EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Wednesday 14 February 2018

የሰሞኑ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባና አንድምታው


(በስንታየሁ ግርማ)
የኬንያው ስታንዳርድ ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያውያን መኪናመገጣጠማቸው እንደተገረመ ያስታውቅበታል፡፡ ዛዉ ሙሳዩ የተባለው ፀሀፊ በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር በቢሾፍቱ የሚገኘውን የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከጎበኘ በኋላ ባለ አንድና ሁለት ጋቢና ፒክ አፕ እና ስቴሽን ዋገን አይነት ቀላል መኪኖችን ኢትዮጵያውያን ሴቶች አሳምረው ሲገጣጥሙ ተመልክቷል። በእነዚህ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በየቀኑ ስድስት መኪናዎች ይመረታሉ። ሴቶችና ወንዶች ተቀላቅለው በሚሰሩበት በሌላው ረድፍ ደግሞ በየቀኑ 16 ከባድ መኪናዎችን ማምረት የሚያስችል አቅም መገንባቱን ተመልክቷል።
ወደ ቅጥር ግቢው ሲገባ የተመለከታቸው ተደራራቢ አውቶቡሶች እዚህ ግቢ ውስጥ የተመረቱ ስለመሆናቸው ጭራሽ ያልገመተው ይህ ፀሃፊ ፋብሪካው ውስጥ ሲገባ ያየው ነገር ግን አስደንቆታል። ለህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ባለተደራቢ የሸገር አውቶቡሶችን ሲመረቱ አይቷል። ከሰባት ወራት በፊት የተጀመረው ይህን አይነት ምርት እስካሁን 50 ያክል አውቶቡሶችን ለአገልግሎት ማቅረቡን ከተቋሙ ኃላፊዎች መረዳቱን ጽፏል። በፋብሪካው ውስጠ 3500 ያክል ሰራተኞች እንዳሉና ከእነዚህም 40 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውን አስፍሯል።
ዛዉ ሙሳዩ ከጉብኝቱ በፊት በዚህ ፋብሪካ ውስጥ በርካታ ቻይናውያን እንደሚኖሩ ገምቶ ነበር። ሆኖም አንድም እንኳን በግቢው ውስጥ አለመኖራቸውን ሲያይ የተገነዘበው ነገር ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ሽግግር በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ መሆኗን ነው።
ኒክ ብሪውን በደይሊ ኮፊ ኒውስ ላይ ፌብሪዋሪ 8,2018 ኢትዮጵያ የቡና ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቷን አስነብቧል፡፡ ፀሀፊው አያይዞም ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና ተፈጥሯዊ መገኛ እና የአለም የቡና ዘረ-መል ሀገር መሆኗን አስታውሶ፣ ራባኮ የተባለ ድርጅት የኢትዮጵያ ቡና ፍኖተ ካርታ መዘጋጅቱ ለቡና ገዥዎች ዱካን ለማወቅ ያስችላታል ማለቱን ጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ ካለፈው በጀት ዓመት ጀምሮ የቡና ዱካን የሚያሣውቅ አሠራር መዘርጋቷ ይታወቃል፡፡
በሌላ በኩል ዘኢኮኖሚስት በኢትዮ - ጅቡቲ መንገድ በባቡር ተገጭተው የሚሞቱ ግመሎች ከገበያ ዋጋቸው እጥፍ ካሣ ስለሚያስከፍሉ አላስፈላጊ እንቅፋት ሆኗል ብሏል፡፡  ዘኢኮኖሚስት የመጀመሪያው የባቡር መንገድ ... 183 በሊቨርፑል የተገነባ ሲሆን በሳውዲአሸዋ የተነሳ እንዲሁም በኢትዮጵያ የአፍሪካው አዲስ የባቡር መንገድ በግመሎች እየተደናቀፈ ነው ይላል፡፡ እናም ይህ ድርጊት ለኢትዮጵያ መንግስት ራስ ምታት ሆኗል ብሏል ዘኢኮኖሚስት፡፡ ባቡር 2 ቀናት የሚፈጀውን ጉዞ ወደ 1 ሰዓት ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ የታሰበ ቢሆንም አሁን የሚጓዘው ፍጥነቱን በግማሽ ቀንሶ ነው ብሏል፡፡ ለአንድ ግመል መንግስት 30,000 ብር ካሣ ይከፍላል፡፡ ዘኢኮኖሚስት በመጨረሻም የድርጅቱንሥራ አመራር በመጥቀስ ባቡርን ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደ ብሔራዊ ሀብት እያዩት ሲሄዱ ሁኔታዎች እንደሚሻሻሉ ተስፋውን አስቀምጧል፡፡
