EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Wednesday 11 October 2017

የዘርፈ ብዙ ድሎች ባለቤት- ደኢህዴን

ክሩቤል መርኃጻድቅ
ሁሉም የሀገራችን ህዝቦች በበርካታ የጭቆና ታሪክ አልፈዋል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦችም በአፄዎቹም ሆነ በአምባገነኑ የደርግ ስርዓት የደቡብ ክልል ብሄሮች፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ረጅም ጊዜ የቀጠለ አስከፊ ብሄራዊና መደባዊ ጭቆናና አድሎ ሲደርስባቸው ቆይቷል፡፡ ስርዓቶቹ ጸረ- ብዙኃነት መሆናቸው ደግሞ የተለያዩ ማንነቶች፣ ቋንቋዎች፣ እምነቶችና እሴቶች ባለ ቤት ለሆኑ የደቡብ ክልል ህዝቦች ብሄራዊና መደባዊ ጭቆናዉ የከፋ እንዲሆን አድርጎት ቆይቶዋል፡፡ በዚህም መሰረታዊ የሆኑ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውንና ነፃነታቸውን አጥተው እንዲኖሩ፣ በተለይም በአጼዎቹ ዋነኛው የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነውን መሬታቸውን ተነጥቀው የበይ ተመልካች እንዲሁኑና በድህነት ስር እንዲማቅቁ ተገደው ነበር፡፡

በሀገሪቱ ተንሰራፍቶ የነበረውን ጭቆና ለማስወገድ በተለይም 1960ዎቹ ይደረጉ ከነበሩት  የለውጥ እንቅስቃሴዎች መካከል የተማሪዎች ንቅናቄ ተጠቃሽ ሲሆን በወቅቱ በዋናነት ሶስት መሠረታዊ ጥያቄዎች  ማለትም የብሔርና የሃይማኖት እኩልነት፣ የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት (የመሬት ባለቤትነት) እና የደሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶች ጥያቄ በማንገብ የተካሄዱ እንቅስቃሴች ነበሩ፡፡
የለውጥ ጥያቄው ለህዝቦች መሰረታዊ ጥያዎች ሁሉ ሥር-ነቀል ዴሞክራሲያዊ ምላሽ የሚጠይቅ ነበር፡፡ በመሆኑም የተማሪዎች እንቅስቃሴ ዴሞክራሲያዊና የሁሉንም የአገሪቱን ህዝቦች ጥያቄ ምላሽ የሚሻ ታላቅ ትግል ነበር፡፡ ይኼው የተማሪዎች እንቅስቃሴ በቀጣይ በሀገራችን ለተደረጉ የለውጥ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ ነበር፡፡ 
በወቅቱ የለውጥ እንስቃሴ ያካሂዱ ከነበሩ ድርጅቶች አንዱ በሆነው ኢህአፖ በመባል በሚታወቀው ድርጅት ውስጥ በርካታ የደቡብ ህዝቦች ተወላጅ ተማሪዎችና ምሁራን በፖርቲው ታቅፈው ታግለዋል፡፡ 
ይሁንና ኢህአፖ በተከተለው የተሳሳተ የትግል ስልትና የአመለካከት ጥራት ጉድለት ሳቢያ ጉዞው በአጭሩ ሊቀጭ ችሏል፡፡ ከፖርቲው የተነጠሉና ትግሉ መቀጠል እንዳለበት ጽኑ እምነት የነበራቸው ጥቂት ታጋዮችየኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን” /ኢህዴን/ ከመሠረቱ በኋላ ድርጅቱ ህብረ-ብሔራዊ በመሆኑ ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ የክልሉ ተወላጆች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነበር፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ እየተጠናከረ ሲመጣ በንቅናቄው ውስጥ የደቡብ ክልል የየብሔረሰቡ ተወላጆች ተሳትፎም እየጨመረ መጥቶ ከሰባት መቶ በላይ የደቡብ ተወላጆች በኢህዴን ውስጥ ታቅፈው እንደነበረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የታጋዮቹ ዋና ተሳትፎቸው በኢህዴን ውስጥ ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ ማለትም 1967 ዓም በተመሳረተውና ጠንካራ ትግል ያደርግ በነበረው በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) ውስጥም ታቅፈው ሲታገሉ የነበሩ የደቡብ ተወላጅ ታጋዮች ነበሩ፡፡
