EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Tuesday 14 November 2017

የመቻቻል ባህላዊ እሴቶቻንን እናጎልብት!

(የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር)
ኢትዮጵያ አገራችን 3000 ዓመታት በላይ ባፈራቻቸው የረጅም ጊዜ ታሪኳ ውስጥ አስደናቂና ተምሳሌት ከሆኑ እሴቶቿ ውስጥ የመቻቻልና የመከባበር ባህሏን ዓለም ሁሉ ይስማማበታል፡፡
በመሆኑም የራሳቸው ባህል፣ ወግ፣ ሥርዓት፣ እምነት፣ ማንነት፣ ቋንቋና ታሪክ፣ ሌሎችም መገለጫዎች ያላቸው 80 በላይ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አገር ብትሆንም ልዩነትን ማስተናገድ አቅቷት የተቸገረችበት ጊዜና አጋጣሚ ግን አልነበረም፡፡ ለጥቅማቸው ያደሩ ግለሰቦችና ገዥዎች የሚከተሉት ኢፍትሃዊ የአስተዳደር ችግር ካልሆነ በቀር መነሻው የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የቋንቋ ወይም በሌላ ልዩነት ግጭት አስተናግዳ አታውቅም፡፡


በረጅም ጊዜ ታሪኳ በበርካታ ልዩነቶች ውስጥ አንድነቷን አስጠብቃ ዘመን የማይሽራቸው አስደናቂ ቅርሶች ባለቤት ለመሆን በቅታለች፡፡ ቅርሶቿም የአንድ ሃይማኖት ወይም የአንድ ብሔር ብቻ ሳይሆኑ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሁሉም ህዝቦች የጋራ ዕሴት በመሆናቸው በብዙህነት የመቻቻልና የመከባበር ምሳሌ ለመሆኗ ዐቢይ ማሳያ ናቸው፡፡
የሀረርንና የጎንደርን ህዝብ ዕሴት ብንመለከት መሠረትና ባለቤት የሆኑት ህዝቦቻቸው በብሔርና በሃይማኖት ተመሳሳይ አይደሉም፡፡ ነገር ግን በሁለቱም ቅርስ ከተሞች የየትኛውም ብሔር ብሔረሰብ አባላትና የተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች በኔነትና በተቆርቋሪነት፤ በባለቤትነት፣ በፍቅርና በአንድነት ተከባብረው ኖረውባቸዋል፣ እየኖሩባቸውም ነው::
1400 ዓመት በላይ የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ያለምንም ጥላቻና ግጭት በፍቅርና በአብሮነት ተቻችለው ኖረዋል፡፡ ነገሥታት ያደርጉት በነበረው የግዛት ማስፋትና በውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ይፈጠሩ በነበሩ አለመግባባቶች ውስጥ ነገሮችን ወደ ሃይማኖትና ብሔር ነክ ጉዳዮች ለማዞር ቢሞከር እንኳ የሁለቱም ሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጣልቃ በመግባት የተለመደ የምክርና የማግባባት ጥበባቸውን በመጠቀም ኅብረተሰቡ በመቻቻል እንዲኖር ያደርጉ ነበር፡፡
ዕድሜ ጠገብና አስደናቂ ዘመን አይሽሬ ቅርሶች ተጠብቀው የመኖራቸው ሚስጥር የመቻቻልና የመከባበር ባህላችን ውጤት ነው፡፡ መቻቻልና መከባበር ባይኖር ኖሮ በኅብረ-ብሔራዊት አገራችን ውስጥ በሕዝብ ብዛትም ሆነ በኃይል የተሻለው ብሔርና ሃይማኖት የሌላውን ቅርስና ማንነት አጥፍቶ ኢትዮጵያ የአንድ ብሔርና ሃይማኖት የታሪክና የቅርስ ባለቤት በሆነች ነበር፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፤ ሃይማኖቶች ታሪክና ቅርሶች ባለቤት ከመሆኗ ባሻገር የመቻቻል ድንቅ ተምሳሌት በመሆን በዓለማችን ተጠቃሽ ሃገር ናት፡፡
በዚህ ሰዓት አገራችን አስደናቂ ታሪክ በመሥራት ከድህነትና ኋላ-ቀርነት ለመላቀቅ በእልህና በወኔ በትንሳኤና በሕዳሴ ጉዞ ላይ ትገኛለች፡፡ የሕዳሴ ጉዟችንም በፈጣንና ተከታታይ እድገት የታጀበ ስለመሆኑ ዓለም ሁሉ እየመሰከረው ያለ ሐቅ ነው፡፡ የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድም ሁለተኛ ዓመቱን የያዘ ሲሆን የአገራችንን የኢኮኖሚ ሥርዓት ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት በአስተማማኝ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ በዚሁ ፈጣንና ተከታታይ እድገት ግስጋሴ ከቀጠልን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ጎራ የምንቀላቀልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ መልካም ለውጥ እየመጣና ለወደፊትም እንዲቀጥል በብዙህነት የመቻቻል የመከባበርና የአንድነት ባህላችንን መጠበቅ ስንችል ብቻ ነው፡፡
