EPRDF is a ruling party committed to realize Ethiopia's Renaissance.

Tuesday 1 November 2016

የካቢኔ አባላት ፕሮፋይል



የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥቅምት 22/2009 ለህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ያቀረቧቸው የካቢኔ አባላት በምክር ቤቱ ሙሉ ድምፅ ሹመታቸው ፀድቆላቸዋል፡፡ የአዲስና ነባር የካቢኔ አባላትን ዝርዝር የስራ ልምድና የትምህርት ይዞታቸው በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ሙሉ ንግግር (ፅሁፍ) ተከታዩ ነው፡፡

1. ለኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት
/ ወርቅነህ ገበየሁ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-    የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት፣
-    ማስተርስ ዲግሪ (MA) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለም አቀፍ ግንኙነት፣
-    .ኤች. (PHD) University of South Africa (UNISA) በፖሊሲ ሳይንስ አግኝተዋል፡፡
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    1985-1991 . በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች፣
-    1992-1993 . በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣
-    1994-2005 . መጨረሻ ድረስ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣
-    2005 ሃምሌ እስከ አሁን የትራንስፖርት ሚኒስትር በመሆን፣
ከላይ በተዘረዘሩት ቦታዎች ባገለገሉባቸው ዘመናት የህዝቡንና የሀገሪቱን ሰላም የሚያስጠብቁ ስኬታማ ተግባራት በማከናወናቸው ዘመናዊና የፖሊስ ሰራዊት ግንባታ ሂደት ጠንካራ አመራር የሰጡ፤ በትራንስፖርት ሚኒስትርነታቸው ዘመን የመንገድ መሰረት ልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የከተማና ሀገር አቀፍ የባቡር መሰረተ ልማት የመንግስት በሰጠው አቅጣጫ መሰረት በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲሳኩ የበኩላቸውን ጉልህ የአመራር ድርሻ አበርክተዋል፡፡ የከተማ ትራንስፖርት ስርዓት የሚያሻሽሉ ውጤታማ ስራዎች የሰሩ በመሆናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ቢያገለግሉ ለሀገራችን ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

2. ለኢፌዴሪ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትርነት
አቶ ታገሰ ጫፎ
ብሔር ጋሞ
የትምህርት ዝግጅት
-    በስነህይወት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ (BSC) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-    ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በአሳ ሳይንስና እርባታ ከህንድ ሀገር፣
-    የማስተርስ ዲግሪ (MBA) በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ኦፖን ዩኒቨርሲቲ፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    በወረዳ አመራርነት ለሁለት አመታት፣
-    በዞን አመራርነት ለስድስት አመታት፣
-    የደ/////መንግስት የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣
-    የደ/////መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
-    የደ/////መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ በድምሩ በክልል አመራር ደረጃ 10 አመታት፣
-    2007 . ጀምሮ የኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
 ከላይ በተጠቀሱት የስራ ጊዜያት የከተማና የገጠር ኢንቨስትመንት በክልሉ ለማስፋፋት ስኬታማ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው የክልሉ የንግድ ሪፎርም ፓኬጅ በተሟላ ሁኔታ እንዲደራጅ በማድረጋቸው የመንግስት የሪፎርም ስራዎች የስራ ሂደት ለውጥ አመራር በተሻለ ሁኔታ እንዲፈፀም የጎላ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው፤ በክልሉ የፍትህ ዘርፍ ስራዎች የመልካም አስተዳደር ፓኬጅ ዝግጅት በተሻለ ስለመሩ በፌዴራል ስራ የመልካም አስተዳደርና የሌሎች ጥናቶች በጥልቀት እንዲጠኑ በማስተባበራቸውና ውጤታማ በመሆናቸው በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ቢያገለግሉ ለሀገራችን ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

3. ለኢፌዴሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትርነት
/ አብርሃም ተከስተ
ብሔር ትግራይ
የትምህርት ዝግጅት
-    የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በኢኮኖሚክስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-    ማስተርስ ዲግሪ (MA) በኢኮኖሚክስ ፖሊሲ አናሊሲስ፣
-    ዶክትሬት ዲግሪ (PHD) በኢኮኖሚክስ ከእንግሊዝ ሀገር፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    1983-1991 . ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ኢኮኖሚስት በቀድሞ የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር፣
-    1996-1998 . የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባው ዋና አማካሪና የከንቲባ /ቤት ኃላፊ፣
-    1998-2003 . የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲ፣ ጥናትና እቅድ ቢሮ ኃላፊ፣
-    2003-2008 . የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣
-    2008 . መጀመሪያ ጀምሮ በብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሲሆኑ፣
አንደኛውንና ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዝግጅት ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ በማድረግ የአገሪቱን ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በመከታተል መንግስትን በማማከርና ለህዝቡ በማሳወቅ ውጤት ያስገኙ የሀገሪቱ የበጀት ስርዓት በውጤት ላይ ተመስርቶ የፕሮግራም በጀት ስርዓት እንዲሸጋገር በማድረግ፤ አገራዊ የከተማ ልማት እና መልካም አስተዳደር ፕሮግራሞችን በዝርዝር በማዘጋጀትና ወደ ትግበራ እንዲሸጋር በማድረግ በከተማና ቤቶች ፕሮግራም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የወጣቶች ልማት ፕሮግራም በከተሞ መሰረተ ልማት ፕሮግራም ውጤት እንዲገኝ የጎላ አስተዋፅኦ በማድረጋቸውና ውጤታማ በመሆናቸው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ሀገራችንን ቢያገለግሉ ውጤት ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