የደርግ ስርዓት መገርሰስ አይቀሬነት እየተረጋገጠ በመጣባቸው ዓመታት በኢህዴንና በህወሓት ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወላጅ የሆኑ ታጋዮች የክልሉን ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ትግል መምራት የሚያስችላቸውን አደረጃጀት ለመመስረት እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡
1981 . መጨረሻ አካባቢ በዋናነት በኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን) ውስጥ ሲታገሉ ከነበሩ የደቡብ ተወላጅ ታጋዮች መካከል አርባ አምስት ያህል አመራሮች የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን የሚያታግል ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እንዴት መመሥረት አለበት በሚለው ጥያቄ ብዙ ጊዜ የወሰደ ሰፊና ነፃ ውይይት አድርገዋል፡፡
በመቀጠልም አመራሮቹ ወደ አባላት በመመለስ ቅድመ ዝግጅት ካደረጉ በኋላ ከእያንዳንዱ የኢህዴን ብርጌድ ቁጥራቸው 1300 ያህል የደቡብ ታጋዮችን በማሰብሰብና የአባላት ኮንፈራንስ በማካሄድ ታህሣሥ ወር 1982 . በትግራይ ክልል ሽሬ እንደሰላሴ ከተማ በስተደቡብ ምዕራብ አስር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝው ማዕበራ በሚባል ቦታ ላይየስምጥ ሸለቆ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ታጋዮች መሸጋገሪያ ማህበር" ተመስርቷል፡፡
በሰ የሀገራችን ክፍል የህዝቡን የዘመናት ጥያ የሚፈታበትን ስልት በአግባቡ ተረድተው ትግል በጀመሩ የህወ እና ኢህ ታጋዮች የተጀመረው አብዮታዊ ደሞክራሲያዊ ትግል ብዙ ተከታዮችን ማሰለፍ በመቻሉ በአብዮታዊና ደሞክራሲያዊ መስመር ትግሉን የተቀላቀሉት የደቡብ ሮች፤ ረሰቦችና ሕዝቦች ልጆችም የህዝቡን የዓመታት መሰረታዊ የነጻነት፤ የደሞክራሲ፤ የእኩልነትና የመልማት ጥያዎችን በትግል የመለሰ አብዮታዊ ድርጅት ቋቋ ችለዋል፡፡ ሕዝቡ በተበታተነ ሲያካሂድ የነበረው የዓመታት ትግል በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት መመስረት አፍርቶ የክልሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አካል አድርጓል፡፡
ጥር 1983 . የኢህአዴግ የመጀመሪያ ጉባዔ ሲካሄድ ስምጥ ሸለቆ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ታጋዮች መሸጋገሪያ ማህበር አባላት ተመርጠው በጉባዔው በድምጽ ተሳትፈዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የማህበሩ አባላት በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው በትጥቅ  ትግሉ ወቅት  የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡ የመጀመሪያው የስምሪት ዘርፍ ሥልጠና ሲሆን በዚህ ዘርፍ የተመደቡ ታጋዮች በየማሰልጠኛ ጣቢያው ለሰራዊቱ የወታደራዊ ሣይንስና የፖለቲካ ብቃት ሥልጠና ይሰጡ ነበር፡፡ ሁለተኛው ዘርፍ ደግሞ የክፍለ ህዝብ ስምሪት ሲሆን ይህም ህዝቡን የማደራጀት፣ የማንቃትና የማስታጠቅ ሥራ ነበር፡፡ ሌላው ደግሞ በአውደ ውጊያዎች በመሳተፍ የደርግን ኃይል የመደምሰስ ተልዕኮ ነበር፡፡ የማህበሩ አባላትም ሆኑ በማህበሩ ሳይታቀፉ በኢህዴን ዉስጥ ሆነው ትግላቸውን የቀጠሉ የደቡብ ተወላጅ ታጋዮች በእነዚህ ዘርፎች በመሰማራት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት ለፋሽስቱ ሥርዓት መደምሰስ የድርሻቸውን ተጫውተዋል፡፡