የአገራችንን ልማትና መልካም አስተዳደር ለማስቀጠልና መልካም ገጽታዋን ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን የባህል ሀብቶቻችንንና የቱሪዝም መዳረሻዎቻችንን በማልማት፣ በመጠበቅና በማስተዋወቅ ኢትዮጵያን በሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ከአምስቱ ተመራጭ የአፍሪካ የቱሪስት መዳረሻ አገራት አንዷ ለማድረግ ራዕይ ይዘን በመሥራት ላይ እንገኛለን፡፡
በዚህም ጉዟችን ዋናው ስትራቴጂካዊ ተግባራችን ቱባ የባህል ሀብታችንን እና ጠቃሚ እሴቶቻችን ከሚሸረሽሩ መጤ ባህሎችና ጎጂ ልማዶች በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ነው፡፡ ከበርካታ ጠቃሚና አስደናቂ የባህል እሴቶቻችን ውስጥ አንዱና ዋናው ደግሞ የመቻቻል ባህላችን ነው፡፡ በብዙህነታችን ውስጥ ያዳበርነው የመቻቻል፣ የመከባበርና የአብሮነት ባህላችን ለማንነታችን ሁሉ መሠረት ነው፡፡ የሕዳሴ ጉዟችንም ሊረጋገጥ የሚችለው ይኸው ባህላችን ሲጠበቅና ሲቀጥል ብቻ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ማንኛውም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊና ሌሎች መስተጋብሮች በመቻቻልና በመከባበር ባህል የተመሠረቱ ናቸው፡፡ በዕድር፣ በዕቁብና በልዩ ልዩ ማህበራዊ ተቋማት ውስጥ የየትኛውም ብሔር/ብሔረሰብና ሃይማኖት ተከታይ ያለምንም ልዩነት በእኩልነት ይሳተፋል፡፡ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በደስታም ሆነ በሀዘን ወቅት ተለያይቶ አያውቅም፡፡ በአንዱ ሃይማኖታዊ ክብረ በዓል ላይ ሌላው መገኘትና ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ መስጂድን በጋራ ተባብሮ መሥራት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ የአገራችን ገበያዎች፣ የትምህርት ተቋማትና መዝናኛዎች ሁሉ መቻቻልና መከባበር የሚሰበክባቸው ሕያው መድረኮች ናቸው፡፡ ባጭሩ ኢትዮጵያ የመቻቻል፣ የመከባበር፣ የፍቅርና የአንድነት ምሳሌ በመሆን በዓለም ተጠቃሽ አገር ናት ማለት ይቻላል፡፡
ይህን በአንክሮ ስንመለከት ከዚህ በላይ ዘመናዊነትና ሥልጣኔ የለም፡፡ እድገት በምጣኔ ሀብትና በቴክኖሎጂ ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን የአስተሳሰብና የጥበብ መስተጋብርም እንጂ፤ የዓለማችን ዘመናዊነትና ሥልጣኔ ምሉዕ የሚሆነው መሠረታዊ የሆኑ ባህላዊ እሴቶችም ተጠብቀው ለትውልድ ሲተላለፉና በህዝቦችና በሰዎች ሁሉ ዘንድ ሠላምና ፍቅር ማስፈን ሲቻል ሠልጥነናል ማለት ነው፡፡ ኅብረ-ብሔራዊት የሆነችው ሀገራችን ለጀመረችው የሕዳሴ ጉዞ መቻቻልና ሰላም ዋስትናችን ነው የምንለውም አብሮ ለመኖር ከመቻቻልና ከመከባበር ሌላ አማራጭ መፍትሄ ሊኖር ስለማይችል ነው፡፡
በመሆኑም በአገራችን የረጅም ጊዜ ታሪክ ውስጥ ያልነበሩና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መታየት የጀመሩትን መሠረታቸውም ሆነ ፍፃሜያቸው ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት የሆኑ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አመለካከቶችና ተግባራትን አስተውለን በተደራጀ መንገድ ታግለን ለማስወገድ የሁላችንም ተግባር ሊሆን ይገባዋል፡፡ ለሁከትና ለሽብር አራማጆች የጀመርነውን የሕዳሴ ጉዞ እንዲያደናቅፉ ዕድል ልንሰጣቸው አይገባም፡፡
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የመቻቻል ቀን በመከባበርና በመቻቻል ላይ የተመሰረተው ፌዴራላዊ ስርዓታችን- ለህዳሴያችን!” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ///ክልል የመቻቻል ምሳሌና ተጠቃሽ በሆነችው በዲላ ከተማ የሚከበር ሲሆን በዓለም 20 ጊዜ በአገራችን ደግሞ 8 ጊዜ በደማቅ ሁኔታ ለማክብር ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ በዓሉን የምናከብርበት ዋና ዓላማም የመቻቻልና የመከባበር ባህላችንን ጠብቀን ለተተኪው ትውልድ እንዲተላልፍ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው፡፡