4. ለኢፌዴሪ እርሻና፣ የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትርነት
/ እያሱ አብርሃ
ብሔር ትግራይ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያና ማስተርስ ዲግሪያቸውን በአግሮኖሚ በማዕረግ ከራሺያ ሳብ ትሮፒክስ ኢንስቲትዩት፣
-       .ኤች. (PHD) በእፅዋት ሳይንስ ከቼክ ሪፐብሊክ ፕራግ ዩኒቨርሲቲ፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          1986-1993 . ድረስ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የዞን ኤክስቴንሽን ኃላፊ አግሮኖሚስት፣
-          1994-1995 . የትግራይ ግብርና ቢሮ የአዝርዕት ክፍል ኃላፊ፣
-          2001-2003 . ድረስ የመቐለ እርሻ ምርምር ኃላፊና ተመራማሪ፣
-          2004 . እስከ አሁን የትግራይ የእርሻ ምርምር ዋና ዳይሬክተር፣
በመሆን የሰሩ ሲሆኑ በዘርፉ በምርምር ስራቸው የተመሰገኑና ውጤት ያስመዘገቡ በመሆናቸው መልካም ስነ ምግባር ያላቸው በመሆኑ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ቢመደቡ ለአገራችን ውጤት ያስመዘግባሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

5. ለኢፌዴሪ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስትርነት
/ ፍቃዱ በየነ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-       በእንስሳት ሳይንስ (BSC) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-       ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በእንስሳት እርባታ ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ፣
-       .ኤች. (PHD) በደሪ ቴክኖሎጂ ከነርዌይ የግብርና ዩኒቨርሲቲ፣
-       የትምህርት ማዕረግ የምግብ ሳይንስት ቴክኖሎጂ ፕሮፌሰር፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          1975-1987 . ድረስ በረዳት ሌክቸረርነት፣ በሌክቸረርነትና በትምህርትና በምርምር ስራ ተሳትፈዋል፡፡
-          1988-1991 . ድረስ የአዋሳ ግብርና ኮሌጅ ምክትል ዲን፣
-          1992-1998 . ድረስ በቀድሞ የደቡብ የአሁኑ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክስ ጉዳዮች ኃላፊ፣
-          1998-2008 . ድረስ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣
-          2008 . መጀመሪያ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፣
ከላይ በተጠቀሱት የስራ ዘመናት ከአርባ አምስት በላይ ፅሁፎችን በግልና በቡድን በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ፤ በዩኒቨርሲቲ መምህርነት፣ በተመራማሪነትና በዩኒቨርሲቲ አመራርነት ባገለገሉባቸው ቦታዎች ውጤት በማስመዝገብ የታወቁ፣ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ በተደጋጋሚ ዩኒቨርሲቲው በስራ አፈፃፀም ከአቻዎቹ ግንባር ቀደም እንዲሆን ያበቁ፣ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ አመራር ቦታዎች በኮሚቴ አመራርነትና ሰብሳቢነት የሰሩ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ኮነሰርተም በሊቀ-መንበርነት በመምራት ላይ ያሉ፤ በስራቸውና በስነ ምግባራቸው ውጤታማና የተመሰገኑ በመሆናቸው ለእንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስቴር ሚኒስትርበመሆን ሀገራችንን ቢያገለግሉ ውጤት ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