ባሳለፍነው ሣምንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬቶች በስፋት በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ያገኙበት ነበር፡፡ የናይጀሪያው ዘኔሽን በአየር መንገዱ የአለም አቀፍ ኦኘሬሽን ማኔጂኒግ ዳይሬክተር አቶ ኢሣያስ /ማርያምን ቃለምልልስ ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡  አቶ ኢሣያስም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ የካርጐ አገልግሎት የማስፋፋት እቅድ እንዳላት ገልፀውአፍሪካ ብዛት ያላቸው ምርቶች ወደ ሌላው አለም የመላክ ከፍተኛ አቅም አላት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ በአፍሪካ አቪዬሽን 55 ቦታዎች በማገናኘት ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል።ስለዚህ ከአፍሪካ ወደ ሌላው አለም ኤክስፖርት ለማድረግ እና ወደ አፍሪካ የሚገቡትን በማጓጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አፍሪካዊ መንፈስ ለመፍጠር እንዳለመ ተናግረዋል፡፡
የቱርኩ አናዶሉ ኤጀንሲ በቱርክ የተማሩ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ለውጥ እያመጡ ነው በማለት / ጀላል መሐመድ ሃሰን የተባሉ ሀኪምን በእማኝነት ያስቀምጣል፡፡ /ር ጀላል ኢትዮጵያ የአፍሪካ ከተማ ስለሆነች ቱርክ ያላትን ያካበተ የጤና ልምድ በመጠቀም በአዲስ አበባ ሆስፒታል እንድትገነባ ይመክራሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት የህዝብ ፈንድ ኢትዮጵያ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ የሴቶች እና ልጃገረዶችን ጋብቻ በማስቀረት አስገራሚ ውጤት እያስመዘገበች ነው ብሏል፡፡ ድርጅቱ ለማህበረሰቡ አመቻች ሆነው እያገለገሉ ያሉትን የቆላ ተምቤይን በጐ ፈቃደኛዋን አፀደ ግርማይን በዋቢነት አስቀምጧል፡፡ እነ / አፀደ ስለ ህፃናትጋብቻ የማሰልጠኛ መፅሐፍ አላቸው፡፡ በየሣምንቱ እሁድ 35 ልጃገረዶችን በማግኘት ስለጉዳዩ ውይይት ያደርጋሉ፡፡ በትምህርት ቤት ያሉ የልጃገረዶች ክበባትም የህፃናት ጋብቻን በማስቀረት በጐ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡
ኢፒክታይምስ በድረ-ገፁ ኢትዮጵያ የስደተኞችን ካምኘ ወደ ከተማነት በመቀየር የዜግነት መንፈስ እንዲሰማቸው እያደረገች ነው ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ የሸብርተኝነት ሰለባ በመሆን እና በድርቅ ምክንያት ወደ ምድሯ የመጡ ጎረቤት ህዝቦችን ተቀብላ መጠጊያ ሆናለች ብሏል። የዶሎ ካምኘን በአካል ከጎበኘ በኋላ ኢትዮጵያተመድ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የግል ኩባንያዎች ጋር በመተባበር በረሃውን ወደ ከተማነት፣ ሠዎቹን ከጥገኝነት በማላቀቅ በራሳቸው የሚተማመኑ እንዲሆኑ በመስራት ላይ ናቸው ብሏል።
ሹንዋ በበኩሉ ኢትዮጵያ ከሩስያ ጋር ያላትን የንግድ ጉድለት ለማስተካከል እየሰራች እንደሆነ አስነብቧል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ሩስያ 24.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ ምርቶች ስትልክ በአንፃሩ 52.4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ታስገባለች፡፡ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ / / ወርቅነህ ገበየሁ የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፋቸውንም ጠቅሷል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሀገራቱ መካከል በመሰረተ ልማት፣ በንግድና ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ትስስራቸውን ለማጠናከር መስማማተቸውንም ዘግቧል።
ሽንዋ አክሎም ቻይና የኢትዮጰያ ኤክስፖርት ዋነኛ መዳረሻ መሆኗን ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ቻይና ባለፉት 6 ወራት 144.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ምርቶችን መላኳን አስፍሯል፡፡ የቅባት እህሎች የቆዳ ውጤቶች ቡናና የኤሌክትሪክ ምርቶች ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸው ዋና ዋና ምርቶች እንደሆኑ ዘግቧል፡፡
