EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Thursday 17 August 2017

መለስ ሰብአዊ ፣ ዲሞክራሲያዊ ፣ ፍትሃዊ መሪ !!

                                                    
                                                

 በወጋገን አማኑኤል
1947 ዓ.ም በወርሃ ግንቦት መባቻ በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ የህፃን ልጅ ለቅሶ የመወለድ ብስራትን ይዞ ብቅ አለ  ፡፡ በዚያች የጥቁር ህዝብ ነፃነት ምድር ተምሳሌት በሆነችዉ አድዋ ታሪክ ራሱን ለመድገም ያሰበ መሆኑን ማንም የገመተው አይመስልም ፤ ያኔ ነበር ታላቁ መሪ ወደዚች አለም የተቀላቀለው ፡፡ ስለታላቁ መሪ መለስ ብዙ ሲባል ሰምተናል ፤ ተብሏልም ፡፡ እኔም ወግ ይድረሰኝ ብዮ ብእሬን አነሳዉ፡፡ የታላቁ መሪ ህልፈት ከተሰማ እነሆ ዘንድሮ 5ኛ አመት ላይ ደርሰናል ፡፡ 
                          



በርግጥ ስለ ታላቁ መሪ ብዙ ሊባል ይችላል ፡፡ በጣም ብዙ የሚባሉ ስራዎችን ያለመታከት ለሀገራችን ብሎም ለአፍሪካ እንዲሁም ለአለም አብርክቷልና፡፡ እንደ እኔ  ግን መለስን በአጭሩ መግለፅ ይቻላል የሚል እሳቤ ነው ያለኝ፡፡ በአጭሩ መለስ ሲገለፅ  መለስ ሁሌም ውግንናው ለድሃዉ ማህበረሰብ (disadvantage society) ነው፡፡ ታላቁ መሪ ለምን ለድሃው ወግነ ቢባል ሀብታም እማ የፈለገውን ነገር ለማድረግ ብዙም ድጋፍ አያስፈልገውም ሰለዚህም ነው ለድሃ የሚወግነው፡፡ ይህ ሁኔታ ታዲያ ለእኔ ታላቁ መሪ ምን ያክል ሰብአዊ፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ሰብእና እና አስተሳሰብ ባለቤት መሆኑን ያሳያል፡፡ 

መለስ ለድሃ ይወግናል ሲባል በአብዛኛው በግብርና የተመሰረተ ኑሮ እና ኢኮኖሚ ላላቸው እንደ አፍሪካ ፣ ኤዢያ እና መካከለኛው ምስራቅን  ለመሳሰሉ ሀገራት ዜጎች ጭምር የሚቆረቀር መሪ ነበር ፡፡ በሀገር ውስጥ ብቻ የታጠረ አስተሳሰብን ያራመደ መሪ አልነበረም ፡፡ ይልቁኑ ለሁሉም ጭቁኖች የሚወግን እንጂ፡፡
                                             



መለስ በአየር ንብረት ዙሪያም ያደረገው ተጋድሎ መላዉ አለም ቆም ብሎ እንዲያስብ ያደረገ ነበር ፡፡ መለስ ስለአየር ንብረት ለውጥ ሲያነሳ በአየር ንብረት ለውጡ የሚመጡ ችግሮችን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ሳይሆን ዘላቂነት ያላት ፤ ለሰው ልጆች የምትመች በተለይ ለድሃው እና እንዲሁም ሁሉም አካላቸው በውሃ የተከበቡ በርካታ ዴሰቶች ያሉባት አለማችንን በተፈጠረው የአየር ለውጥ መዛባት እየጨመረ የመጣው የአለም  ሙቀትና የተለያዩ ተፈጥራዊ አደጋዎች እነዚህን ደሴቶች ጭምር ሊያጠፋቸው ስለሚችል ለእነሱም በመቆርቆር ጭምር ነው ፡፡
                            

መለስ የኒዮ ሊበራሊዝምን አስተሳሰብ በተጨባጭ ታግሎ አሁን ባለንበት ሁኔታ በኒዮሊበራል መንገድ ሂደህ ለውጥ እማይመጣበት ጉዞ ነው የሚሆነው ብሎ በድፍረት የወጣ መሪ፣ የፓሊሲ ነፃነት ለድሃው እንደሚበጅ እና እንደሚሰራ በበርካታ መድረኮች ተከራክሯል፡፡ በራችሁን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከፍታችሁ ሃብታችሁን ሽጡ ሲሊ ራሳቸው ለመግዛት ፣ ህጋችሁን ላላ አድርጉ የሚሉ የኒዮሊበራል ጫናዎችን ጭምር ታግሎ ያሸነፈ መሪ ነው ፡፡

ታላቁ መሪ አለም አቀፋዊ ሰላምን አጥብቆ የሚሻ እና የሰላም መኖር ለድሃው በጣም አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነ መሪ ነው ፡፡ እውነትም ነው ድሃው ሰላም ሲኖር ብቻ ነው ከድህነት ለመውጣት  የሚፍጨረጨረው ስለዚህ ለድሃው የሰላም ዋጋው ብዙ ይመስለኛል፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያውያን  በሰላም ማስከበር ግንባር ቀደም ሆነው እንዲሳተፉ ያደረገው ፡፡ ሰላም አስከባሪ ሃይላችን ሲሰማራ ለተጎዱት ዜጎች ለማግዝ ነው፡፡ ታላቁ መሪ ድሃ ተበትኖ ሃይል እንደማይኖራው ያስተማረ ባለምጡቅ ስብዕና ባለቤትም ነው ፡፡ 
                               
   


መለስ ለፍትህ የቆመ መሪ ነው ፡፡ ለፍትህ የቆመ ሲባልም ለሁሉም የአለም ጭቁን ህዝቦች መብት ፣ የተሻለ ህይወት ፣ ለተሻለች አለም ፣እድገት ሽንጡን ገትሮ የተከራከረ በተግባር ያሳየ እና ውጤት ማስመዝገብ የቻለ የምጡቅ ሰብዕና ባለቤት ነው፡፡

 በአጭሩ መለስ ለድሃ የወገነ ፣ ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ ፣ ለፍትህ የቆመ መሪ ነበር ፡፡ መለስ ተጫዋችና የማይጠገብ ቀልዶችን በማምጣት ጥርስ የማያስከድን ሰውም ነበር ይባላል፡፡ መለስ ወደ ትክክለኛ መንገድ የመለሰን  መሪ!  ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማዕታት !

No comments:

Post a Comment