግሎት በመስጠት ላይ
የሚገኙት ኢሕአዴግ በመከላከል
ሊቀሩ ያልቻሉ በሽታዎች
በህክምና መፍትሄ ሊያገኙ
እንደሚገባቸው ስለሚያምን ነው።
በአንዳንድ ህክምና ተቋማት
የሚታየው የአግልግሎት አሰጣጥ
መጓደል ሌላው ተቃዋሚ
ፓርቲዎች ፖሊሲያችንን በማጣጣል
ለፖለቲካ ፍጆታነት የሚጠቀሙበት
ጉዳይ ነው፡፡ በመስኩ
አስደናቂ እምርታ የተገኘውን
ያህል አሁንም ከህክምና
ተደራሽነትና ከአገልግሎት ጥራት
ጋር ተያይዞ ችግሮች
መኖራቸው እሙን፡፡ በኢህአዴግ
የሚመራው መንግስት ግን
በዘርፉ በአቅም ማነስ
ይሁን በመልካም አስተዳደር
ምክንያት የሚያጋጥሙ የጥራትና
አቅርቦት መጓደሎች እንዳሉ
ተገንዝቦ ችግሮቹን ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡
ኢሕአዴግ አሁንም መላው
ህዝብ ተገቢውን የህክምና
አገልግሎት በአቅራቢው እንዲያገኝ
የተጀመረውን ጥረት አጠናክሮ
ማስቀጠል ትኩረት የሚሰጥበት
ጉዳይ ነው፡፡ የህክምና
ተቋማት በስፋት ከማዳረስ
በተጨማሪ የባለሙያዎች አቅም
የማሳደግና የህክምና መሳርያዎች
የማሟላት ስራ አጠናክሮ
ይቀጥላል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲወች ግን
የጥራትና አቅርቦት መጓደሎቹን
ከመጠን በላይ በማራገብና
የችግሮቹን ምንጭ አዛብተው
በማቅረብ የችግር እንጂ
የመፍትሄ አካል አለመሆናቸውን ዳግም
አረጋግጠዋል።
No comments:
Post a Comment