ዘገባዎቹ ሀገራችን ተጨባጭ ተስፋ ያላት መሆኗን የሚያሳዩ ናቸው። እስካሁን ያሉንን ስኬቶች ለላቀ ውጤት ልንጠቀምባቸው ይገባል። ለምሣሌ የሶማሊያ ስደተኞች አያያዝ በሀገራችን እየላላ የመጣውንማህበራዊ ካፒታልእንደገና ለመጠገን ልናውለው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ እንኳን የሀገሯን ዜጐች ቀርቶ ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን መጠጊያ እና መኖሪያ መሆኗን በማሣየት እየላላ የመጣውን ማህበራዊ አንድነታችንን መልሰን ለመጠገን ያስችላል፡፡
ፍራንሲስ ፋኩዋሚ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማህበራዊ ካፒታልን ያጠናክራል የተጠናከረ ማህበራዊ እድገት ኢኮኖሚያዊ እድገትንና ልማትን ያፋጥናል ይላል፡፡ ማህበራዊ ካፒታል ለማጠናከር ደግሞ ሚዲያ፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ ክበባት፣ ወዘተ.. ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
የሀገሪቱ እድገት በመላው አለም እውቅና እያገኘ መምጣቱ ዛሬ የሥራ እድል ያላገኘው ወጣት ነገ ምቹ ሁኔታዎች እንዳለ በማሣወቅ ተስፋ እንዲሰንቅ የሚያደርግ ነው። ኢኮኖሚስት እንደሚለው የአፍሪካ ወጣቶች 3 ነገሮች ይፈልጋሉ፡፡ ትምህርት፣ ነፃነት እና የሥራ እድል። ወጣቶች የነገ ተስፋቸው የለመለመ መሆኑን ማሣየት የሚገባቸው ማህበራዊ ካፒታል የመገንባት ሃላፊነት ያለባቸው ተቋማት ናቸው፡፡ በራሱ የሚተማመን እና ተስፋ ያለው ወጣት መገንባት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ በራስ መተማመን ለዜጋም ለሀገርም ራዕይ መሣካት ወሳኝ ነው፡፡
ወጣቶች በሀገራቸው እና በመሪዎቻቸው ላይ እምነት እንዲኖራቸው ማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት መሠራት አለበት፡፡ ቢል ኮሲእምነት አለምን ይቆጣጠራልይላል። ስለዚህ ወጣቶች ነገ የራስ እድል እንደሚያገኙ እና ህይወታቸው እንደሚቀየር እርግጠኛ መሆን መቻል አለባቸውሠዎች ወደ ጦርነት የሚሄዱት እንደሚያሸንፉ እርግጠኛ ከሆኑ ነው፡፡ ሠዎች ትዳር የሚመሠርቱት ትዳሩ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው አስቀድመው እርግጠኛ መሆን ስለቻሉ ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ እንደ መተማመን ሀይለኛ ሀይል የለም፡፡ በሌላ በኩል በነገው ላይ እምነት የሌለው ሠው ህልሙ ይጨልማል፡፡ በሀዘን ማቅ ውስጥ ይኖራል፡፡ 
የሰው ልጅ እንቅስቃሴ እና ውጤታማነት በቀጥታ ከመተማመን ጋር የተያያዘ ነው፡፡ መተማመን ካለ ለድርጊት ትነሳሳለህ፣ ለድርጊት ስትነሳሳ ውጤት ታስመዘግባለህ፣ ውጤት ደግሞ ለሌላ ስኬት ይጋብዝሀል፡፡ በህልምህ እምነት ካለህ በመጪው ጊዜ ተስፋ ይኖርሀል፡፡ ከዚያም የሩቅ ጉዞ ለመጓዝ ሀይል ታገኛለህ፡፡  ህልምህም እውን ታደርጋለህ ይላል ቢል።
ስለዚህ የሀገሪቱ የዛሬ እድገት የወጣቶችን ተስፋ መሆኗን ማሳየት ይገባናል፡፡ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ በአግባቡ መንስኤውን በመመርመር ለዘላቂ መፍትሄ መጠቀም ይገባል፡፡ቀውስ በቻይና ሁለት ትርጉሞች አሉት፡፡ አንደኛው መልካም አጋጣሚ ሌላኛው ስጋትየቀድሞው የአሜሪካ ኘሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬነዲ ናቸው የተናገሩት፡፡
መንግስትም ከተለያዩ ክፍላተ አለማት የሚመጡ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የሚያስመሰግነው ቢሆንም ኢንቨስተሮቹ በየአካባቢው ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን መከታተል እና ተጠያቂነት ማስፈን ለኩባንያዎቹም አዋጭ እና ዘላቂነት በማድረግ የየአካባቢው ህዝብ በመንግስት ላይ እምነት እንዲኖረው ማድረግም ይገባዋል፡፡

No comments:

Post a Comment