EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Saturday 28 October 2017

ቀጣይነት ያለው የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል ለልማታዊ አስተሳሰብ የበላይነት!



(በወጋገን አማኑኤል)
የኢትዮጲያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግምባር /ኢህአዴግ/ ለዘመናት በእሳት የተፈተነ በርካታ ስር የሰደዱ ውስብስብ ችግሮች ሳይበግሩት በፅናት በመቆም አገር መምራት የቻለ ጠንካራ ተራማጅ ፓርቲ ነው፡፡ ኢህአዴግ ገና ከምስረታዉ ጀምሮ የሚያጋጥሙትን ችግሮች በድርጅቱ ዲስፕሊን መሰረት እልባት እየሰጠ፤ በርካታ ድሎችን እያስመዘገበ መምጣት የቻለ ድርጅት ነው፡፡ አብዮታዊዉ እና ዴሞክራሲያዊዉ ኢህአዴግ በተለያየ ጊዜ የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች እንደ ዕድል አይቶ ተምሮባቸው ለተሻለ ስኬት ሌት ተቀን የሚታትር ድርጅት መሆኑን ያለፉት ዓመታት ተግባራቶቹ አብይ ማሳያ ናቸው ብየ አምናለሁ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች መጠናቸዉ የተለያየ አለመረጋጋቶች መከሰታቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም ዉድ በሆነዉ የሰዉ ልጅ ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ተከትሏል፡፡ የዚህ እኩይ ተግባር ዋነኛ ተዋናዮችንም ህብረተሰቡ እና የፍትህ አካላት በጥምረት በመስራት በህግ ተጠያቂ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን አገራችንን የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን የችግሮችን መንስኤ በማጤን እነዚህ ችግሮች ከመሰረታቸው ለመፍታት የሚያደርገው ጥረትም ውጤት እንደሚያመጣ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡
አሁንም ቢሆን በጅምር ደረጃ የሚጠቀሱ ቢሆንም የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው፡፡ ኢህአዴግ ችግሮች ሲፈጠሩ በሰከነ መንገድና ብሰለት በተሞላበት አካሄድ መፈታት እንዳለበት የሚያምን ድርጅት ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ አለመረጋጋቶችንና አንዳንድ ሁነቶችን መነሻ በማድረግ ድርጅቱን በቅጡ ካለመገንዘብ የሚመነጩ አስተያየቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲሰነዘሩ ይደመጣል፡፡  
ሁላችንም እንደምንገነዘባው ኢህአዴግ ላለፉት ዓመታት ባደረጋቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በእኔ እምነት ለውጡ የፈጠራቸው አዳዲስ እና አዳጊ  ህዝባዊ ፍላጎቶችንም መሰረት በማድረግ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ኢሕአዴግ ከህዝቡ ጋር በመሆን እየተጋ ያለ ደርጅት ነው፡፡ ድርጅታችን እያደረገዉ ያለዉ መጠነ ሰፊና ስር ነቀል ትግል እንደ ከዚህ ቀደሙ ከሰፊዉ ህዝብ ጋር በመሆን ለፍሬ እንደሚበቃ ጥርጥር የለኝም፡፡   
በአገራችን ለውጥ እየተመዘገበ በሄደ ቁጥር የሚፈጠሩ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራት ሁሌም ቢሆን ተግዳሮት ሆነው የሚቀጥሉና ሁሌም ቢሆን ትግል የሚፈልጉ መሆናቸው አጠያያቂ አይመስለኝም፡፡ ገዥው ፓርቲ ኪራይ ሰብሳቢነት የስርዓቱ አደጋ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራትና ለማራገፍ ቀጣይነት ያለው ትግል እንደሚያስፈልግ እሙን ይመስለኛል፡፡ ይህ ልማታዊ መስመራችንን እየተፈታተነ ያለውን ኪራይ ሰብሳቢነት የተጠናወተውን ሃይል ኢህአዴግ በገነባው በሳል የትግል መስመር እያጠራው የሚሄድና አሁን ከገባንበት ውስብስብ ችግር በመላቀቅ ወደፊት መራመዱን የሚቀጥል እንደሆነ ባለሙሉ እምነት ነኝ፡፡
ኢህአዴግ የህዝባችንን የዘመናት የልማት ጥያቄ እየመለስ ታሪክ እየሰራ ራሱን እያደሰ ለላቀ ድል እያዘጋጀ የሚሄድ ህዝባዊ ድርጅት መሆኑን ከታሪኩ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለሚያጋጥሙት ፈተናዎች በፅናት ታግሎ የማለፍ ልምዱ አሁንም አብሮት ያለው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ከዚህ አኳያ የልማታዊ አስተሳሰብ የበላይነት እንዲቀዳጅ የሞት የሽረት ትግል የሚፈልግና በመሆኑ አባሉና አመራሩ የኢህአዴግ መለያ ባህሪዎችን ተላብሶ፤ ድርጅታዊ ስብእናውን ጠብቆ፤ ተራማጅ በሆነ አስተሳሰብ የመሪነት ሚናው ወስዶ ራሱን ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ነፃ በማድረግ በተግዳሮቶች ሳይረታ ቀጣይነት ያለው ትግል ማድረግ ይጠበቅበታል ብየ አምናለሁ፡፡

2 comments:

  1. This comment has been removed by the author.

    ReplyDelete
  2. It’s a great advice! Political commitment is must be added to solve the root of all problems. I know this party for years and currently it looks like the party is loosing its marks by so called musagnoch! For the sake of Ethiopia EPRDF must be strong, democrat, and inclusive! I don’t want to see the failur of this party! Instead I want to see its glorious work to be remain for generations to come! Currently I’m worried by mistakes done by this party to loose everything done by itself! We need wise, decisive and decision makers at this time! We need ethiopian! Not for ourselves but for generations !!!! Ethiopia be keberrr lezelalem tenur!!! Thank you for ur service all past and current leaders

    ReplyDelete