6. ለኢፌዴሪ ንግድ ሚኒስትርነት
/ በቀለ ቡላዶ
ብሔር ሲዳማ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በማኔጅመነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-       ማስተርስ (MBS) በቢዝነት ሳይንስ፣
-       .ኤች. (PHD) በስትራቴጂክ ማኔጅመንትና ቢዝነስ ፖሊሲ (NUI) አየርላንድ ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ፣
-       የአካዳሚክ ማዕረጋቸው በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          1985-1987 . ኢትዮጵያ አየር መንገድ የግዥ ባለሙያ በመሆን ሰርተዋል፣
-          1987-1989 . የወንዶ ንግድ ኩባንያ ኃላፊ፣
-          1993-1995 . የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ የፔፕሲ ዘርፍ የገበያና ሽያጭ ኃላፊ፣
-          1996-2000 . የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ የፕላንና የቢዝነስ ልማት ክፍል ኃላፊ፣
-          2000-2008 . ድረስ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት፣
-          ከመጋቢት 2008 . ጀምሮ እስከ አሁን የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሲሆኑ፣
በመንግስት የተለያዩ ተቋማትና በግል ኩባንያዎች በከፍተኛ ባለሙያነት፣ በመምህርነትና በአመራርነት በመሩባቸው ጊዜያት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በተማሪዎቻቸውና በሰራተኞቻቸው የተመሰገኑና መልካም ስነ ምግባርና የረዥም ጊዜ ልምድ ያካበቱ በመሆናቸው የንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ሀገራችንን ቢያገለግሉ ውጤት ያስመዘግባሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡
  
7. ለኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነት
/ / ጌታሁን መኩሪያ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያ ዲግሪ (BSC) ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-       የማስተርስ ዲግሪ (MSC) በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-       .ኤች. (PHD) በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዱላቡርግ ኤሲን ዩኒቨርሲቲ ጀርመን፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          በሌክቸረርነት በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ኃላፊነት አገልግለዋል፣
-          በጀርመን ዩኒቨርሲቲ በተመራማሪነት ሰርተዋል፣
-          የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ፋክሊቲ ዲን በመሆን አገልግለዋል፣
-          በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዳይሬክተር ጄነራልና በሚኒስቴር ዴኤታነት አገልግለዋል፣
11 የሚልቁ በግል በቡድን ፅሁፎችን በታወቁ አለም አቀፍ ጆርናሎች ያሳተሙ የተሰጣቸው ስራ በትጋት በታማኝነትና በቅንነት በመስራት ውጤት በማስመዝገብ የሚታወቁ መልካም ስነ ምግባር ያላቸው በመሆናቸው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ቢመደቡ ለሀገራችን ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

8. ለኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት
አቶ አህመድ ሺዴ
ብሔር ሶማሌ
የትምህርት ዝግጅት
-    ፖስት ግራጁዌት ዲፕሎማ፣ በገጠር ሀብት ማኔጅመነትና ግጭት አወጋገድ፣ የማህበራዊ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ ዘሄግ ኔዘርላንድ፣
-    ባችለር ዲግሪ በኢኮኖሚክስ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ፣
-    ማስተርስ ዲግሪ በህዝብ ተሳትፎ፣ ልማትና ማህበራዊ ለውጥ ሳሴክስ ዩኒቨርሲቲ ብራይተን ዩናይትድ ኪንግደም፣
-    ማስተርስ ዲግሪ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ለንደን ዩናይትድ ኪንግደም፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    ከታህሳስ 1990 መስከረም 1991 . በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሲኒየር ኢኮኖሚስት፣
-    ከመስከረም 1991 . እስከ ግንቦት 1994 . በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ፣
-    ከመጋቢት 1995 . እስከ መስከረም 1996 . በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአርብቶ አደርና ገጠር ልማት ኮሚቴ ሊቀ-መንበር፣
-    ከመስከረም 1996 . እስከ ጥቅምት 1997 . በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንቱ /ቤትና የካቢኔ /ቤት ኃላፊ፣
-    ከጥቅምት 1997 . እስከ መስከረም 1998 . በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ቢሮ ኃላፊ፣
-    ከመስከረም 1998 . እስከ መጋቢት 2001 . የኢትዮጵያ ሱማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ፣
-    ከመስከረም 1998 . እስከ ሐምሌ 2001 . በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአርብቶ አደርና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
-    የሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንቱ ከፍተኛ የልማት አማካሪ፣
-    የሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርናና ገጠር ልማት ምክትል የቢሮ ኃላፊ
-    ከህዳር 2001 . ጀምሮ የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን፣
ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬት የሚያስፈልግ የውጭ ሀብትን በብዛትና በጥራት ለማሰባሰብ እንዲሁም የተገኘውን ገንዘብ ለታለመለት የትኩረት መስክ እንዲውል ለማድረግ ለጋሾችን፣ አስፈፃሚ አካላትንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በመምራትና በማስተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ ለተገኘው የልማት ውጤት አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ተቋማትን በመምራት፣ የክልሉን ልማት በማረጋገጥ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የሚያግዙ ጥረቶችን በማስተባበርና የተቋማትን አቅም ግንባታ ስራዎችን በመምራት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሱማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የስራ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ክልሉ ላስገኘው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ከላይ በተገለፁት ስራዎች ውጤታማ በመሆናቸው የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ሀገራችንን ቢያገለግሉ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

