በቸነነም
ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ የደርግን መንግስት ለመፋለም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው በረሃ በነበሩበት ጊዜ የ1977 ዓ.ም አስከፊ ድርቅን አስመልክቶ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ በሰጡት ቃለምልልስ "ዛሬ በህይወቴ በጣም ያዘንኩበት ግዜ ነው። በጣም ፈታኝ የሚባሉት ግዜያትን አሳልፌያለሁ፡፡ እንደዛሬ ግን ተስፋ የቆረጥኩበት ወቅት የለም፡፡ እና ለምን እዋጋለሁ፣ የምዋጋላቸው ሰዎች እኮ በረሀብ እየሞቱ ነው። እነዚህ ህዝቦች ጠንካሮች ናቸው ነገር ግን ዘመናዊ የእርሻ ዘዴ ባለመኖሩና ድጋፍ ስላልተደረገላቸው እየሞቱ ነው። በራሳቸው ችግር ግን አይደለም።" በማለት ተናግረው ነበር፡፡ አቶ መለስ ለአገራቸው ምን ራዕይ ነበራቸው? ለሚለውን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እስከዚች በሂወታቸው እጅግ እስካዘኑባት ቀን ድረስ ወደኋላ ዞር ብሎ ማሰብን ይጠይቃል፡፡
ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ የደርግን መንግስት ለመፋለም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው በረሃ በነበሩበት ጊዜ የ1977 ዓ.ም አስከፊ ድርቅን አስመልክቶ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ በሰጡት ቃለምልልስ "ዛሬ በህይወቴ በጣም ያዘንኩበት ግዜ ነው። በጣም ፈታኝ የሚባሉት ግዜያትን አሳልፌያለሁ፡፡ እንደዛሬ ግን ተስፋ የቆረጥኩበት ወቅት የለም፡፡ እና ለምን እዋጋለሁ፣ የምዋጋላቸው ሰዎች እኮ በረሀብ እየሞቱ ነው። እነዚህ ህዝቦች ጠንካሮች ናቸው ነገር ግን ዘመናዊ የእርሻ ዘዴ ባለመኖሩና ድጋፍ ስላልተደረገላቸው እየሞቱ ነው። በራሳቸው ችግር ግን አይደለም።" በማለት ተናግረው ነበር፡፡ አቶ መለስ ለአገራቸው ምን ራዕይ ነበራቸው? ለሚለውን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እስከዚች በሂወታቸው እጅግ እስካዘኑባት ቀን ድረስ ወደኋላ ዞር ብሎ ማሰብን ይጠይቃል፡፡
መለስ ዜናዊ በዚህ ቃለምልልሳቸው የአገራቸው አርሶ አደሮች የዘመናዊ የግብርና
ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑና የምግብ ዋስትናቸው እንዲረጋገጥላቸው ራዕይ ሰንቀው እንደነበር ማየት ይቻላል፡፡
ታላቁ መሪ አገራቸውን ከኢኮኖሚ ድቅት፤ ከሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አፈና በማላቀቅ በእድገት ጎዳና እንድትራመድ፤ ሁሉም ብሄሮች፤ ብሄረሶቦችና ህዝቦች ከጭቆና ተላቀው በእኩልነት እንዲኖሩ አልመው ነበር፡፡
ደርግ ከወደቀ በኋላም በህዝብ ተሳትፎና በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ
የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፤ ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፤ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ
ያላት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተደረገው ጥረት ውስጥ
የመለስ የመሪነት ሚና ሁሌም ሲዘከር የሚኖር ነው፡፡
የአቶ መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተቆርቋሪነትና የአመራርነት ሚና በአገር ውስጥ ብቻ
ሳይወሰን በአፍሪካ ቀንድና አካባቢው እንዲሁም በመላው አፍሪካና በአለም ድሃ ህዝቦች ዘንድም አሻራውን ጥሎ ያለፈ ነው፡፡ መለስ
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር፤ የአዲስ አጋርነት ለአፍሪካ እድገት /NEPAD/ የስራ አስፈፃሚ ሊቀመንበር፤ የአለም አቀፍ
ጥምረት ለአፍሪካ ሊቀመንበር እና ሌሎች የሃላፊነት ቦታዎችና ደረጃዎች በሰሩበት ወቅት አፍሪካን ልክ እንደ አገራቸው ኢትዮጵያ
ሳይታክቱ አገልግለዋል፡፡
በቡድን 8 እና በቡድን 20 አገራት ጉባዔዎች አፍሪካን ወክለው ለአፍሪካውያን
ተጠቃሚነት ተከራክረዋል፡፡ በኮፐንሃገኑ የአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ልዑክን በመምራት፤ በ2010 የተባበሩ መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ
ድጎማ አማካሪ ቡድን ሊቀመንበር በመሆን አፍሪካ የአደጉ አገሮች
በሚለቁት በካይ ጋዝ ተጠቂ መሆኗ ኢፍትሃዊ እንደሆነና ለዚህም ካሳ ልታገኘ እንደሚገባት ሃያላን አገራትን ሞግተዋል፡፡
ታላቁ መሪ የቤጂንግ አፍሪካ ሰሚት ሊቀመንበር በሆኑበት ወቅትም አፍሪካውያን
ከእርዳታ ተቀባይነት ስሜት ወጥተው በሰጥቶ መቀበል መርህ ላይ የተመሰረተ አቻ አገራዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ የሚያስችሉ
አማራጮችን አቅርበዋል፡፡ በሰላም ማስከበር፤ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታና በእድገት ፖሊሲ አማራጮች በአገራቸው ያለው ምርጥ
ተሞክሮ ለሌሎች አገራትም እንዲተርፍ ሰርተዋል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ በእነዚህና በሌሎች መልካም ተግባሮቻቸው እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ
ሳንሆን አለም የሚያደንቀው አመራር ሰጥተውን አልፈዋል፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ ከሁለት አመት በፊት ሲያርፉ ይህን አለም
አቀፋዊ እውቅናቸውንና ተደናቂነታቸውን የመገናኛ ብዙሃን በስፋት ዘግበውታል፡፡ በዚህ ጹሁፍ የተለያዩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዜና ህልፈታቸውን ተከትሎ ስለታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ያሰፈሯቸውን ፅሁፎች መለስ ብለን እንዳስሳለን፡፡
እ.አ.አ ነሃሴ 12/2012
የታተመው ታዋቂው ዘ ዋሸንግተን ፖስት ጋዜጣ
“ስለ መለስ ዜናዊ መታወቅ ያለባቸው አምስት ነገሮች” በሚል ርዕስ በድህረ ገጹ ባሰፈረው ጹሁፍ ‹‹መለስ የፖሊሲና የስትራቴጂ መሃንዲስ›› በማለት እርሳቸው በ1983 ዓ.ም የሀገሪቷን መረጋጋትና ቀጣይ እጣፈንታ መወሰን የሚችለው ሰፊው ህዝብ መሆኑን ስለመናገራቸው ጠቅሶ ከጅምሩ ህዝባዊ ስለነበሩ በተገበሯቸው የእድገት ፖሊሲዎች ውጤታማ ሆነዋል በማለት ጽፏል፡፡
የስትራቴጂ እና የአለም አቀፍ ጥናት ማዕከል /CSIS/ በተመሳሳይ ቀን “የመለስ ዜናዊን ሌጋሲ ፍተሻ” በሚል ባስነበበው ጹሁፍ፤ በእርሳቸው የመሪነት ዘመን የአገሪቷ ኢኮኖሚ ለተከታታይ ዓመታት እድገት ማሳየቱን ጽፏል፡፡ ያልተማከለ አስተዳደርና ራስን በራስ ማስተዳደር በእሳቸው ዘመን የተገኙ ውጤቶች
ናቸውም ሲል አትቷል፡፡ የሱዳንና የደቡብ ሱዳንን የመለያየት ሂደት፤ በአቢዬ፤ በዳርፉር እንዲሁም በሶማሊያም የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሀይልን ሚና በአብነት በማንሳት ባለመረጋጋትና በግጭት በሚታወቀው የአፍሪካ ቀንድ በፈፀሙት ተግባር መልካም ዝናን ያተረፉ መሪ ስለመሆናቸው ዘግቧል፡፡ ለቀጠናውና ለአለም ስጋት የሆነውን ሽብርተኝነት በተሳካ ሁኔታ መከላከል
የቻሉ መሪ ሲልም አወድሷቸዋል፡፡ ጹሁፉ በማከልም ‹‹የክፍለ ዘመኑ ኃያሉ ፖለቲከኛ እና ቁርጠኛው መሪ የቡድን ስምንትና ቡድን ሃያ አባል አገራት ጉባኤዎችን ደጋግሞ የረገጠ አፍሪካዊ መሪ›› ብሏቸዋል፡፡ CSIS አገሪቷ የሚሰጣትን ድጎማ በአግባቡ የምትጠቀም በመሆኗ የአሜሪካና የብሪታኒያ የእድገት ድጎማ ዋነኛ ተመራጭ እንድትሆን ያደረጉ እና አዳዲስ መንገዶች፤ ሆስፒታሎች እንዲሁም ትላላቅ የኃይል ማመንጫዎች ተገንብተው ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡና የአገሪቱን ገጽታ እንዲቀየር ያደረጉ መሪ ናቸው በማለት አስፍሯል፡፡
“የመለስ ሌጋሲ በአፍርካ
ቀንድ”
በሚል ርእስ አልጀዚራ ፊት ገጹ ላይ ያሰፈረው የሚኒሶታው ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አብዲ እስማኤል የከተቡት ጹሁፍ ደግሞ ‹‹በሽግግሩ ወቅት የተጋረጠውን የመበጣጠስ አደጋ በመቋቋም ሀገሪቷ አንድ ሆና እንድትቀጥል በማድረጉ ምን ጊዜም የሚታወሱ መሪ›› በማለት ይጀምራል፡፡ በስርዓተ ቀብሩ አያሌ የአፍሪካ መሪዎች የተገኙት ለቁርጠኛው የአፍሪካ ምድር ልጅ፤
ለአፍሪካውያን
እና ለኢትዮጵያውያን ላደረገው መልካም ተግባራት ያላቸውን ክብር እና ምስጋና ለማቅረብም ጭምር እንደሆነ ጠቅሷል፡፡ ጹሁፉ በመቀጠልም የመለስ ሌጋሲ በሀገር ውስጥና በአካባቢው ያለው አንድምታ በማለት የብሄር ብሄረሰብ እኩልነት፤ የመሰረተ ልማት ዝረጋታ፤
የከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት መስፋፋት፤ የማዕድን ልማት፤ የአስከፊ ድህነት ቅነሳና በጋራ ቤቶች ልማት የተገኙ ውጤቶች በበሳል አመራር የተቃኙ የመለስ ትሩፋቶች እንደሆኑ ይገልፃል፡፡
በታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ስልጣን ዘመን ወጥቶ በትግበራ ላይ የሚገኘውን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን
እቅድ
ውጤቶች ላይ ሰፊ ትንታኔ ያስቀመጠው ሶማሊላንድ ሰን የተባለ ጋዜጣ ደግሞ በነሃሴ 2014 የመለስ እረፍት ሁለተኛ ዓመትን አስመልክቶ “መለስ ዜናዊን ለማስታወስ” በሚል ርዕስ ባወጣው ጹሁፉ በተከታታይ ዓመታት የታየው የአገሪቷ ኢኮኖሚ እድገት በቀጠናው ካለው ዓመታዊ አማካይ 5.4በመቶ እድገት በእጥፍ ይበልጣል፤ የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ባወጣው መረጃም ኢትዮጵያ ነዳጅ አምራች ያልሆኑና ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት ተርታ መሰለፍ ችላለች ሲል ያትታል፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ፤
የግብርናና
አገልግሎት ዘርፍ መስፋፋት፤
የመጀመሪያ
ደረጃ የተማሪዎች ቅበላ በአራት ዕጥፍ መጨመሩን፤
የጨቅላ
ህጻናት ሞት በግማሽ መቀነሱ፤ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ማደጉ፤
ኤች
አይ ቪ/ኤድስ እና ወባን የመከላከል ጥረትም በእጅጉ መጠናከሩን አውስቷል፡፡ በአገሪቷ ውስጥ ያልተማከለ አስተዳደር፤ የግል ሚዲያ (ኤፍ ኤም ጣቢያዎች፤ ጋዜጦች እና መጽሄቶች) መስፋፋት፤ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት፤
የሀይማኖት
ነጻነት እንዲሁም በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር መብትም በኢህአዴግ/መለስ ዘመን ተከብሯል ነው ያለው ድረ ገፁ፡፡ ታላቁ መሪ ታላቁ የኢትዪጵያ ህዳሴ ግድብን ለማስጀመር የወሰዱት እርምጃም ለብዙዎች ግርምትን ከመጫር ባለፈ ሌሎች አገራትም ያላቸውን የውሃ ኃብት
እንዲጠቀሙ የማንቂያ ደወል ሆኗል
ሲል ይቀጥላል ፅሁፉ፡፡ በ2012 ብቻ በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች መዳረሻቸውን በኢትዮጵያ ማድረጋቸው፤ ከራሷ አልፎ ለጎረቤቶቿ የተረፈው የአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት አገሪቷን ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል በውጭ ቀጥታ ኢንቨስተመንት ተመራጭ አድርጓታል፤ በዚህ ሁሉ መልካም ተግባር ውስጥ የመለስ አሻራ አርፏል ሲል
ዘግቧል፡፡
ጭፍን ጥላቻን በማስወገድ ምክንያታዊ መሆንን አበክረው ይመክሩ የነበሩት መለስ ዜናዊ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫን ከአዲስ አበባ ለማንሳት የተረባረቡ መሪዎችን በምክንያት በማሳመን የህብረቱ መቀመጫ በኢትዮጵያ እንዲቆይ ያደረጉም ናቸው ሲል አድንቋቸዋል፡፡
የቢቢሲው የአለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ ፒተር ባይልስ በወቅቱ በአዲስ አበባ በመገኘት ሲዘግብ
‹‹ኢትዮጵያውያን “እንኮራብሃለን፤ ሌጋሲህን እናስቀጥላለን” የሚሉ መፈክሮችን አንግበው በየቦታው ይታያሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት የህዝብ ስሜት በአለማችን ለጥቂት መሪዎች ብቻ ነበር፡፡
ይህ
ደግሞ በእሳቸው ዘመን ህዝቡ የልማቱ ተጠቃሚ መሆኑን እና መስመሩን ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኘኝነት ስለሚያሣይ ኢትዮጵያ ከዚህም በኋላ የእድገት ግስጋሴዋን
እንደምትቀጥል ይጠቁማል›› ሲል ዘግቧል፡፡
Always Proud of him. He was such an extraordinary person. He was a true leader in such a way that he inspires everyone who wants the best for Ethiopia to follow him and his vision. He will truly be missed by Ethiopia and all of us.
ReplyDeleteThis comment has been removed by the author.
ReplyDelete