ማህበሩ የተመሠረተው በትግሉ የመጨረሻ ወቅት ቢሆንም የማህበሩ አባል ታጋዮች ማህበሩ ከመመስረቱ በፊትም ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ ትግሉ በተጠናቀቀበት ሰሞንም ቢሆን በትግሉ ወቅት በመሳተፍ፣ የበኩሉን መሰዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ማህበር እንደነበረ መረዳት ይቻላል፡፡
የማህበሩ ትግል፣ ጥንስስ መነሻ የሚያሳየው ደረጃ በደረጃየስምጥ ሸለቆ ታጋዮች መሸጋገሪያ ማህበርወደተሟላ አብዮታዊና ዴሞክራሲያዊ ድርጅትነት ቀይሮ በደቡብ አከባቢዎች የሚካሄደውን ትግል በመሪነት ተረክቦ ካስኬደበት ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ታጋዮቹ በየትግል ምዕራፉ ህዝብን እንዴት ከጎናቸው ማሰለፍ እንደሚችሉ በተለያዩ የህዝብ አመራር ጥበቦች ላይም ቀደም ሲል  ሰልጥነዋል፡፡ 
የማህበሩ ተጋዮች ደርግ ከወደቀ በኃላም ሰላምና መረጋጋትን የማስፈን፣ የኢህአዴግን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣የማህበራዊና የውጭ ግንኙነት ፕሮግራሞችን ማስተዋወቅ እንዲሁም የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደቱን ማመቻቸት ተልዕኮዎችን ለመወጣት ተግተው ተጋለዋል፡፡   ህገ መንግስት በማርቀቅና በማጽደቅ ሂደቱም በታጋዮቹ ትከሻ ላይ የወደቀ ተግባር ነበር፡፡ ለደኢህዴግ ምስረታም ታላቅ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡
አዲሲቷ ኢትዮጵያ የሁሉም ብሔሮችና ብሔረሰቦች መብት የተረጋገጠበት፣ ፍትህና እኩልነት ሊያሰፍን የሚችል ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ መሆን የጀመረበት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት እየተረጋገጠ የመጣበትና በአዲስ አቅጣጫ ለዘላቂ ሠላም ዋስትና የሆነ ፌደራላዊ ሥርዓት መገንባት የጀመረች አገር ናት፡፡ የደቡብ ክልልም በደኢህዴን/ኢህአዴግ እየተመራ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አንዱ አካል እንደመሆኑ የሁለንተናዊ ለውጥ ተቋዳሽ ሆኗል፡፡
በደኢህዴን/ኢህአዴግ መሪነት ፀረ- ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ከተወገደ በኋላ ለዘመናት ያጡትን መብት ዕውን የሚያደርግ ህገ-መንግስታዊ ፌደራላዊ የመንግስት አደረጃጀት ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ የፌደራል ስርዓቱ ብዙሃነትን ሊያስተናግድ የሚችል ሆኖ የተዋቀረ ሲሆን  የክልሉ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በቀድሞ ጊዜ የተነፈጉትን መብት፤ ታፍኖ የነበረው ታሪክ፤ ቋንቋ፤ ባህልንና ሌሎች የማንነት መገለጫዎችን በህገ-መንግስት ዋስትና እንዲያገኙና በተግባርም ተፈጻሚ ማድረግ በመቻሉ የማንነት መገለጫ የሆኑትን ራስን በራስ የማስተዳደር፤ ቋንቋ፤ ባህልንና ታሪክን ማጥናት፣ መንከባከብና ማጐልበት የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡
ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያለገደብ የተጠበቀ ነው ሲባል የክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በቋንቋቸው የመናገር፤ የመጻፍ፤ ቋንቋውን የማሳደግ እና ባህሉን የመግለጽ ወይም የማሳደግና የማጎልበት፤ የማስፋት እንዲሁም ታሪካቸውን የመንከባከብ መብቶች ያለ ገደብ እንዲከበሩ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ደኢህዴን እነዚህ መብቶች በክልሉ ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ በመርህ ላይ ቆሞ በጽናት በመታገሉ በዚህ ረገድ ባለፉት 25 ዓመታት አስደናቂ ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡
በደኢህዴን መሪነት የደቡብ ክልል ህዝቦች ከጭቆና ቀንበር ተላቀው ራሳቸውን በራሳቸው ህገ መንግስቱ ባጎናጸፋቸው መብት አከባቢያቸውን እንዲያለሙ፣ ባህላቸውን፣ ቋናቋቸውንና ሌሎች እሴቶቻቸው ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል፡፡ በቋንቋው የመማርና ቋንቋውም በመገናኛ ብዙኃን ሽፋን የማግኘት መብት ተጎናጽዋል፡፡ በዚህም መገናኛ ብዙኃኑ በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲጫወቱ ተደርጓል፡፡ በደኢህዴን መሪነት በተመዘገበው ሁለንተናዊ ፈጣን ዕድገትም የክልሉ ህዝቦች ከልማቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ 
የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በመጀመርያ ደረጃ የወሰደው እርምጃ በመሬቱ ላይ ያለው ሙሉ መብቱን የማረጋገጥ ሲሆን አርሶአደሩ መሬቱን የመንከባከብ፣ የማውረስ፣ ለትውልዱ ማስተላለፍ፣ ማከራየት ሁሉ የሚችልበትን ሙሉ መብት በመረጋገጡ  አርሶአደሩ በይዞታው ላይ ያለው አመለካከት እንዲለወጥ አድርጎታል፡፡ የግብርና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ በርካታ ስራዎች በመከናወናቸው ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፡፡
ደኢህዴን በክልሉ ለዘመናት የነበረውን የመሰረተ ልማት ችግር ለምፍታት ባደረገው ርብርብ አመርቂ ወጤቶችን አስመዝግቧ፡፡ 1990 . በክልሉ አጠቃላይ የመንገዶች ርዝመት 2910 ኪሎ ሜትር ብቻ የነበረ ሲሆን  የመንገዶች ርዝመት 15356 ማድረስ ተችሏል፡፡
በማህበራዊ ልማት ረገድም ቢሆን ባለፉት ስርዓቶች ትምህርትና ጤና እንደሰማይ ርቋቸው የነበሩ የገጠር ቀበሌዎችንም ጭምር ትምህርት ቤቶችና የጤና መስጫ ተቋማት ተጎንብቶላቸዋል፡፡ በትምህርት መስክ ስናይ 1987 . በክልሉ 1ኛና 2 ደረጃ /ቤቶች 801867 ተማሪዎቸ ብቻ በትምህርት ላይ ከነበሩበት 2009 . አጠቃላይ ክልላዊ የቅበላ አቅማችንን 5ነጥብ2 ሚሊየን በላይ ማድረስ መድርሱ በማህበራዊ መስክ ላይ ምን ያህል አመርቂ ውጤት መመዝገቡ መገንዘብ ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ደኢህዴግ  በርካታ ውጣ ውረዶችን እያለፈ የመጣ ድርጅት ነው፡፡ በአገሪቱ ብሎም በክልሉ  በረጅም ዘመናት በማሽቆልቆል ጉዞ ውስጥ የቆየ፣ ድህነትና ኋላቀርነት ሥር የሰደደበት፣ የጠባብነትና ትምክህት አመለካከትና ተግባር ሊሸከሙ የሚችሉ ነባራዊ ሁኔታዎች መሠረት የያዘበት በድምሩ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊነትን ሊያደናቅፉ የሚችሉ ማነቆዎች የሞሉበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ተረክቦ ሲሆን  ይህንኑ ነባራዊ ሁኔታ ሊቀይር የሚካሄድ ትግልና ፍልሚያ እልህ አስጨራሽ ውስብስብ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት እነዚህ ተግዳሮቶች እየተፈታተኑት ነገር ግን በከፍተኛ ብስለትና ህዝባዊነት ችግሮችን እየፈታ በዕድገት ጐዳና እየገሰገሰ ያለው ህዝባዊ መሰረት ያለው ድርጅት ነው፡፡

No comments:

Post a Comment