9. ለኢፌዴሪ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትርነት
/ አምባቸው መኮንን
ብሔር አማራ
የትምህርት ዝግጅት
-    የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በኢኮኖሚክስ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
-    ሁለተኛ ዲግሪ (MA) በፐብሊክ ፖሊሲና ኢኮኖሚክስ ከደቡብ ኮሪያ KDI School of Public Policy and Management
-    ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በዓለም አቀፍ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት እንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ኬንት ዩኒቨርሲቲ፣
-    .ኤች. (PHD) በኢኮኖሚክስእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ኬንት ዩኒቨርሲቲ፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    1983-1987 . ድረስ የወረዳ አመራር፣
-    1990-1993 . የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ኃላፊ፣
-    1994-1997 . የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ /ቤት ኃላፊ፣
-    1998-1999 . የአማራ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣
-    2004-2005 . የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር፣
-    2006-2007 . የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
-    2008 . መጀመሪያ ጀምሮ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን፣
/ አምባቸው የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ደርግን ለመደምሰስ በተደረገው ትግል አስተዋፅኦ በማበርከት ከመልሶ ማደራጀት ጀምሮ በሽግግሩ ዘመን የወረዳ አመራር በመሆን ህዝቡን በማረጋጋት አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በድርጅትና በመንግስት እንዲሁም ክልሉን መልሶ በማደራጀት ተቋማት ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች እንዲተገበሩ በመምራትና በማስተባበር ስኬታማ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ የከተማ ልማት ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ስራዎች በክልል ላስገኙት ውጤቶች አስተዋፅኦቸው ነበረበት፡፡ ከስድስት በላይ የምርምር ፅሁፎች በህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ጆርናሎች ያሳተሙ ውጤታማ፣ በስነ ምግባራቸው የተመሰገኑ በመሆኑ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ሀገራችንን ቢያገለግሉ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

10. ለኢፌዴሪ ኮንስትራክሽን ሚኒስትርነት
/ አይሻ መሀመድ
ብሔር አፋር
የትምህርት ዝግጅት
-    የመጀመሪያ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋካልቲ፣
-    ማስተርስ ዲግሪ በለውጥና ትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ኢንግላንድ፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    1995-1996 . በአፋር ክልል በስራና ከተማ ልማት ቢሮ በዲዛይን ቡድን መሪነት፣
-    1997-1998 . PSCAP በአፋር ክልል የከተማ ልማት ማሻሻያ ንኡስ ፕሮግራም አስተባባሪ፣
-    1999-2001 GIZ የዩኒቨርሲቲ አቅም ግንባታ ፕሮግራም (UCBP) የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ፕሮጀክት ምክትል ስራ አስኪያጅና ከፍተኛ የሳይቱ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ በመሆን ግንባታው በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ስራውን በማስተባበር ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡
-    2003-2007 . መጨረሻ ድረስ ደግሞ የአፋር ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ /ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡
-    2008 . መጀመሪያ ጀምሮ በኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በማገልገል ላይ ናቸው፣
በዚህም ጊዜ ውስጥ በክልል፣ በመንግስትና በተለያዩ የልማት አጋሮች የሚሰሩ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎችን በማስተባበር አደጋ ሲከሰት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥበት በማድረግ ውጤታማ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በሌላ በኩል በክልሉ የሚሰሩ መንግስታዊ ድርጅቶችንና የልማት አጋሮችን በማስተባበር የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ተቀርፀው እንዲተገበሩ በቁርጠኝነት ሰርተዋል፡፡ በኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ብቃት ያለው አመራር በመስጠት በውጤታማነት ያገለገሉ በመሆናቸው የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ሀገራችንን ቢያገለግሉ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