በአጠቃላይ የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የመቻቻል ቀን ስናከብር ማስተዋል ያለብን ዐቢይ ጉዳይ ኅብረ-ብሔራዊት በሆነች አገራችን ጥንታዊ ሥልጣኔያችንና የሕዳሴ ጉዟችን ስኬት መሠረቱና ዋስትናው በልዩነት ውስጥ መቻቻልና መከባበር በመሆኑ ነው፡፡ በተለይ ወጣቱ ትውልድ የአባቶቹ ድንቅ የመቻቻልና የመከባበርን ባህል በማጎልበት የተጀመረውን የሕዳሴ ጉዞ ዳር የማድረስ ታላቅ አደራ ስለተጣለብን መጤ ባህሎችንና አሉታዊ አመለካከቶችን ልናስወግድ ይገባናል፡፡

1 comment:

  1. a simple message to OPDO officials:

    Do not forget the sacrifices paid by our beloved sisters and brothers and by the Oromo brothers for your present well-being and if not even for your luxurious positions!
    No matter who and where in the country, killings are deplorable! but even more primitive killing methods by Stones and Poles for innocent Tegarus who grew up among you is even more lamentable than all murders in the 21st century?

    Why are they killed?

      Did they host demos against your administration? Did they damage public Properties? but it is said that they have been charged as "OLF supporters"?
    Please give us a break! and change your game!
    we will see if Tigreans or Oromos, are supporters of the OLF and the Metamorphosis OLF are the Juwharian movements in the Diaspora whom they delight your hearts.

             Do not play a double standard

    Anyway, the truth will be revealed sooner or later, but one thing we want to include, please do not ignore the Tigrean people, as we will not do to the OROMO people! hold your words to the people who choose you! Do not play a double standard, as we have observed from some OPDO politicians!

                       Our base is still very strong

    A person or a leader can be weak, but Our People never! so be aware of the consequences of the killing and detention of innocent people.

    Our base is still very strong to meet any challenge! So let us work together to cross the bridge of poverty that has united us for a century! Keep the legacy of the PM Meles, even though he came from Tigray.
    TBT -

    ReplyDelete