11. ለኢፌዴሪ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትርነት
/ / ስለሺ በቀለ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና፣
-       የማስተርስ ዲግሪ በሃይድሮሊክስ ምህንድስናና ሃይድሮሎጂ ከኒውካስትል ዩኒቨርሲቲ ኢንግላንድ፣
-       የፒ.ኤች. (PHD) በሃይድሮሊክስና በውኃ ሃብት ምህንድስና ከድሬስደን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ማዕረግ፣
 ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          1980-1996 . በቀድሞው የአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖለጂ ኢንስቲትዩት ከጀማሪ መምህርነት እስከ ዲንነት በተለያዩ ደረጃዎች የሰሩ ሲሆን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እስኪመሰረት ድረስ ምስረታውን በኃላፊነት መርተዋል፣
-          1996-2003 . አለም አቀፍ የውኃ ምርምርና አስተዳደር ኢንስቲትዩት (IWMI) የምስራቅ አፍሪካና የናይል ተፋሰስ ኃላፊ በመሆን አለም አቀፍ ሙያተኞችን መርተዋል፡፡ በመጨረሻም የአፍሪካ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል፣
-          2003-2006 . የተ.. የአፍሪካ ኢኮኖሚክስ ኮሚሽን የውኃና የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ስፔሻሊስት ሆነው ሰርተዋል፣
-          2006 . እስከ አሁን የተ.. ኒውዮርክ በኢኮኖሚና ሶሻል ዲፓርትመንት 2030 ዘላቂ የልማት ግቦች የአቅም ግንባታ፣ የውኃና ኢነርጂ ከፍተኛ ኢንተር ሪጅናል አድቫዘይር በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
60 በላይ የምርምርና የማስተማሪያ መፅሃፍት በመፃፍና ፅሁፎችን በግልና በቡድን በታወቁ አለም አቀፍ ጆርናሎች ያሳተሙ በተለያዩ ሀገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ቦርዶችንና የጥናት ቡድኖች የመሩ ያስተባበሩ በተለይም ደግሞ በውኃና በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሰሩ ካውንስሎች አባልና አስተባባሪ በመሆን ሰርተዋል፡፡ ውኃን ማዕከል ያደረገ Think Thank በመመስረት የጊቤ 3 ግድብ የብሄራዊ ኤክስፐርት ፓናል /ሰብሳቢ በመሆን ሰርተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ኒውዮርክ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በማሰባሰብ በኢትዮጵያ የሳይንስና የሂሳብ ትምህርቶች ላይ ድጋፍ እንዲሰባሰብ በማድረግ ላይ የሚገኙ ከአገርና አህጉር አልፈው በአለም አቀፍ የፖሊሲና ስትራቴጂ ንድፍ ስራ የሚያግዙ ውጤታማ ምሁር በመሆናቸው የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ቢያገለግሉ ሀገራችንን ውጤታማ ያደርጋሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

12. ለማዕድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትርነት
አቶ ሞቱማ መቃሳ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-    የመጀመሪያ ዲግሪ በስታቲክስ (BSC) የትምህርት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-    በዚሁ የትምህርት ዘርፍ የሁለተኛ ዲግሪ (MSC) ከህንድ አገር ፓቲየላ ዩኒቨርሲቲ፣
-    በተጨማሪ በውኃ ሀብት አስተዳደር፣ በኢነርጂ ዘርፍና በተመሳሳይ ዘርፎች ላይ በአለም አቀፍና አገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ጊዜያት በተካዱ ስልጠናዎች፣ ኮንፈረንሶችና ዎርክሾፖች ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    1980-1991 . በተለያዩ /ቤቶች በፕሎንና በጀት ስራ ከፍል ከጀማሪ ባለሙያ እስከ ከፍተኛ ባለሙያ በመሆን ሰርተዋል፣
-    1992-1997 . በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውኃ ሃብት ቢሮ በፕላንና በጀት መምሪያ ኃላፊነት እንዲሁም በግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፣
-    1998-መጋቢት 2000 . በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የውኃ ሀብት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፣
-    ከግንቦት 2000-ህዳር 2001 . በኦሮሚያ ክልል የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በመሆን ሰርተዋል፣
-    ከታህሳስ 2001-መጋቢት 2004 . በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ /ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል፣
-    ከሚያዚያ 2004-መስከም 2008 . በኦሮሚያ ክልል የውኃ፣ ማዕድንና ኢንርጂ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል፣
-    ከጥቅምት 2008 እስከ አሁን የውኃ፣ መስና ኤሌሄክትሪሲቲ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን
ከላይ በተዘረዘሩት የስራ ጊዜያት በተመደቡባቸው ቦታዎች ውጤታማ ተግባር ያከናወኑ በመሆናቸው በስነ ምግባራቸው የተመሰገኑ ስለሆኑ የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ቢመደቡ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

13. ለኢፌዴሪ የአካባቢ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትርነት
/ ገመዶ ዳሌ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያ ዲግሪ (BSC) ባዮሎጂ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-       ማስተርስ ዲግሪ (MSC) በእፅዋት ሳይንስት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-       .ኤች. (PHD) በግብርና ሳይንስ ጂኦርግ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          1984 . የሁለተኛ ደረጃ መምህር፣
-          1985-1989 . የወረዳ ትምህርት /ቤት ኃላፊ፣
-          1989-1992 . በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የስልጠና ባለሙያ፣
-          1992-1993 . የዕ   ፅዋት ሳይንስ ባለሙያ በመሆን በኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ኢንስቲትዩት፣
-          1993-1995 . በቦረና የአርብቶ አደር ልማት ፕሮግራም ረዳት ተመራማሪ፣
-          1996-2003 . በዳይሬክተርነትና በክፍል ኃላፊነት በብዝሃ ህይወት ጥበቃ ኢንስቲትዩት ውስጥ ሰርተዋል፣
-          2004 . እስከ አሁን የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን የሰሩ ሲሆን፣
ሃያ አምስት የምርምር ፅሁፎችን በግልና በቡድን በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ መሆናቸው በመምህርነት፣ በተለያዩ ቦታዎች ውስጥ በተመራማሪነት፣ በባለሙያነትና አመራርነት ያገለገሉና በሰሩባቸው ቦታዎች ውጤት ያስመዘገቡ፣ በስነ ምግባራቸው የተመሰገኑ በመሆናቸው የአካባቢ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ሀገራችንን በሚያገለግሉ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡
  
14. ለኢፌዴሪ የመንግስት የልማት ድርጅት ሚኒስትርነት
/ ግርማ አመንቴ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያ ዲግሪ (BSC) በፎረስትሪ ከአለማያ ዩኒቨርሲቲ፣
-       ማስተርስ ዲግሪ (MSC) Production Forestry የስዊድሽ ግብርና ዩኒቨርሲቲ ከወንዶ ገነት ደን ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣
-       .ኤች. (PHD) In silvi-culture ከአልበርት ሊዲዊግስ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን 
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          1988-1992 . በሞጆ የማገዶ እንጨት ተከላ ፕሮጀክት ባለሙያ፣
-          1993-1996 . የአዳባ ዶዶላ የተቀናጀ የደን ፕሮጀክት ባለሙያ፣
-          1997-1998 . የኦሮሚያ ክልል የደን ልማት ኃላፊ፣
-          1998-2000 . የኦሮሚያ የመሬት አጠቃቀም /ዳይሬክተር፣
-          2001-2003 . የኦሮሚያ የመንግስት ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ዳይሬክተር፣
-          2003-ነሃሴ 2007 . የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣
-          2007 መጨረሻ ጀምሮ የምስራቅ አፍሪካ ዩኒክ የደንና የመሬት አጠቃቀም ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ ያሉ ሲሆን
 12 በላይ የምርምር ፅሁፎችንና ሪፖርቶችን በግልና በቡድን በአለም አቀፍ በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ፣ የተለያዩ የአለም አቀፍ የእውቅና ሽልማቶችንም ያገኙ ከፍተኛ ባለሙያ፣ መምህርና አማካሪ ተመራማሪና በተለያዩ ደረጃዎች በአመራርነት ያገለገሉ ውጤታማና በስነ ምግባራቸው የተመሰገኑ በመሆኑ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ቢመደቡ ለሀገራችን ለውጥ ያስመዘግባሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

15. ለኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትርነት
/ ሽፈራው /ማርያም
ብሔር ሀዲያ
የትምህርት ዝግጅት
-    በተቋማ አመራር የማስተርስ ዲግሪ፣
-    በህብረተሰብ ጤና ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪ፣
-    በህክምና ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪ፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    1985-1998 . ድረስ የደ/////መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊነትን ጨምሮ በተለያዩ ደረጃዎች መሰረታዊ ጤና አገልግሎቶችን በክልሉ በመዘርጋትና በማስፋፋት፣
-    1990-2000 . ድረስ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የፕሮግራም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የምዕተ አመቱን የጤና ልማት ግቦችን በማሳካት፣
-    2001-2007 . ድረስ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ተመጣጣይ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን በማቀድና በመተግበር፣
-    በየአካባቢው በድንበር አካባቢ የሚታዩ የድንበር ግጭቶችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው ጋር አብሮ በመስራት፣
-    የኃይማኖት አክራሪነትና ፅንፈኝነትን ለመከላከል ማህበረሰብ ተኮር ንቅናቄ በማቀጣጠል፣
-    የፌዴራል ስርዓቶች ግንባታ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በመዘርጋት በትምህት ተቋማት ተግባራዊ በማድረግ፣
-    2008 . ጀምሮ እስከ አሁን በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ አለም አቀፍ ድርድሮችን በማካሄድ የኢትዮጵያን መሪነት የማስቀጠል፣የተለያዩ ሀብት የማፈላለጊያ ሰነዶች እንዲዘጋጅ በማድረግ የአገራችንን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣
ከዚህ በላይ በተመደቡባቸው ተቋማት በሙሉ የተጣለባቸው የመንግስትና የህዝብ አደራ በብቃት የተወጡ ውጤታማ በመሆናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ቢመደቡ ለሀገራችን ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

16. ለኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትርነት
/ ይፍሩ ብርሃነ
ብሔር አማራ
የትምህርት ዝግጅት
-       በህክምና ዶክትሬት ድግሪ፣
-       የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም፣
-       የትምህርት ማዕረጋቸው የማህፀንና ፅንስ ፕሮፌሰር፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          የተለያዩ ፕሮጀክቶችና የጥናትና የምርምር ቡድኖችን የመራ፣
-          1989-1990 . የቡሌ ወረዳ ጤና /ቤት ኃላፊ፣
-          1991-1992 . የዲላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር፣
-          1998-2007 . የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት አባል የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን፣
-          2008 . መጀመሪያ ጀምሮ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ፣
-          70 በላይ የምርምር ፅሁፎችን በግልና በቡድን በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ ምሁር ናቸው፡፡
ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት ዘርፍና በአመራር ዘርፍ በመሰማራት በጤና ልማትና ምርምር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በቅርቡ በተመደቡበት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና ጤና ሳይንስ ኃላፊነት ጉልህ ውጤት ማምጣት የጀመሩ ተመራማሪ፣ መምህርና ሀኪም ሲሆኑ በስራቸው ውጤታማ፣ በስነ ምግባራቸው የተመሰገኑ በመሆኑ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ሀገራችንን ቢያገለግሉ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

17. ለኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርነት
 / ሂሩት /ማርያም
ብሔር ከምባታ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) ስነ ልሳን (የቋንቋና ጥናት)
-       የሁለኛ ዲግሪ (MA) በስነ ልሳን (የቋንቋና ጥናት)
-       .ኤች. (PHD) በስነ ልሳን ከኮለን ዩኒቨርሲቲ ጀርመን፣
-       የአካዳሚክ ማዕረጋቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስነ ልሳን ተባባሪ ፕሮፌሰር፣
 ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          1981-1988 . የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ ተመራማሪ በመሆን አገልግለዋል፣
-          1989-1995 . የአዲስ አበባ ሌክቸረር፣
-          1998-2000 . የትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የዩኒቨርሲቲዎች የፀረ ሙስና መኮንን በመሆን፣
-          2000-2002 . ድረስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ /ፕሬዝዳንት፣
-          2002 እስከ አሁን ድረስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣
31 በላይ የምርምር ውጤቶችን በግልና በቡድን አለም አቀፍ ደረጃ በጠበቁ ጆርናሎች ያሳተሙ በርካታ አለም አቀፋዊ በሆኑ ኮንፈረንሶች ሀገራቸውንና የሙያ ዘርፋቸውን በመወከል የምርምር ፅሁፎች በማቅረብ የሚታወቁ በአለም አቀፍ የምርምር ትስስር ውስጥ በቦርድ አባልነት የሚሰሩ ምሁር ሲሆኑ የሀገራችን የብሄረሰቦች ቋንቋዎች ጥናት በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው፤በተሰማሩባቸው የማስተማር የምርምርና የአመራር ችሎታቸው ውጤት ያስመዘገቡ በስነ ምግባራቸው የተመሰገኑ በመሆናቸው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትርበመሆን የሀገራችንን የባህልና የቱሪዝም ዘርፍ በብቃት ይመራሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

18. ለኢፌዴሪ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትርነት
 / ደሚቱ ሃምቢሳ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-    የመጀመሪያ ዲግሪ በህግ ትምህርት (LLB) ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
-    ማስተርስ ዲግሪ በሊደርሺፕ ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    1975-1996 . በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት፣ በወረዳ ትምህርት ቤቶች /ቤት ስራ አስኪያጅነት፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊነት፣
-    2000-2005 . በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአቃቤ ህግ ቢሮ አማካሪ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የጥቃቅንና አነስተኛ ኤጀንሲ ኃላፊ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣
-    2006-2007 . ድረስ የኤፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣
-    2008 . ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የኢፌዴሪ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር፣
በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ታታሪ፣ ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸውና የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት፣ በታማኝነትና በቁርጠኝነት በመወጣት ውጤታማ ስራ በመስራት ላይ የሚገኙ አመራር በመሆናቸው የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ሀገራችንን ቢያገለግሉ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

19. ለኢፌዴሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትርነት
አቶ እርስቱ ይርዳ
ብሔር ጉራጌ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያ ዲግሪ በልማት አስተዳደር ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
-       ሁለተኛ ዲግሪ በከተማ አስተዳደር ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          1984-2001 . ከወረዳ እስከ ዞን አስተዳዳሪነት፣
-          2001-2002 በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሶማሌ ክልል የልማት አማካሪ፣
-          2003-2004 . በጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት የማህበራዊ ፖሊሲ አፈፃፀም ክትትል ሚኒስትር ዴኤታ፣
-          2004-2007 . በግብርና ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሶማሌና አፋር ክልሎች ድጋፍ ማስተባበሪያ /ቤት ኃላፊ፣
-          2008 እስከ አሁን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላሰተር አስተባባሪና የንግድ ቢሮ ኃላፊ በመሆን፣
በተመደቡባቸው ቦታዎች ውጤታማ ስራ የፈፀሙ መንግስትና ድርጅት የሰጧቸውን ተግባራት በቅንነትና በስኬታማ መንገድ ያከናወኑ በበርካታ የአመራር እርከኖች ካያስመዘገቧቸው ውጤቶች ሲመዘን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ቢመደቡ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

20. ለኢፌዴሪ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኃላፊ ሚኒስትርነት
አቶ ከበደ ጫኔ
ብሔር አማራ
የትምህርት ዝግጅት
-       የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በህግ (LLB) ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡
-       የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሰላምና ደህንነት (Peace and Security) (MA) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡
 ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-          ደርግን ለመደምሰስ በተደረገው የትጥቅ ትግል 1976 . ጀምሮ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃዎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በታጋይነታቸው ተወጥተዋል፡፡
-          1983 . እስከ 1986 . የብአዴን የድርጅትና ፖለቲካ ዘርፍ አባልና ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡
-          1987 . እስከ 1993 . ድረስ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ አባልና የአቅም ግንባታና ሞቢላይዜሽን ዘርፍ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡
-          ከግንቦት 1997 . እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2004 . የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡
-          ከህዳር 1 ቀን 2004 . እስከ 2007 . የንግድ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል፡፡
-          2008 . እስከ አሁን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሚኒስትር በመሆን እየሰሩ ያሉ ናቸው፡፡
ከላይ በተዘረዘሩት የስራ ቦታዎች ተመድበው በሰሩባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት የተወጡ በመሆናቸው፤ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበርና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ዋስትና እንዲያገኝበትጋት ሰርተዋል፡፡ የንግድ አሰራርናሪፎርሙ ውጤታማ እንዲሆን ሌት ተቀን የተጉና የንግድ ሪፎርም ፓኬጅ በማዘጋጀት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ተደራሽ እንዲሆን ጥረት ያደረጉ በመሆናቸውና ይኽው ጥረታቸው ደግሞ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን /ቤት እንደሚደግሙት በማመን፣ በአጠቃላይ በተመደቡባቸው የድርጅትና የመንግስት ስራዎች ሁሉ በቅንነት፣ በመልካም ስነ ምግባርና በውጤታማነት አገልግሎት የሰጡ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኃላፊ ሚኒስትር በመሆን ሀገራችንን ቢያገለግሉ ውጤት ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

21. ለኢፌዴሪ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ኃላፊ ሚኒስትርነት
/ ነገሪ ሌንጮ
ብሔር ኦሮሞ
የትምህርት ዝግጅት
-    የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በእንግሊዝኛ ቋንቋ እና ስነ ፅሁፍ ከኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣
-    ማስተርስ ዲግሪ (MA) በሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ጥናት ከሃይአራባድ ዩኒቨርሲቲ ህንድ፣
-    .ኤች. (PHD) በጋዜጠኝነትና በሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ከአንድራ ዩኒቨርሲቲ ህንድ፣
-    የትምህርት ማዕረግ ረዳት ፕሮፌሰር በሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን፣
ዋና ዋና የስራ ልምዶች
-    1988-1993 . የምርምር ኤክስፐርት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣
-    1996-1997 . በጋዜጠኝነት በቀድሞ የኦሮሚያ ኢንፎርሜሽን ቢሮ፣
-    1997-2002 . ሌክቸረርና ተጠባባቂ ዲን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
-    2003 . እስከ አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን /ቤት በድህረ ምረቃ አስተባባሪነት፣
-    በአሁኑ ጊዜ ከመደበኛ ስራቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኦሮሚያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦርድ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ በመያዝ በሚዲያያ ኮሚዩኒኬሸንና በባህል ጉዳዮች ላይ ከሶስት በላይ መፅሃፍት ያሳተሙ የተለያዩ ህትመቶችን በታወቁ ጆርናሎች ያሳተሙ፣ በተመራማሪነት፣ በመምህርት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነትና የተለያዩ ከሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን የጥናትና የምርምር ስራቸው በተጓዳኝ መንግስትንና ህዝብን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በቁርጠኝነት የሚያገለግሉ መልካም ስነ ምግባር ያላቸው ውጤታማ ምሁር በመሆናቸው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን /ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ሆነው ቢመደቡ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ በማመን አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

ባሉበት የሚቀጥሉ ሚኒስትሮች

1.   አቶ ደመቀ መኮንን         የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
2.   አቶ ሲራጅ ፈጌሳ           የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሚኒስትር፣
3.   / /ፅዮን /ሚካኤል      የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር፣
4.   አቶ ካሳ /ብርሃን          የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር
5.   አቶ ጌታቸው አምባዬ        የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣
6.   አቶ አህመድ አብተው             የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣
7.   አቶ አብዱልፈታ አብዱላሂ   የኢፌዴሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
8.   አቶ አስመላሽ /ስላሴ             በህዝብ ተወካዮች /ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
9.   / ይናገር ደሴ           የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
 

No comments:

Post a Comment